የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ቀኖና በማስጠበቅ ሥርዓቷን ለትውልድ እናስተላልፍ !(መልእክት ዘማኅበረ ቅዱሳን )
የነሐሴ ወር ሐመር #መጽሔት #በውስጧ ምን ይዛለች ?
የነሐሴ ወር ፳፻፲፰ ዓ.ም መልእክት ዘማኅበረ ቅዱሳን “#የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ቀኖና በማስጠበቅ ሥርዓቷን ለትውልድ እናስተላልፍ ! . ›› በሚል ርእስ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለደነገገችው ሥርዓቶች ሁሉ ተገዥ በመሆን መጽናት እንደሚገባ ታስነብባለች።
#ዐውደ ስብከት ሥር” በመጣህበት መንገድ በዚያ አትመለስ ” በሚል ዐቢይ ርእስ ትምህርት ይዛለች፡፡
#በትምህርተ ሃይማኖት ዐምድ ሥር” ሱባኤ” በሚል ርእስ ሱባኤ ለምን እንደምንገባ? መቼ ሱባኤ መግባት እንደአለብን ፤ሱባኤ የምንገባው እንዴት ነው?የሚል ጹሑፍ በትምህርተ ሃይማኖት ይዛለች።
#ዐቢይ ጉዳይ ዐምድ ሥር ደግሞ “#የቤተ ክርስቲያንን የስብከተ ወንጌል ስምሪት በዘመናዊ አሠራር መቃኘት ” በሚል ርእስ ስብከተ ወንጌል ስምሪት ላይ የሚታዩ ዐቢይ ችግሮችና ውስንነቶችን ከመፍትሔ ጋር ይዛለች ።
“#ክርስትና በማኀበራዊ ኑሮ፦ ” #ያለኝን እሰጥሃለሁ “በሚል መነሻነት ችግሩን መረዳት ፤ያለንን ማወቅ ና በሌለን ነገር መጨነቅ እንደማይገባን ልንፈታው በማንችለው ችግር መጨነቅ እንደሌለብን በሰፊው ያሳያል ።
• #በእናስተዋውቃችሁ ዐምድ ሥር “#የደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል ካቴድራል ታሪክ “ክፍል ፩ ስለ አመሠራረቱና ሌሎችም ጉዳዩች ላይ ሰፊ ትምህርት ይሰጣል ።
• #በነገዋ ቤተ ክርስቲያን “ከአንድ ምእተ ዓመት አርምሞ እሰከ ዘመናዊ የልህቀት ማእከልነት” የደብረታቦር መድኃኔዓለም የ4ቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ምስክር ጉባኤ ቤት ሁለንተናዊ አገልግሎትና ስኬቶች ፣የልማት ርእይና የወደፊት ዕቅዶች ታስነብባለች።
#በኪነ ጥበብ ዐምድ #በርናባስ “በሚል ርእስ ታስነብባለች ።
• #የጥያቄዎቻችሁ መልስ ዐምድ “#ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ” በሚል ርእስ በሰዋሰወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የሐዲስ ኪዳን ትርጓሜ መምህር ከሆኑት ከመዝገበ ጥበብ ልሳነ ወርቅ ዋሴ ጋር የተደረጉ ጥያቄና መልስ ይዛለች ።
ሐመር መጽሔት #፴፫ ኛ ዓመት ቁጥር ፰ በማሰራጨት ፡በማንበብና በማስነበብ የድርሻችን እንወጣ !
Magazine @eotcmk.org #ሐመር #መጽሔት ዝግጅት ክፍል
