ቅዱስ ፓትርያርኩ ጾመ ፍልሰታ ለማርያምን ምክንያት አድርገው መልእክት አስተላለፉ።
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፣ አሜን በሀገር ውስጥና በመላው ዓለም የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች በሙሉ! የሰውን ወገን ለማዳን የልጁ ማደሪያ ትሆን ዘንድ ድንግል ማርያምን የመረጠ መፍቀሬ ሰብእ እግዚአብሔር አምላካችን እንኳን ለሁለት ሺህ ዓሥራ ስምንት ዓመተ ምሕረት ጾመ ማርያም አደረሰን አደረሳችሁ! “ወእመሰ ታፈቅሩኒ ዕቀቡ ትእዛዝየ፡- ከወደዳችሁኝስ ትእዛዜን ጠብቁ” (ዮሐ.14፥15)፤ ፍቅር […]
