ሥረይ ግሦች
የተወደዳችሁ አንባብያን! እንደምን ሰነበታችሁ? የእግዚአብሔር አምላካችን ስም የተመሰገነ ይሁን! የጥቅምት ወር የመጨረሻ ክፍለ ጊዜያችን የሆነውን ትምህርት ለዛሬ ይዘንላችሁ ቀርበናል፡፡ ከዚያ በፊት ግን የባለፈው ትምህርታችን ላይ ስላስተማርናችሁ ‹‹ረብሐ ግሥ›› ጥቂት እናስታውሳችሁ፡፡
ከግሥ ዓይነቶች አንዱ የሆነው ረብሐ ግሥ ዘማች ግሦችን ከቀዳማይ አንቀጽ ጀምሮ እስከ አርእስት እና ከዚያ በላይ ያሉትን ቅጽሎችን የሚያገሰግስ ማለት እንደሆነ ተመልክተናል፡፡ በዚህ የግሥ ዓይነት ሥር የሚገኙት የዋህና መሠሪ ግሦች መሆናቸውንና እነርሱንም በግሥ አርእስት ማለትም በቀተለ፣ በቀደሰ፣ በተንበለ፣ በባረከ፣ በማህረከ፣ በሴሰየ፣ በክህለ እና በጦመረ ዘርዝረን ለማየት ሞክረናል፡፡ የዚህንም ግሥ ዝርዝር ርባታ እንዳጠናችሁት ተስፋ እያደረግን ወዳዘጋጀንላችሁ ትምህርት እናልፋለን፡፡ ከዚህ ቀጥሎ የምንመለከተው የግሥ ዓይነት ‹‹ሥረይ ግሥ›› ይባላል፡፡
