ደብረ ማርቆስ ማእከል 252 የግቢ ጉባኤ ተማሪዎችን አስመረቀ።
በማኅበረ ቅዱሳን የደብረ ማርቆስ ማእከል ግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ዋና ክፍል ለ4 ዓመታት
በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ እንድማጣ ገነተ ኢየሱስ ዋናው ግቢ 150 እና ጤና ካምፓስ የመቃ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን 102 በድምሩ 252 ተማሪዎችን ካህናት አባቶች፣ የማእከሉ የሥራ አስፈጻሚ አባላትና የተመራቂ ቤተሰቦች በተገኙበት ሰኔ 21 ቀን 2018 ዓ.ም አስመረቋል።
በመርሐ ግብሩ ለተመራቂ ተማሪዎች የእንኳን ደስ አላችሁና የማኅበሩን መልእክት ያስተላለፉት የማእከሉ ሰብሳቢ ድረስ እንዳላማው ጌታ በወንጌሉ
“ነገር ግን ሽሽታችሁ በክረምት እንዳይሆን ጸልዩ” (ማቴ.24 ÷20) በማለት የክረምትን ዝናብ ውርጭ፣ ጭቃ የተሰቀቀ /የሰነፈ/ ገበሬ በበጋው ወራት ረሃብ፣ ችጋር፣ ሰቆቃ እንደሚያጋጥመው የታወቀ ነው። እናንተ ይህንን ተገንዝባችሁ እንደ ታታሪ ገበሬ በበጋ መሬቱን አርሶ እና አለስልሶ፣ ዘሩን አዘጋጅቶ፣ በክረምት ዘርቶ፣ አርሞ ኮትኩቶ በመኸር ወቅት መልካሙን የስንዴ፣ የጤፍ፣ የገብስ ምርቱን በብዙ ትዕግሥት ጠብቆ እንደሚሰበስበው ሁሉ እናንተም ለዚህ ፍሬ ለመብቃት ወጥታችሁ፣ ወርዳችሁ፣ ረጅም ሰዓታትን አንብባችሁ፣ ብዙ መጻሕፍት በማገላበጥ፣ ለትምህርቱ የተመደበውን ሰዓት በክፍል ተቀምጣችሁ ተምራችሁ እና የሚሰጡ የቤት ሥራዎችን እና ፕሮጀክቶችን በተገቢው ሁኔታ ሠርታችሁ፣ የቀረቡላችሁን የተለያዩ ፈተናዎችን በማለፍ፣ የመምህሮቻችሁን ቃል ተቀብላችሁ፣ የቤተሰቦቻችሁን እና የጓደኞቻችሁን በጎ ምክር ሰምታችሁ ለዚህች ፍሬ የበቃችሁ ያለመታከት በብዙ ትዕግሥት ነውና እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
ከተመራቂ የግቢ ጉባኤ ተማሪዎች መካከል ከቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ማኔጅመንት ትምህርት ክፍል ተማሪ ነጋሽ አሰፋ 39A⁺ በማስመዝገብ አጠቃላይ 3.98 ውጤት በማምጣት 1ኛ ደረጃን እና ተማሪ ቤተልሔም ጥላሁን 3.92 እንዲሁም 30A⁺ በማምጣት በዩኒቨርሲቲ ደረጃ የተዘጋጀውን ዋንጫ በሁለቱም ጾታ በማሸነፍ በድምሩ ስድስት ሜዳሊያዎችን በመውሰድ በሁለት በኩል የተሳሉ ሰይፎች የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች መሆናቸውን በአደባባይ አስመስክረዋል።
ዘገባ በማኅበረ ቅዱሳን የደብረ ማርቆስ ማእከል ሚዲያ አገልግሎት ነው።👇👇👇👇👇👇👇
የማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ሚዲያ አውታሮች ይቀላቀሉ
ቴሌግራም፡- http://t.me/mkpublicrelation
የማኅበረ ቅዱሳን ሕዝብ ግንኙነት:-https://www.facebook.com/mahiberekidusan.mkusa/
ድረገጽ፡- http://www.eotcmk.org
ዩ ቲዩብ፡- http://www.youtube.com/user/EOTCMK
:- https://www.youtube.com/@-zemawetibebzmk7905
