የግእዝ መግባቢያ ዓረፍተ ነገሮች
የተወደዳችሁ አንባብያን! እንደምን ሰነበታችሁ? የእግዚአብሔር አምላካችን ስም የተመሰገነ ይሁን! እንኳን ለዘመነ ሉቃስ አደረሳችሁ! እግዚአብሔር አምላክ አዲሱን ዓመት የሰላምና የደስታ እንዲያደርግላችሁ ከወዲሁ እንመኝላችኋለን!
አዲሱ ዓመት ቤተሰቦቻችንን፣ ዘመዶቻችንን፣ ጓደኞቻችንን እንዲሁም ጎረቤቶቻችንን የምንጠይቅበትና እንኳን አደረሳችሁ የምንልበት ጊዜ ነውና ከሰዎች ጋር ንግግር የምናደርግባቸው የመግባቢያ ዓረፍተ ነገሮች በግእዝ ምን እንደሆኑ ታውቁ ዘንድ እንደ ዐውደ ዓመት ስጦታ እነሆ ብለናችኋል!
