ወደ ቤቴል ውጣ በዚያም ኑር ዘፍ.35፥1
የካቲት 27 ቀን 2005 ዓ.ም.
ዲ/ን ሰለሞን መኩሪያ
ይህንን የተናገረ አምላካችን እግዚአብሔር ነው፡፡ ይህ የተነገረው እስራኤል ለተባለ ያዕቆብ ነው፡፡Â በቅዱስ መጽሐፍ ታሪኩ ተጽፎ እንደምናገኘው ከወንድሙ ከዔሳው ሸሽቶ የአባቱን የይስሐቅን በረከት ተቀብሎ ወደ አጎቱ ወደ ላባ ሲሄድ ሎዛ ከምትባለው ምድር ሲደርስ ጊዜው መሸ፡፡ እርሱም ደክሞት ስለነበር ድንጋይ ተንተርሶ ተኝቶ ሳለ ሌሊት በራእይ እግዚአብሔር ተገለጠለት ራእዩም የወርቅ መሰላል ከምድር እስከ ሰማይ ተተክሎ በመሰላሉ መላእክት ሲወጡ ሲወርዱ ነበር፡፡ እግዚአብሔርም በዙፋኑ ተቀምጦ ነበር፡፡
Â
ያዕቆብንም âእኔ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅ አምላክ እግዚአብሔር ነኝ፤ አትፍራ፣ ይህችን አንተ የተኛህባትን ምድር ለአንተም ለዘርህም እሰጣለሁ ዘርህም እንደ ባሕር አሸዋ ይሆናል፡፡ በአንተ በዘርህ አሕዛብ ይባረካሉ፡፡ እነሆም እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፡፡ የነገርኩህን ሁሉ እስካደርግልህ ድረስ አልተውህምâ አለው፡፡ ያዕቆብም ከእንቅልፍ ተነሥቶ በእውነት እግዚአብሔር በዚህ ስፍራ አለ፤ እኔ አላወቅሁም ነበር፡፡
Â
ይህ ሥፍራ እንዴት ያስፈራል? ይህ ስፍራ የእግዚአብሔር ቤት ነው እንጂ ሌላ አይደለም፤ ይህችም የሰማይ ደጅ ናት፡፡ ያዕቆብም ማልዶ ተነሣ ተንተርሷት የነበረችውንም ድንጋይ ወስዶ ሐውልት አድርጎ አቆማት፤ በላይዋም ዘይት አፈሰሰባት፡፡ ያዕቆብም ያን ሥፍራ ቤቴል ብሎ ጠራው አስቀድሞ ግን የዚያ ከተማ ስም ሎዛ ነበር፡፡ ያዕቆብም ስዕለትን ተሳለ፡፡ እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ቢሆን በምሄድበት መንገድ ቢጠብቀኝ፣ የምበላውን እንጀራ የምለብሰውን ልብስ ቢሰጠኝ ወደ አባቴ አገር በሰላም ቢመልሰኝ እግዚአብሔር አምላኬ ይሆንልኛል፡፡ ለሐውልት ያቆምኳት ይህች ድንጋይ የእግዚአብሔር ቤት ትሆንልኛለች፤ ከሰጠኸኝ ሁሉ ለአንተ ከአስር እጅ አንዱን እሰጥሃለሁ አለ፡፡ እግዚአብሔርም ስእለቱን ሰምቶ ሁሉንም ፈጸመለት ወደ አጎቱ ወደ ላባ ደርሶ ሚስት አግብቶ ብዙ ልጆችን ወልዶ እንዲሁም ብዙ ባሮችን እና ሀብት ንብረት አፍርቶ ወደ አባቱ ሀገር ሲመለስ እግዚአብሔር አምላክ ተገለጠለትና âወደ ቤቴል ውጣ በዚያም ኑርâ ብሎ አዘዘው ዘፍ.28፥10-20፣ ዘፍ.35፥1፡፡
x
Â
ለመሆኑ ይህች ቤቴል ማን ናት? እግዚአብሔር አምላክ ለጊዜው ያዕቆብና ቤተሰቡ እንዲኖሩባት ለፍጻሜው ሁላችንም እንድንኖርባት የታዘዝንባት ቤቴል ምስጢራዊ ትርጉሟ ምን ይመስላል? አባቶቻችን እንዲህ ይተረጉሙታል፡፡
Â
1.   ቤቴል የተባለች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት፡፡
አባታችን ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ ባየው ራእይ እግዚአብሔር አምላክ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ክብር ገልጾለታል፡፡ ይኸውም የወርቅ መሰላል ከምድር እስከ ሰማይ ድረስ ተተክሎ በመሰላሉ መላእክት ከላይ ወደ ታች ሲወርዱ እና ሲወጡ ተመልክቷል፡፡ በመሰላል የላዩ ወደ ታች እንዲወርድ አምላክ ሰው ለመሆኑ የታቹ ወደ ላይ እንዲወጣ ሰው አምላክ ለመሆኑ ምክንያት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት፡፡ መሰላሉ ደግሞ ወርቅ ነበር፡፡
Â
ወርቅ ፅሩይ ነው፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም በማሰብ፣ በመናገር፣ በመተግበር፣ በመዳሰስ፣ በማሽተት ወ.ዘ.ተ. ሰው ሁሉ ኀጢአት በሚሠራበት ህዋስ ሁሉ ያልተዳደፈች፣ ንጽሕት፣ መልዕልተ ፍጡራን /ከፍጡራን በላይ/ መትሕተ ፈጣሪ /ከፈጣሪ በታች/ ናት፡፡ ከነገደ መላእክት ከደቂቀ አዳም በክብር የሚመስላት በጸጋ የሚተካከላት የለም፡፡ ይህንንም ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም በውዳሴ ማርያም ዘረቡዕ ሲገልጽ âየዐቢ ክብራ ለማርያም እምኩሎሙ ቅዱሳንâ âየማርያም ክብር ከቅዱሳን ክብር ይበልጣልâ ብሏል፡፡
Â
በወርቁ መሰላል መላእክት ሲወጡ ሲወርዱ መታየታቸው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ምዕራገ ጸሎት እንደሆነች በእመቤታችን ምልጃ የሰው ሁሉ ጸሎት ወደ እግዚአብሔር እንደሚቀርብ የእግዚአብሔርም ቸርነት ለሰዎች እንደሚሰጥ ያመለክታል፡፡ ሊቁ አባ ጽጌ ድንግል በማኅሌተ ጽጌ ድርሰቱ âአልቦ ጸሎት ወአልቦ ትንባሌ እንበሌኪ ማርያም ዘየዓርግ ሎዓሌâ ብሎ አጉልቶታል በወርቁ መሰላል ጫፍ ዙፋን ነበር፡፡ በዙፋኑም ላይ እግዚአብሔር ተቀምጦ ለያዕቆብ ተገልጦለታል፡፡ ባርኮታል፤ ዙፋን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል የማኅፀኗ ምሳሌ ነው፡፡ በማኅፀኗም ፍጥረቱን ለማዳን እግዚአብሔር ሰው እንደሆነ ማለትም በማኅፀነ ድንግል መፀነሱን ያመለክታል፡፡ ከዚያም በአጭር ቁመት በጠባብ ደርት በሰው መጠን መገለጹን ያስረዳል፡፡ ያዕቆብን እንደባረከው ርስት እንደሰጠው ሁሉ በእመቤታችን ሥጋ ተገልጦ በበደሉ ምክንያት የተረገመውን ሰው እንደባረከው አጥቶት የነበረውን ርስት ገነት መንግሥተ ሰማያትን እንደሰጠው ያመለክታል ዮሐ.14፥2፡፡ âበአባቴ ቤት ብዙ ማደሪያ አለ ቦታÂ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና፡፡ ዳግመኛም እመጣለሁ እናንተም እኔ ባለሁበት ትኖሩ ዘንድ ወደ እኔ እወስዳችኋለሁâ እንዲል፡፡ ፍጥረቱም ሁሉ ፈጣሪው እግዚአብሔር ተመለከተው፡፡
Â
ፍጥረት ማለትም መላእክትና ደቂቀ አዳም ፈጣሪያቸው እግዚአብሔርን ለመመልከት የቻሉት በእመቤታችን ሥጋ በመገለጡ ነው፡፡ ያዕቆብ ተንተርሶት የነበረው ድንጋይ እመቤታችን በትንቢተ ነቢያት ጸንታ መኖሯን ያመለክታል፡፡ እንግዲህ ይህችን ነቢያት በትንቢታቸው ደጅ ሲጠኗት የነበረችውን እግዚአብሔር የተገለጠባት የእግዚአብሔር ዙፋን ጸሎትን መሥዋዕትን ሁሉ የምታሳርግ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን አማላጅ መጠጊያ ልናደርግ ያስፈልጋል፡፡ ያዕቆብ በቤቴል እንዳደረ እኛም በአማላጅነቷ ከልጇ ዘንድ በተሰጣት የከበረ ቃል ኪዳን ልባችንን እንድናኖር ያስፈልጋል መዝ.47፥12፡፡ âበብርታቷ ላይ ልባችሁን አኑሩâ እንዲል፡፡ የእመቤታችን ምልጃ ለሁላችንም ይደረግልን፡፡
Â
2.   ቤቴል የተባለች ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡
አባታችን ያዕቆብ ባየው ራእይ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ክብር እግዚአብሔር ገልጦለታል፡፡ ያዕቆብ የጳጳሳት የቀሳውስት ምሳሌ ነው፡፡ ቦታው የቅድስት ቤተ ክርስቲያን፣ የተንተራሰውን ድንጋይ ዘይት አፍስሶበታል፡፡ ለጊዜው ቦታው እንዳይጠፋበት ለምልክት ለፍጻሜው ሊቃነ ጳጳሳት ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በቅብዐ ሜሮን እንደሚያከብሯት የመንፈስ ቅዱስ የጸጋው ግምጃ ቤት እንደሚያደርጓት ማሳየቱ ነው፡፡ ሐዋ.20፥28፡፡ የወርቁ መሰላል ምሳሌዋ የሆነ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ዘለዓለማዊ ድንግልና ክብር አማላጅነት የሚነገርባት እግዚአብሔር የታየባት ዙፋኑ የተዘረጋባት ይኸውም የታቦቱ ምሳሌ ነው፡፡ መላእክት የእግዚአብሔርን ቸርነት ወደ ሰው ልጆች የሚያመጡባት የሰው ልጆችን ጸሎት ወደ እግዚአብሔር የሚያሳርጉባት ዘወትርም በኪዳን በቅዳሴ በማኅሌት በሰዓታት የማይለያት የምሕረት አደባባይ አማናዊት ቤቴል ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡
Â
አምላካችን እግዚአብሔር ለቅዱስ ያዕቆብ âወደ ቤቴል ውጣ በዚያም ኑርâ ሲል አዞታል፡፡ ምክንያቱም ሕይወት የሚገኝባት በሥጋ በነፍስ የምንጠበቅባት ስለሆነ ነው፡፡ አባቶቻችን ቅዱሳን ሐዋርያት በደብረ ታቦር የጌታችንን ብርሃነ መለኮቱን በተመለከቱ ጊዜ ቅዱስ ጴጥሮስ âበዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነውâ ማቴ.17፥4 እንዳለ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን መኖር ለእኛ መልካም ነው፡፡ ቅዱስ ዳዊትም እግዚአብሔርን አንዲት ነገር ለመንኩት እርሷንም እሻለሁ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ â¦. ቤተ መቅደሱንም አገለግል ዘንድ እንዳለ መዝ.26፥4፡፡ ቅዱስ ዳዊት መንግሥቱ እንዲደላደልለት ዙፋኑ እንዲጸናለት ያይደለ በእግዚአብሔር ቤት መኖር እንዲገባ አጥብቆ እግዚአብሔርን የለመነበት ልመና ነው፡፡ ይህም የተወደደ ሆኖለታል፡፡ እንግዲህ በእግዚአብሔር ቤት በአማናዊት ቤቴል ለመኖር እንዴት ሆነው ተዘጋጅተው መውጣት /መሄድ/ እንደሚገባቸው ያዕቆብ ለቤተሰቡ አስገነዘባቸው እንዲህ አላቸው፡፡
Â
1.   እንግዶች አማልክትን ከእናንተ አስወግዱ አላቸው፡፡
አባታችን ያዕቆብ ለቤተሰቦቹና ከእርሱ ጋር ላሉት âከእናንተ ጋር ያሉ እንግዶችን አማልክት ከእናንተ አስወገዱâ አላቸው አምላካችን እግዚአብሔር በአምልኮቱ የሚገባበትን አይወድም በሊቀ ነቢያት በሙሴ አድሮ ሲናገር âከእኔ በቀር ሌሎች አማልክትን አታምልክâ ዘጸ.20፥3 ብሏል፡፡ ሰማይና ምድርን በውስጧ ያሉትን የሚታየውንና የማይታየውን ፈጥሮ በመግቦቱ በጠብቆቱ የሚያስተዳድር እግዚአብሔር ሆኖ ሳለ ከእግዚአብሔር ሌላ አምላክ አጥንት ጠርቦ ድንጋይ አለዝቦ፣ በጨሌ፣ በዛፍ፣ በተራራ፣ በጠንቋይ ወ.ዘ.ተ. ማምለክ አይገባም፡፡ እንዲህ በሚያደርጉ ሰዎች ላይ የእግዚአብሔር ቁጣው ትነዳለችና ዘጸ.20፥4፡፡ ዛሬም በዘመናችን ከወገብ በላይ ታቦት ከወገብ በታች ጣዖት ሆነው ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚመጡ ሰዎች አሉ፡፡ ጠዋት ቤተ ክርስቲያን መጥተው ኪዳን አድርሰው ቅዳሴ አስቀድሰው ለእግዚአብሔር የሚገባውን እጣኑን ጧፉን ዘቢቡን ሌላም ለቤተ ክርስቲያን የሚያስፈልገውን ሰጥተው ሰግደው አምልኮታቸውን ፈጽመው ደግሞ ሲመሽ ሰው አየኝ አላየኝ ብለው ጨለማን ተገን አድርገው ጫት፣ ሰንደል፣ ቡና፣ ቄጤማ ተሸክመው ወደ ቤተ ክርስቲያን በሄዱበት እግራቸው ወደ ጠንቋይ ቤት የሚሄዱ በዚያ የሚሰግዱ በቤታቸውም ጠንቋዩ ያዘዛቸውን ጨሌ የሚያስቀምጡ ቀን እና ወር ለይተው ጥቁር በግ ገብስማ ዶሮ ወ.ዘ.ተ.
Â
የሚያርዱ እህል የሚበትኑ እንደዚህ ባለ በሁለት እግር በሚያነክስ ልብ ወይም ሁለት እግር አለኝ ብሎ ሁለት ዛፍ ላይ ሊወጣ የሚመኝ ሰው ከእግዚአብሔር አንዳች ነገር አያገኝም፡፡ ስለዚህ ይህንን ሰይጣናዊ ልምድ አስወግዶ ማለትም ከዚህ የኀጢአት ሥራ ንስሐ ገብቶ ተለይቶ በፍጹም ልብ በፍጹም ነፍስ እግዚአበሔርን ብቻ በማምለክ ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መገስገስ ያስፈልጋል፡፡ የያዕቆብ ቤተሰቦች የአባታቸውን ምክር ሰምተው የጣዖት ምስል ተቀርፆባቸው የነበሩ በእግራቸውና በእጃቸው በጆሮአቸውም የነበሩትን አውልቀው ለያዕቆብ ሰጡት እርሱም እንዳያገኟቸው አድርጎ አርቆ ቀበራቸው፡፡ እስከ ዛሬም አጠፋቸው ዘፍ.35፥4 እንዲል፡፡ ያዕቆብ የቀሳውስት ምሳሌ ነው፡፡ ቤተሰቦቹ የምእመናን ምስሎቹን አምጥቶ ለያዕቆብ እንደመስጠት ኀጢአትን ለካህን መናዘዝ ከአምልኮ ጣዖት እንደመለየት ሲሆን ያዕቆብ ወስዶ እንደ ቀበራቸው በቀኖና ወደ እግዚአብሔር የመቅረብ ምሳሌ ነው፡፡ ከአምልኮ ጣዖት ተለይተን እግዚአብሔርን ብቻ እያመለክን በቤቱ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንድንኖር የቅዱሳን አምላክ ይርዳን፡፡
Â
2.   ንጹሐን ሁኑ ልብሳችሁን እጠቡ አላቸው፡፡
አባታችን ያዕቆብ ለቤተሰቡ እንግዶችን አማልክትን እንዲያስወግዱ ካዘዙ በኋላ እነርሱም ካስወገዱ በኋላ የሰጣቸው መመሪያ âንጹሐን ሁኑ ልብሳችሁን እጠቡâ አላቸው፡፡ ሰው ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲመጣ አፍአዊ /የውጭ/ ንጽሕናውን እንዲሁም ውስጣዊ /የልብ/ ንጽሕናውን መጠበቅ እንደሚገባው አስተማረ ዘሌ.11፥44 እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና ሰውነታችሁን ቀድሱ ንጹሐንም ሁኑ እኔ አምላካችሁ እግዚአብሔር ቅዱስ ነኝና፡፡â ይላል ስለዚህ ወደ ቅዱስ እግዚአብሔር ወደ ክብሩ ዙፋን ወደ ጸጋው ግምጃ ቤት ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከእግዚአብሔር ለመገናኘት ንጹሕ ልብስ ለብሰን ደግሞ በንስሐ ታጥበን ሕይወታችንን አድሰን ሊሆን ይገባል፡፡ ቅዱስ ዳዊትም በመዝ.50፥7 âበሂሶጵ እርጨኝ እነጻማለሁ እጠበኝ ከበረዶም ይልቅ ነጭ እሆናለሁ፡፡â እንዲል፡፡
Â
አንዳንድ ሰዎች ወደ ቤተ ክርስቲያን ለመሄድ የልብስ ንጽሕና መጠበቅ የሚገባ የማይመስላቸው ወደ አንድ ሰርግ ወይም ድግስ በሰው ፊት ለመታየት የሚያደርጉትን ጥንቃቄ እና የአለባበስ ሥርዓት ወደ ቤተ ክርስቲያን ግን ሲመጡ አልባሌ ሆነው መምጣት የሚገባ የሚመስላቸው አሉ አንዳንዶችም ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲመጣ ሰውነትን የሚያራቁት /የሚያስገመግም/ ልብስ ለብሰው የሚመጡ አሉ ይህ የሚገባ አይደለም፡፡ ምክንያቱም ለጸሎት የመጣውን ሰው አእምሮ የሚሰርቅና የሚያሰናክል እንዳይሆን መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ ምስጢሩ ግን አባታችን ያዕቆብ ለቤተሰቡ ንጹህ ሁኑ ልብሳችሁን እጠቡ ማለቱ በንስሐ ሕይወት ተዘጋጅታችሁ ወደ እግዚአብሔር ቤት ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በእግረ ልቡና ውጡ ለማለት ነው፡፡ ለዚህም የቅድስት ሥላሴ ቸርነት የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት የቅዱሳን መላእክት ፈጣን ተራዳኢነት የቅዱሳን ጸሎትና ምልጃ አይለየን ይርዳን አሜን፡፡


“የቤተ ክርስቲያንን ትምህርተ ሃይማኖትንና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን አከብራለሁ አስከብራለሁ” ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ያሬዳዊ ወረብ አቅርበዋል፡፡ በተጨማሪም በጠቅላይ ቤተ ክህነት አስተባበሪነት ከየቤተ ክርስቲያኑ የተውጣጡ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን የቆሜ አጫበር ወረብ፤ እንዲሁም የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የመዝሙር ክፍል አባላት ለበዓሉ ያዘጋጁትን ያሬዳዊ ወረብ አቅርበዋል፡፡
የግብፅ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን በመወከል በበዓለ ሢመቱ ላይ የተገኙት ብፁዕ አቡነ ጳኩሚስ “በአሁኑ ወቅት በዓለማችን ላይ በጣም ብዙ ችግሮችና ፈተናዎች ይታያሉ፡፡ በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የሚያጋጥሙን ፈተናዎችን ለመቋቋም እኛ የኦርየንታል ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናት የጌታችን የአምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስን ቃል ለመፈጸም በአንድነት ሆነን መጸለይና መሥራት ይጠበቅብናል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና የአሌክሳንድርያ ቤተ ክርስቲያን ከ4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ ያለንን የጠበቀ ግንኙነት አጠናክረን መቀጠል ይገባናል” ብለዋል፡፡
ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት ባለው መንፈሳዊ ሥልጣን ምርጫው እንዲፈጸም ባሳለፈው ውሳኔ የእግዚአብሔር ቅዱስ ፈቃድ ተጨምሮበት ምርጫው ተከናውኗል፡፡ እግዚአብሔር ሥራውን የሚሠራው በሰው ላይ አድሮ ነው፡፡ ሓላፊነቱና ሸክሙ ከባድ ቢሆንም እንደ ፈቃድህ ይሁን በማለት የእግዚአብሔርን ጥሪ በትሕትና ተቀብዬዋለሁ፡፡ መታዘዝ ከመሥዋዕት ይበልጣልና፡፡ አቅሜ የፈቀደውን ያህል ለቤተ ክርስቲያኔ እታዘዛለሁ፡፡ አልችልም ማለት እችል ነበር ነገር ግን የቤተ ክርስቲያንን ጥሪ አልቀበልም ማለት መሥዋዕትነትን መሸሽ ሆነ፡፡ ይህ መንፈሳዊ ሥልጣን የክርስቶስ መከራ መስቀልን ተሸክሞ ለመሥዋዕትነት መሰለፍ እንጂ ለክብርና ለልዕልና እንዳልሆነ ይገባኛል፡፡ ሁላችሁም እንደምትረዱኝም ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ እግዚአብሔር ይርዳኝ፡፡ ጸሎታችሁና ትብብራችሁ አይለየኝ፡፡ ይህንን ታላቅ ሓላፊነት ከእግዚአብሔር እርዳታ ጋር ከቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጭምር እንጂ የእኔ ብቻ ሊሆን ስለማይችል በጋራ እንወጣዋለን የሚል ጽኑ እምነት አለኝ” ብለዋል፡፡


ለመምረጥ በተደረገው ሂደት መሠረት 806 መራጮች ድምጽ የሰጡ ሲሆን ከሰዓት በኋላ በተደረገው ድምጽ ቆጠራ ብፁዕ አቡነ ማትያስ በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ሊቀ ጳጳስ በ500 ድምጽ በመመረጥ የመጀመሪያውን ድምጽ በማግኘት 6ኛው ፓትርያርክ ሆነዋል፡፡ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ 39 ድምጽ፤ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ 98 ድምጽ፤ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ 98 ድምጽ፤ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል 70 ድምጽ በማምጣት ምርጫው ተጠናቋል፡፡ አንደ ድምፅ በትክክል ባለመሞላቱ ውድቅ ሆኗል፡፡
ፓትርያርክ ሆነው የተመረጡት ብፁዕ አቡነ ማትያስ በመጨረሻ ባስተላለፉት መልእክት “ከእግዚአብሔርና ከሕዝበ ክርስቲያኑ የተሰጠኝን አደራ ለመወጣት ከብፁዓን አባቶች፣ ካህናትና ከምእመናን ጋር አብረን ስንለምንሠራ ሥራው የቀለለ ይሁናል ብዬ አምናለሁ” ብለዋል፡፡


ዛሬ ከስዓት በኋላ በቅዱስ ሲኖዶስ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፤ የአስመራጭ ኮሚቴ አባላት፣ እንዲሁም ከልዩ ልዩ የሚዲያ አካላት የተወከሉ ጋዜጠኞች በተገኙበት በተሰጠው መግለጫ ላይ፡-ብፁዕ አቡነ ማትያስ በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ገዳማት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የባሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ የምዕራብና ደቡብ አዲስ አበባ የከፋ ሸካ ቤንች ማጂ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የወላይታና ዳውሮ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ለፓትርያርክነት እጩ ሆነው መቅረባቸው ተገልጧል፡፡

ከ2003 ዓ.ም. ጀምሮ በደብረ ጽጌ ቅድስት ማርያም ገዳም፤ በፍቼ ቅዱስ ጴጥሮስ ቤተ ክርስቲያን፤ እንዲሁም በበኬ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር መካሄዱ የሚታወስ ሲሆን ምእመናን ከወዲሁ ትኬቱን በብር 120፡00 /አንድ መቶ ሃያ/ በመግዛት በጉዞው እንዲሳተፉ የማኅበሩ ምክትል ዋና ጸሐፊና የጉዞው አዘጋጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ግርማ ተሾመ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡