መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
‹‹ሽማግሌዎች ከአደባባይ፥ ጎልማሳዎች ከበገናቸው ተሻሩ›› (ሰቆ.ኤር.፭፥፲፬)
በኤርምያስ ዘመን የሆነው እንዲህ ነበር፡፡ ልክ እንደ ዛሬው ክፉዎች ሠልጥነው ነበር፤ ከመከራቸው የተነሣ ልጆች፣ ድሃ አደጎችና አባት እናት የሌላቸው ሕፃናት ብዙዎች ነበሩ፤ እናቶች እንደ መበለቶች ሆነው ነበር፡፡ ውኃቸውን በብር እንጨቶቻቸውን፣ በዋጋ ገዝተው የተጠቀሙበት ጊዜ ነበር፡፡
ጽዮን ሆይ ክበቢኝ!
የገባልሽ ኪዳን የሰጠሽ መሐላ
ከንቱ ነበረ ወይ የጨረቃ ጥላ?
በአጋንንት ፍላጻ ነፍሴ ብትወጋ
ምልጃሽ ነው ተስፋዬ ከጥላሽ ልጠጋ፡፡
ጽዮን ሆይ ክበቢኝ ለውዳሴሽ ልትጋ
የኃጢአት ጎዳናዬ መንገዴ ይዘጋ!
ብፁዕ አቡነ አብርሃም እየተዳከመ የመጣው የብራና መጽሐፍ ዝግጅት ዳግም ማንሠራራቱን ገለጹ
ሐመረ ብርሃን የብራና መጻሕፍት ሥራ ድርጅት በኅዳር ፲፭፤ ፳፻፲፯ ዓ.ም. በጠቅላይ ቤተ ክህነት በአካሄደው የምስጋና መርሐ ግብር ላይ የተገኙት የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባሕር ዳርና ሰሜን ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ባስተላለፉት መልእክት የብራና መጽሐፍት ዝግጅት ረጅም ጊዜ የሚወስድ በመሆኑ እየተዳከመ የመጣ ቢሆንም ዛሬ ላይ በዚህ መልክ እያደገ መምጣቱ የሚያስደስት መሆኑን አክለው ገልጸዋል፡፡
‹‹ፈኑ እዴከ እምአርያም፤ ወአድኅነኒ፤ እጅህን ከአርያም ላክ፤ አድነኝም›› (መዝ. ፻፵፫፥፯)
ይህ ሱባኤ፣ ዘመነ ነቢያት፣ ወርኃ ጾመ ነቢያት ከመቼውም በላይ አስጨናቂዎቻችን፣ በሥጋ በነፍስ የሚዋጉን፣ አጋንንት ውሉደ አጋንንት፣ ረቂቃኑ አጋንንት፣ ልቡሰ ሥጋ አጋንንት፣ ሁሉ እንደ ጤዛ ረግፈው፣ እንደ ትቢያ ተበትነው፣ ከሕዝበ ክርስቲያንና ከቤተ ክርስቲያን ይርቁ ዘንድ፣ የክርስቶስም መንጋ በሰላም በበረቱ ያድር ዘንድ፣ ‹‹እጅህን ከአርያም ላክ፤ አድነንም›› የምንልበት ጊዜ ነው፡፡
የቅዱሳን መላእክት አማላጅነት
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! ለከበረው ጤንነታችሁ እንዴት አላችሁልን?! በፈቃደ እግዚአብሔር አዲሱን ዓመት ከተቀበልን ሁለት ወራትን አሳልፈን ሦስተኛውን ጀምረናል! ለዚህ ያደረሰን አምላክ ይመስገን! ለመሆኑ ትናንት ከነበረው ማንነታችሁ ላይ ምን ለውጥ አመጣችሁ? በዘመናዊ ትምህርትስ ምን ያህል ዕውቀትን ሸመታችሁ? በመንፈሳዊ ሕይወታችሁስ በሥነ ምግባር ምን ያህል ለውጥ አመጠችሁ? በርትታችሁ መማር ይገባል፤
….ባለፈው ተከታታይ ትምህርታችን ስለ አማላጅነት ትርጉም እንዲሁም ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ተምረን ነበር፡፡ በዚህ የትምህርት ክፍለ ጊዜያችን ደግሞ ስለ ቅዱሳን መላእክት አማላጅነት እንማራለን! መልካም!
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎችን የሃይማኖት ነጻነት የሚጋፋ መመሪያ ማውጣቱ ተገለጸ
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሃይማኖታዊ ነጻነታቸውን የሚጋፋ መመሪያ መውጣቱን ገለጹ፡፡ ዮኒቨርስቲው በ፳፻፲፯ ዓ.ም ያወጣውን የሥነ ምግባርና ዲሲፕሊን መመሪያ ተከትሎ ይህንን መመሪያ ማውጣቱን ተማሪዎቹ አክለው ገልጸዋል፡፡
እኔም ልመለስ!
እኔም ልመለስ ድንግል እናቴ
ከስደት ሕይወት ከባርነቴ
በልጅሽ ጉንጮች በወረደ ዕንባ
ባዘነው ልብሽ በተላበሰው የኀዘን ካባ
በእናት አንጀትሽ እንስፍስፍ ብሎ ያኔ በባባ
ልመለስ ድንግል ሆይ እኔም ከስደት
እውነትን ልያዝ ልራቅ ከሐሰት፡፡
ጥላቻ ገዝቶኝ ወንድሜን ከጠላው
እምነት ምግባሬን ሰይጣን ዘረፈው
መልሽኝ ድንግል ይብቃኝ ግዞቱ
በምግባር እጦት በቁም መሞቱ!
ወርኃ ኅዳር
ሦስተኛው ወር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ መሠረት “ኅዳር” ተብሎ ይታወቃል፡፡ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ በመዝገበ ቃላት መጽሐፋቸው ውስጥ የዚህን ወር ቃል ሲተረጉሙ “ማኅደር” ከሚለው ሥርወ ቃል የወጣ እንደሆነና “ማደሪያ” የሚል ፍቺ እንደሚሰጥ ገልጸዋል፡፡
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት አላችሁልን? ትምህርት እንዴት ነው? በርትታችሁ እየተማራችሁ ነውን? ጥናቱንም ከወዲሁ ጀምሩ! አዲሱን ዓመት ከተቀበልን ሁለት ወራትን አስቆጥረናል፤ ታዲያ በእነዚህ ጊዜያት በዘመናዊ ትምህርታችን ከነበረን ዕውቀት ምን ያህል አዲስ የማናውቀውን ነገር ዐወቅን? አንዳንድ ትምህርት ቤት የሙከራ ፈተና ጀምረዋል፤ ታዲያ እንዴት ነበር የመመዘኛው ፈተና? ጥሩ ውጤት እንዳስመዘገባችሁ ተስፋችን ነው! መልካም!
ባለፈው ትምህርታችን ስለ አማላጅነት በመጠኑ ተምረናል፤ ለዛሬ ደግሞ ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት እንማራለን፤ ተከታተሉን!
ከውድቀት አነሣን!
ለሰሚው በሚከብድ ቃላት በማይገልጸው
በመከራ ውሎ አዳምን አዳነው!
ዲያብሎስ ታሠረ አዳም ነጻ ወጥቶ
ልጅ ተባለ ዳግም በደሉ ተረስቶ
የማይሞተው አምላክ ስለ እኛ ሲል ሞቶ
ከውድቀት አነሣን ልጅነትን ሰጥቶ!