Entries by Mahibere Kidusan

«ስለ ሰላም ጸልዩ» (ሥርዓተ ቅዳሴ)

ሰዎች በሕይወታችን ውስጥ እጅጉን ከሚያስፈልገን ነገር ዋነኛው ሰላም ነው፡፡ ያለ ሰላም መኖር አይቻልንም፡፡ ሰላም የተረበሹትን ያረጋጋል፤ ያዘኑትን ያጽናናል፤ ጦርነትን ወደ ዕርቅ ይለውጣል፡፡

በዓለ ደብረ ቁስቋም

ከሦስት የስደት እና መከራ ዓመታት በኋላ የአምላክ እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልጇ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ይዛ አረጋዊ ዮሴፍንና ሰሎሜን አስከትላ ወደ ግብፅ ስትሰደድ በስተደቡብ የምትገኘው ደብረ ቊስቋም ላይ ያረፉበችበት ኅዳር ፮ ቀን ይከበራል፡፡

የሕይወት ኅብስት

እግዚአብሔር አምላክ ሰውን ከአራቱ ባሕርያተ ሥጋ ከአምስተኛ ባሕርያተ ነፍስ ፈጥሮ በመንፈስ ቅዱስ አክብሮ ሲያኖረው ለሥጋውም ለነፍሱም ምግብ እንዲያስፈልገው አድርጎ ነው፡፡ ለሥጋውም የሚያስፈልገውም ምግብ ልዩ እንደሆነ ሁሉ የሥጋውንና የነፍሱን ባሕርያት የተለያየ ነው፤ ነፍስም እንደ ሥጋ ባሕርያት (ነፋስ፣ እሳት፣ ውኃና መሬት) ባሕርይዋም ሆነ ምግቧም እንደዚያው ይለያል፡፡ የነፍስ ተፈጥሮዋ ረቂቅ ነው፤ በዚህም ለባዊነት፣ ነባቢነትና ሕያውነትም ባሕርይዋ መሆናቸውን ማወቅና መረዳትም ያስፈልጋል፤ ምግቧም የሕይወት ኅብስት ነው፡፡

ርእዮ ለይብኪ ዐይነ ልብ ዘቦ (ሰቈቃወ ድንግል)

አባ ጽጌ ድንግል ይህን ቃል የተናገረው የቅድስት ድንግል ማርያምን ስደቷን፣ በስደቷ ጊዜም የደረሰባትን መከራና ኃዘን አምልቶ በገለጸበትና አምላክን በኅቱም ድንግልና ፀንሳ በኅቱም ድንግልና የወለደች ድንግል ማርያምን ባመሰገነበት ክፍሉ ነው። ሙሉ ቃሉን እንደሚከተለው እንመልከተው።…

ምኞት

ሰው አንድን ነገር የራስ ለማድረግ በብርቱ ፍላጎት ወይንም ምኞት ይነሣሣል፤ በመልካም ምኞቱ የነፍስ ፍላጎትን ሲፈጽም የሥጋዊው ግን ወደ ጥፋት ይመራዋል፡፡ ሥጋዊ ምኞት በመጀመሪያ ጊዜያዊ ደስታን ቢሰጥም ፍጻሜው ግን መራራ ኅዘንን የሚያስከትል ነው፡፡ ጠቢቡ ሰሎሞንም ይህን በምሳሌው እንዲህ ሲል ገልጾታል፤ ‹‹የጻድቃን ምኞት መልካም ነው፤ የኃጥአን ተስፋ ግን መቅሠፍት ነው›› (ምሳሌ. ፲፩፥፳፫)

‹‹እመን እንጂ አትፍራ›› (ማር. ፭፥፴፮)

የደኅነታችን መሠረት እምነት በክርስቲያናዊ ሕይወታችን ውስጥ ችግርና መከራ በበዛብን ጊዜ ጸንተን እንድናለፍ ይረዳናል፡፡ የሰው ዘር በኃጢአቱ የተነሣ በምድር እንዲኖር ከተፈረደበት ጊዜ አንስቶ በተለያዩ ችግርና መከራ ተይዞ ሲሠቃይ ፈጣሪውን ያስባል፤ ይማጸናልም፡፡ አንዳንድ ጊዜ ፈውስን ሲያገኝ በሌላ ጊዜ ግን ወደማይመለስበት ዓለም በሞት ይለያል፤ ሆኖም ድኅነተ ሥጋንም ሆነ ድኅነተ ነፍስን ከአምላካችን እናገኝ ዘንድ እምነት ያስፈልጋል፡፡

‹‹የሞተ ሰውስ ዐረፈ፤ ነገር ግን መታሰቢያውን አድርግለት›› (ሲራክ ፴፰፥፳፫)

ሰዎች ሕያው ሆነን በፈጣሪ አምሳል እንደተፈጠርነው ሁሉ በኃጢአት ሳቢያ የተፈረደበትንን ሥጋዊ ሞት እንሞት ዘንድ አይቀሬ ነው፤ ‹‹አፈር ነህና ወደ አፈር ትመለሳለህና›› እንደተባለውም የሰው ዘር በሙሉ ወደ አፈርነት ይመለሳል፡፡ በሕፃንነትም ይሁን በጎልማሳነት እንዲሁም በእርጅና ሰዎች ይሞታሉ፡፡ በበሽታ፣ በአደጋ ወይንም በግድያ የሰዎች ሕይወት በየጊዜው ይቀጠፋል፡፡ በተለይም በዚህ ትውልድ ዓለማችን በየጊዜው በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን አያጣች ነው፡፡ በእርስ በርስ ግጭትና ጦርነት እንዲሁም የሰዎችን ሕይወት እንደ ቅጠል እያረገፈ ባለው ኮሮና በሽታ እጅግ ብዙ ሰዎች ሞተዋል፡፡