• እንኳን በደኅና መጡ !

ሰሙነ ሕማማት (በመ/ር ኃይለ ማርያም ላቀው)

ሰሙነ ሕማማት እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ያለው ፍቅር ስለ ተገለጠበት፣ የመሥዋዕትነት ሥራ የተሠራበት፣ የሰው ልጆች ድኅነት ስለ ተፈጸመበት፣ መድኃኔ ዓለም በመስቀል ተሰቅሎ ለእኛ ቤዛ መኾኑ በስፋት ስለሚነገርበት ‹ቅዱስ ሳምንት› ይባላል፡፡ በተጨማሪም ‹የመጨረሻ ሳምንት› ተብሎ ይጠራል፡፡ ይኸውም ጌታችን አምላችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዓለም በመዋዕለ ሥጋዌው ለፈጸማቸው የቤዛነትና የአርአያነት ተግባራት ፍጻሜ በመኾኑ ነው፡፡ በዚህ ልዩ ሳምንት ካህናትና […]

ሆሳዕና 🌿🌿🌿

(በመምህር ኃይለ ማርያም ላቀው) ሆሳዕና የሚለው ቃል በዕብራይስጥ ሆሼዕናህ የሚል ሲሆን ትርጉሙም እባክህ አሁን አድን ማለት ነው፡፡ አቤቱ እባክህ አሁን አድን፣ አቤቱ እባክህ አሁን አቅና፣ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ቡሩከ ነው (መዝ.117፡25-26)። የሆሳዕና በዓል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያ ጀርባ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ የሚቀድሙትና የሚከተሉት ሕዝብ በተለይም አእሩግና ሕፃናት ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ፣ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ […]

በማኅበረ ቅዱሳን የሩቅ ምሥራቅ ማእከል አባላት ዕለተ አኮቴትን (የምስጋና ቀን) አከበሩ

በሀገር ውስጥና በውጪ ባሉ የማኅበረ ቅዱሳን ሁሉም መዋቅሮች የሚከበረው ዕለተ አኮቴት (የምስጋና ቀን) በሩቅ ምሥራቅ ማእከል ተከብሯል፡፡ ዕለተ አኮቴት በየዓመቱ ከሆሳዕና በዓል ቀድሞ በሚውለው ዕለተ ዐርብ የሚከበር ሲሆን መርሐግብሩ ማኅበሩ በሚያከናውናቸው አገልግሎቶች ውጤታማ እንዲሆን የረዳውን እግዚአብሔርን የሚያመሰግንበት ነው፡፡ መርሐግብሩ በሩቅ ምሥራቅ ማእከል ስር ባሉ የተለያዩ ሀገራት የሚገኙ ወንድሞችና እህቶች በኦንላይን በተገኙበት የተከናወነ ሲሆን በአባቶች ጸሎት […]