‹‹በገሊላ አውራጃ በቃና መንደር ሠርግ ሆነ፤ ውኃውንም ወደ ወይንነት ለወጠው›› (ዮሐ. ፪፥፩-፲፩)

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም እና ከቅዱሳን ሐዋርያቱ ጋር በመሆን በገሊላ አውራጃ በቃና መንደር በሠርግ ቤት ተገኝቶ ቤተ ከብካቡን በትምህርቱ በተአምራቱ ባረከ።በጥምቀት በዓል ማግስት ጥር ፲፪ ቀን ይህንኑ ጠብቀን በዓሉን እናከብራለን፡፡

ጥምቀት

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዮርዳኖስን ብርህት ማኅፀን እንድትሆን፣ ምእመናንም ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ፣ ከማኅፀነ ዮርዳኖስ ዳግም ተወልደው መንግሥተ ሰማያት እንዲገቡ  እንደዚሁም ሥርዓተ ጥምቀትን ለማስተማርና አብነት ለመሆን በጥር ዐሥራ አንድ ቀን ተጠምቋልና ይህችን የተከበረች ቀን ሕዝበ ክርስቲያን ያከብር ዘንድ ይገባል፡፡

በዓለ ጥምቀት

የተከበራችሁ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት አላችሁ? እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ! ልጆች! የጌታችንን የልደት በዓልን እንዴት አሳለፋችሁ? በሰላም እንዳሳለፋችሁ ተስፋችን ነው፤ ትምህርትስ እንዴት ነው? የግማሽ መንፈቀ ዓመት ፈተናም እየደረሰ ነውና በርትታችሁ አጥኑ!

ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! ዛሬ ደግሞ ስለ ጥምቀት በዓል እንማማራለን፡፡ ጥምቀት ማለት ‹‹አጥመቀ- አጠመቀ›› ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን ‹‹መነከር፣ መድፈቅ፣ በተባረከው ውኃ ጸበል ውስጥ ሦስት ጊዜ ብቅ ጥልቅ›› ማለት ነው፤ እንግዲህ በዛሬ ትምህርታችን ስለ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀት እንመለከታለን፡፡

አጋእዝተ ዓለም ሥላሴ

አጋእዝተ ዓለም ሥላሴ በኃጢአት የተገነባውን የሰናዖር ግንብ ያፈረሱበት አንድነታቸውንና ሦስትነታቸውን በግልጽ ያሳዩበት ጥር ሰባት ቀን የከበረ በዓል እንደመሆኑ በቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ይከበራል፡፡ታሪኩ በኦሪት ዘፍጥረት ላይ እንደተጻፈ እንዲህ ይነበባል፡፡…

ግዝረቱ ለእግዚእነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ቤተ ግዝረት በመግባት የኦሪት ሕግ የሆነውን ግዝረት የፈጸመበት ዕለት ጥር ስድስት ቀን በቤተ ክርስቲያናችን ይከበራል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ጌታ ክርስቶስ በሥጋ ግዝረትን ተቀበለ፣ ለአባቶች የተሰጠውን ቃልኪዳን ይፈጽም ዘንድ›› ብሎ መስክሯል፡፡ (ሮሜ ፲፭፥፰)

በእንተ ልደቱ ለአቡነ ተክለ ሃይማኖት

የዳሞት አውራጃ ገዚ ሞተለሚ በነበረበት ቡልጋ ደብረ ጽላልሽ በኢቲሳ መንደር ካህኑ ጸጋዘአብና እግዚኀረያ በትዳር ተወስነው ይኖሩ ነበር። ጸጋ ዘአብ በክህነቱ እግዚኀረያ በደግነቷና በምጽዋት ጸንተው በመኖራቸው በሕጉና በሥርዓቱ ለሚኖሩት ቀናዒ በመሆኑ እግዚአብሔር አምላክ ጎበኛቸው። ሃይማኖታቸውን የሚረከብ፣ እንዳባቱ ጸጋዘአብ የሚባርክ የአብራካቸውን ክፋይ ሊሰጣቸው ወደደ።

ብሥራተ ገብርኤል

ብሥራታዊው መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተገልጦ ስለ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእርሷ መወለድ ያበሠራት ዕለት ታኅሣሥ ፳፪ ‹‹ብሥራተ ገብርኤል›› ታላቅ በዓል ነው፡፡

‹‹እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ›› (ሉቃ.፩፥፲፱)

የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል የስሙ ትርጓሜ ‹‹እግዚእ ወገብር፤ አምላክ ሰው ሆነ ሰው አምላክ ሆነ›› ማለት ነው፤ ‹‹ሰላም ለዝክረ ስምከ ዘኢይተረጐም ምሥጢር ባሕቱ ይመስል ብሂለ እግዚእ ወገብር፤ ገብርኤል ሆይ ተመራምሮ ለማይደረስበት ስም አጠራርህ ሰላም እላለሁ፤ ነገር ግን አምላክ ሰው ሆነ ሰው አምላክ ሆነ ማለት ይመስላል›› እንዲል፡፡ (መልክዐ ቅዱስ ገብርኤል)

ዕረፍቱ ለአባ ሳሙኤል ዘዋልድባ

የከበረ ገድለኛ አባት የዋልድባው አባ ሳሙኤል የአባቱ ስም እስጢፋኖስ የእናቱ ስም ደግሞ ዓመተ ማርያም ነው። እነርሱም በዘመድ የከበሩ ደጋግ ናቸው፤ እነርሱም በአክሱም ሀገር ሲኖሩ ሁለት ልጆችን ወለዱ። አንደኛው ስሙ ገብረ ክርስቶስ ሲሆን ይህ ሁለተኛው ደግሞ የእግዚአብሔር ሰው አባ ሳሙኤል ነው።

ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ

ቅድስት አርሴማ ከሃያ ሰባቱ ደናግል ጋራ ሰማዕትነት ከተቀበለች በኋላ የቅዱሳን ሰማዕታቱን ዕፅም ፍልሠታቸው በዚህ በቅዱስ ጎርጎርዮስ እንዲደረግ ሆነ፤ ይህም ታኅሣሥ ስድስት ቀን ነው፡፡ እንዲሁ ደግሞ የእርሷ ማኅበርተኞች የሚባሉ የመቶ ዐሥራ ዘጠኝ ሰማዕታት ዝክራቸው ነው። ከዚያም በስሟ ያማረ ቤተ ክርስቲያን ሠርተው እንዲሁ አከበሩበት።