ልሂድ አደን!

በመዝሙርና ኪነ ጥበባት ክፍል

ጥቅምት ፱ ቀን ፳፻፲፭ ዓመተ ምሕረት

ልቤ ተነሣስቶ ጽድቅህን ፍለጋ

ከማዳንህ ጋራ አንተኑ ሊጠጋ

ልሂድ ወደ ዱሩ ከአባቶች ማደሪያ

ከለምለሙ መስክህ ከጽድቅ መነኻርያ

ዓለምን ‘ሚረግጡት ሰማዩን ሚመኙት

ራሳቸውን ጥለው ….አንተን ካስበለጡት

ስለስምህ ብለው ………ከዋሻ ከገቡት

ቀንና ሌት ተግተው  ወንጌሉን ከኖሩት

የምድሩን ንቀው ቃልህ ጣፍጧቸው

የማዳንህን ሥራ ማንም ላይቀማቸው

እንትፍ ዓለሚቱ ከነመራራሽ ጥፊ

ከጎምዛዛው ……ዓለማቸው ሰፊ

ከየት ይገኛል ለአንተ ልቡን የከፈተ

በደል ምኞትን በውስጡ ያልከተተ

በወንጭፍ አይቀልቡት በጦሩ አይወጉት

ጅማሬው ይጥላል ልቡናን ካልረቱት

አደን ልሂድ ልውጣ ልጀግን ’ደነሱ

እኔም እዛ ልሂድ ጀግኖች እንደደረሱ

ልጨክን ላምርረው ጦሬን ልታጠቀው

ሥጋዬን አሸንፌ ዓለሙን ልካደው!