‹‹ከዚህም በረት ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ፤ እነርሱን ደግሞ ላመጣ ይገባኛል፤ ድምጼንም ይሰማሉ፥ አንድ መንጋም ይሆናሉ እረኛውም አንድ ነው›› (ዮሐ. ፲፥ ፲፮)
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአንቀጸ አባግዕ ሲያስተምር ‹‹ከዚህም በረት ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ፤ እነርሱን ደግሞ ላመጣ ይገባኛል፤ ድምጼንም ይሰማሉ፥ አንድ መንጋም ይሆናሉ እረኛውም አንድ ነው›› ብሏል።(ዮሐ. ፲፥ ፲፮)
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአንቀጸ አባግዕ ሲያስተምር ‹‹ከዚህም በረት ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ፤ እነርሱን ደግሞ ላመጣ ይገባኛል፤ ድምጼንም ይሰማሉ፥ አንድ መንጋም ይሆናሉ እረኛውም አንድ ነው›› ብሏል።(ዮሐ. ፲፥ ፲፮)
በቅዱስ ዮሐንስ እጅ በማየ ዮርዳኖስ ተጠምቆ የባሕርይ ልጅነቱንና አምላክነቱን ከአብ እና ከመንፈሰ ቅዱስ አስመሰከረ፡፡
አስተርእዮ መታየት ወይም መገለጥ የሚል ትርጓሜ ያለው የግእዝ ቃል ነው፡፡ በግሪክ ‹‹ኤጲፋኒ›› የሚል ስያሜ አለው፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትም ይህን ቃል በመጠቀም ኤጲፋኒያ እያሉ በዜማ መጻሕፍቶቻቸው ይጠሩታል፡፡
ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው ‹‹የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ÷ በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ፡፡ እኔም እልሃለሁ÷ አንተ ጴጥሮስ ነህ፤ በዚያች ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ÷ የገሃነም ደጆችም አይችሏትም፡፡››(ማቴ.፲፮፥፲፫—፳)
ለአምስት ሺሕ አምስት መቶ ዘመን በዓለም ላይ ሠልጥኖ የነበረውን ጨለማ ያስወግድ ዘንድ እግዚአብሔር አምላክ ሰው ሆነ፡፡ ከቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደው አማናዊው ብርሃን ፀሐየ ጽድቅ ክርስቶስ በሥጋ ተገለጠ፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም በውዳሴው እንዳለው ‹‹ብርሃን ዘበአማን ዘያበርህ ለኵሉ ሰብእ ለእለ ይነብሩ ውስተ ዓለም፤ በጨለማ ውስጥ ለሚኖር ሕዝብ ታላቅ ብርሃን ወጣላቸው›› (ኢሳ. ፱፥፪)፡፡
አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከሚታወሱባቸው በዓላት መካከል ታኅሣሥ ፳፬ ቀን የሚከብረው በዓለ ልደታቸው አንደኛው ነው፡፡ መጽሐፈ ስንክሳር ዜና ልደታቸውን ሲናገር ‹‹ሐዲስ ሐዋርያ›› በማለት በክብር ጠርቷቸዋል፡፡
በየዘመኑ የተነሡ ነቢያትም ምንም እንኳን አምላክ ይህን ዓለም እንዴት እንደሚያድነው በግልጽ ባይረዱትም እግዚአብሔር ዓለሙን የሚያድንበትን ቀን እንዲያቀርበው እንዲህ እያሉ ይማፀኑ ነበር፤ ‹‹አቤቱ ሰማዮችን ዝቅ ዝቅ አድርጋቸው፤ ውረድም፤ ተራሮችን ዳስሳቸው ይጢሱም፡፡ መብረቆችህን ብልጭ አድርጋቸው፤ በትናቸውም፤ ፍላጾችን ላካቸው፤ አስደንግጣቸውም፡፡ እጅህን ከአርያም ላክ፤ አድነኝም›› (መዝ. ፻፵፫፥፭-፯)፡፡
ይህች ዓለም ከእውነት የራቀች መኖሪያዋን በሐሰት መንደር ያደረገች መሆኗ ይታወቃል፡፡ ሰው ማንነቱን አጥቶ በበደል ምክንያት በሐሰት ኖሯል፡፡ ሰው በፈቃዱ ጥፋት ምክንያት ከሚፈጽማቸው በደሎች ትልቁ በደል ውሸት ነው፡፡ ውሸት ተሸንፎ ይወድቃል፤ ከሕይወት ይርቃል፡፡ የኀጣአን ሁሉ ራስ ሐሰት ናት፡፡ ክፋትን ከራሱ አንቅቶ የበደለ ዲያብሎስ አቡሃ ለሐሰት፤ የሐሰት አባት የተባለው ለዚህ ነው (ዮሐ.፰፥፵፬)፡፡
ታቦተ ጽዮን በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ትመሰላለች፤ ይህን ለመረዳት ስለ ታቦተ ጽዮን አሠራርና መንፈሳዊ ትርጉም አስቀድመን ልናውቅ ይገባናል፡፡
ጾመ ነቢያት ምንም እንኳን ዓላማው አንድ ቢሆንም የተለያዩ ስያሜዎች አሉት፡፡ በዋነኝነት ነቢያት ስለጌታ ሰው መሆንና ስለ ሰው መዳን የጸለዩትን ጸሎት የጾሙትን ጾም በማሰብ፤ የአምላክ ሰው መሆንን ምሥጢር በትንቢት ተመልክተው ለእኛ ለሰው ልጆች የሚከፍለውን የፍቅር ዋጋ አስበው ጾመውታልና ጾመ ነቢያት ይባላል፡
