«እውነት እላችኋለሁ፤ ሴቶች ከወለዱአቸው ወገን ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም» (ማቴ.፲፩፥፲፩)

…ቅዱስ ዮሐንስ ታሥሮ ከጳጉሜን ፪ ቀን እስከ መስከረም ፪ ቀን በእስር ቤት ቆየ፡፡ ያሳሰረው ሔሮድስ አንቲጳስ መስከረም ሁለት ቀን የልደት በዓሉን ያከብር ነበር፡፡ በዚህ ዕለት የሆነውን ነገር ቅዱስ ማቴዎስ በወንጌሉ በምዕራፍ ፲፬ እንደሚከተለው አስፍሮታል፡፡…

ልደቱ ለአቡነ ዘርዐ ብሩክ

በትንቢት ‹‹ከአንዲት ሴት ልጅ በጸሎቱ ዓለምን የሚያድን፣ በአማላጅነቱ ነፍሳትን የሚዋጅ ልጅ ይወለዳል›› ተብሎ ከተነገረ ከብዙ ዘመን በኋላ እግዚአብሔርን የምታመልክ ስሟ ማርያም ሞገሳ የምትባል ሴት ልጅ ተወለደች:: ያችንም ሴት ልጅ እናትና አባቷ ለአቅመ ሔዋን እስክትደርስ ድረስ እግዚአብሔርን በመፍራትና በዕውቀት አሳደጓት:: ዕድሜዋም ለትዳር ሲደርስ እናትና አባቷ እግዚአብሔርን ለሚፈራ ስሙ ደመ ክርስቶስ ለሚባል ሰው ዳሯት::

‹‹እግዚአብሔርን መፍራት›› (መዝ. ፴፫፥፲፩)

ነቢዩ ዳዊት ‹‹ልጆቼ ሆይ ኑ፥ ስሙኝ፤ እግዚአብሔርን መፍራት አስተምራቹሁ ዘንድ›› ያለን ሰው አምላኩ እግዚአብሔርን በመፍራት ሊኖር እንደሚገባ ሲገልጽ ነው፡፡ በዚሁ መዝሙር ላይ ‹‹ሕይወትን የሚፈቅድ ሰው ማን ነው? በጎ ዘመንንም ለማየት የሚወድድ ማን ነው?? አንደበትህን ከክፉ ከልክል፥ ከንፈሮችህም ሽንገላን እንዳይናገሩ። ከክፉ ሽሽ፥ መልካምንም አድርግ፤ ሰላምን ሻት፥ ተከተላትም። የእግዚአብሔር ዐይኖች ወደ ጻድቃኑ፥ ጆሮዎቹም ወደ ልመናቸው ናቸውና›› ብሏል፤ ይህም እኛ ከፈጣሪያችን ጋር እንኖር ዘንድ ማድረግ የሚገባንን ሁሉ እንድንፈጽም ነው። (መዝ. ፴፫፥፲፩-፲፭)

‹‹ለሰዎች ትታዩ ዘንድ፥ ምጽዋታችሁን በሰዎች ፊት እንዳታደርጉ ተጠንቀቁ!›› (ማቴ. ፮፥፩)

ክርስቲያኖች የሚመጸውቱት ከተረፋቸው ሳይሆን ካላቸው ነው፤ ለዚህም ምክንያቱ ደግሞ አስቀድመን እንዳየነው ምጽዋት ትልቅ የክርስትና ቁልፍ በመሆኗ ነው፡፡ ብዙዎቻችን የኃጢአት ሥር በተባለው በገንዘብ መውደድ ልባችን ስለታሰረ ምጽዋት የሚመስለን ከተትረፈረፈው ኪሳችን አንድ ብር ለነዳይ መስጠት ነው፡፡ ምጽዋት ብድሩ ከልዑል እግዚአብሔር ይገኛል በሚል እምነት ለተቸገሩ ሰዎች የሚሰጥ ልግስና እንደመሆኑ አቀራረቡ ከግብዝነትና ከከንቱ ውዳሴ የጠራ መሆን እንዳለበት ጌታችን አስተምሯል፡፡ የድሆችን ጩኸት ሰምቶ በችግራቸው በመድረስ ምላሽ የሚሰጥ እሱ በተቸገረ ጊዜ በጎ ምላሽ ከእግዚአብሔር ዘንድ ያገኛል፡፡ ምጽዋት የክፉ ጊዜ ዋስትና ነውና፡፡ (ሉቃ፳፩÷፩-፬)

‹‹ወደ ፈተና እንዳትገቡ ተግታችሁ ጸልዩ›› ማቴ.፳፮፥፵፩

……ወደ ደቀ መዛሙርቱ በሄደ ጊዜ ግን ተኝተው አገኛቸው፤ ጴጥሮስንም እንዲህ አለው ‹‹አንድ ሰዓት እንኳ ከእኔ ጋር መትጋት እንዲህ ተሳናችሁን? ወደ ፈተናም እንዳትገቡ ተግታችሁ ጸልዩ፤ መንፈስ ይሻልና፤ ሥጋ ግን ደካማ ነው፡፡››

‹‹ሦስቱ የጥፋት ገመዶች እንዳይጥሏችሁ ተጠበቁ!›› አቡነ ተክለ ሃይማኖት

ጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት በተጋድሏቸው ዘመን በአባ በጸሎተ ሚካኤል ገዳም ለዐሥር ዓመት በነበሩበት ጊዜ አገልጋዮቹ ወደ እርሳቸው መጥተው ይመክሯቸው ዘንድ ለመኗቸው፤ እርሳቸውም ‹‹ትዕግሥትን፣ ትሕትናን እና እግዚአብሔርን መፍራት ገንዘብ አድርጉ፤ እነዚህ ሦስት ነገሮች ሰውን ወደ ዘለዓለማዊ ሕይወት ያደርሱታል፡፡ እየጎተቱ ወደደይን ጥልቅነት የሚያወርዱ ሦስቱ የጥፋት ገመዶች እርሳቸውም ቅናት፣ ትዕቢትና ትምክሕት እንዳይጥሏችሁ ደግሞ ተጠበቁ›› ብለው መከሯቸው፡፡ (ገድለ ተክለ ሃይማኖት  ፵፫፥፬-፮)

‹‹ሞትን አትፍሩ፤ ኃጢአትን ፍሩ›› ቅዱስ ያሬድ

የሰው ዘር በሙሉ ምድራዊ ሕይወቱ የሚፈጸምበት ዕለተ ሞቱ በመሆኑ ከዚህች ዓለም  ይለያል፡፡ ነፍሳችን ከሥጋዋ ስትለይም ሥጋችን ሕይወት አይኖረውምና በድን ይሆናል፤ ሥጋ ፈራሽ እና በስባሽ ስለሆነም ወደ መቃብር ይወርዳል፤ ይህም ሥጋዊ ሞት ነው፡፡ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ በሚል መጽሐፋቸው ‹‹መሞት፣ መለየት፣ በነፍስ ከሥጋ፣ በሥጋ ከነፍስ መራቅ፣ እየብቻ መሆን፣ መድረቅ፣ መፍረስ፣ መበስበስ፣ መነቀል፣ መፍለስ፣ መጥፋት፣ መታጣት›› ሲሉ ስለሞት አስረድተዋል፡፡ (ኪዳነ ወልድ፣ገጽ፣፭፻፹፩)

የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ተራዳቸው

መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ ለቅዱስ ቂርቆስና ለቅድስት ኢየሉጣ ተረዳኢ የሆነበት ሐምሌ ፲፱ ቀን ታላቅ በዓል በመሆኑ ቅድስት ቤተ ከርስቲያናችንም  ታከብረዋለች፡፡ የእነዚህም ቅዱሳን ታሪክ በስንክሳር እንደተመዘገበው እንዲህ ይተረካል፡፡

‹‹የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ›› (፩ቆሮ.፩፥፴፩)

እግዚአብሔር አምላክ ኃያልና ገናና ነው፤ የሚሳነውም የለምና ሁሉን ነገር በምክንያት ያደርጋል፡፡ ሰዎችም በሥነ ተፈጥሯችን የእርሱን ህልውና በማወቅ ለፈጣሪያችን እንገዛ ዘንድ ይገባል፡፡ ድኃም ሆነ ሀብታም፣ ባለሥልጣንም ሆነ ተራ ሰው በፈጣሪው መመካት ይችል ዘንድም ተገቢ ነው፡፡ በትንቢተ ኤርምያስም እንደተገለጸው ‹‹ጠቢቡ በጥበቡ አይመካ፤ ኃያልም በኃይሉ አይመካ፤ ባለጠጋም በብልጥግናው አይመካ፤ ነገር ግን የሚመካው፡- ምሕረትንና ፍርድን፥ ጽድቅን በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኘኝ ይህ ነውና›› ሲል አምላካችን እግዚአብሔር ነግሮናል፡፡ (ኤር. ፱፥፳፫)

‹‹እግዚአብሔር በልባቸው የዋሃን ለሆኑ ቅርብ ነው፥ በመንፈስ ትሑታን የሆኑትንም ያድናቸዋል›› (መዝ.፴፫፥፲፰)

ሰዎች የዋህነት ወይንም ትሕትና ሲጎላቸው ከፍቅር ይልቅ መጥፎነት ያስባሉ፡፡ በቤተሰባዊም ሆነ በማኅበራዊ ግንኙነታቸው መከባበር እንዳይኖር፣ መናናቅ እንዲፈጠርና ክፋት እንዲስፋፋ ይጥራሉ፡፡ በዚህም ፍቅርና ሰላም አጥተው ዘወትር በስጋትና በጥላቻ ስሜት ይኖራሉ ማለት ነው፡፡