‹‹እኔ እግዚአብሔር ነኝ›› (ዘፀ. ፮፥፪)

እግዚአብሔር አምላካችን ሰማይና ምድርን፣ መላእክትን፣ ሰውን እንዲሁም ፍጥረታትን በሙሉ የፈጠረ አምላክ ነው፡፡ ለፍጥረታቱም ህልውናውን እንደብቃታቸው ይገልጻል፤ በጥንተ ተፈጥሮ እግዚአብሔር አምላክ መላእክትን ለባውያን (አዋቂዎች) አድርጎ ከፈጠራቸው በኋላ በሰጣቸው ዕውቀት ተመራምረው ፈጣሪያቸውን ያመልኩት ዘንድ እንዲሁም ከባሕርዩ ፍጹም ርቀት የተነሣ በመካከላቸው ሳለ ተሰወረባቸው፡፡ መላእክትም ተፈጥሮአቸውንና ፈጣሪያቸውን መመርመር ጀመሩ፤ አንዱም ለአንዱ ‹‹አንተ ምንድን ነህ? ከየትስ መጣህ?›› ይባባሉ፣ እርስ በርሳቸውም እየተያዩ በተፈጥሮአቸው ይደነቁ ነበር፡፡ በኋላም ‹‹ማን ፈጠረን? ከየትስ መጣን?›› የሚለው የማኅበረ መላእክት ጥያቄ መበርታቱን የተረዳው ሳጥናኤል ሹመቱ ከሁሉ በላይ ነበርና አሻቅቦ ቢያይ ‹እኔ ነኝ ባይ› ድምጽ አጣ፤ ዝቅ ብሎም ቢያዳምጥ ከእርሱ በክብር ያነሱ መላእክት ይመራመራሉ፤ ‹ለምን እኔ ፈጠርኳችሁ ብዬ ፈጣሪነትን በእጄ አላስገባም› ብሎ አሰበ፤ ከዚያም ‹እኔ ፈጣሪያችሁ ነኝ› በማለት ተናገረ፡፡…

የቀለሙ ልጅ

ከጸሐፊው ማስታወሻ…

አባቴ ሲጠራ ሲነሣ ሰማሁኝ
የአብራኩ ክፋይ የቀለሙ ልጅ ነኝ
አባቴን አታንሳው እኔ እበቃለሁኝ
አባትህ ተረት ነው ብለህ ለጠየከኝ…

‹‹ከእነዚህ ታናናሾች አንዱ እንኳ ይጠፋ ዘንድ በሰማያት ባለው አባቴ ፊት አይፈቀድም›› (ማቴ. ፲፰፥፲፬)

የማቴዎስ ወንጌልን ከቁጥር ዐሥራ አንድ ጀምረን ስናበብ እንዲህ የሚል ቃል እናገኛለን፤ ‹‹የሰው ልጅ የጠፋውን ሊፈልግ፣ የተጎዳውን ሊያድን መጥቷልና፤ ምን ትላላችሁ? መቶ በጎች ያለው ሰው ቢኖር ከመካከላቸውም አንዱ ቢጠፋው፥ ዘጠና ዘጠኙን በተራራ ላይ ትቶ የጠፋውን ሊፈልግ ይሄድ የለምን? እውነት እላችኋለሁ፤ ባገኘው ጊዜ ካልጠፉት ከዘጠና ዘጠኙ ይልቅ ጠፍቶ ስለ ተገኘው ፈጽሞ ደስ ይለዋል፡፡ እንዲሁም ከእነዚህ ታናናሾቹ አንዱ እንኳ ይጠፋ ዘንድ በሰማያት ባለው አባቴ ፊት አይፈቀድም፡፡›› (ማቴ. ፲፰፥፲፩-፲፬)

ሰሙነ ፋሲካ

በሰሙነ ፋሲካ ከትንሣኤ እሑድ ጀምሮ እስከ ሳምንቱ እሑድ ድረስ የሚገኙት ዕለታት የተለያየ ስያሜ አላቸው፤ እነርሱም፡-

‹‹እርሱ እንደተናገረው ተነሥቶአል›› (ማቴ. ፳፰፥፮)

በዕለተ ቅዳሜ ለእሑድ አጥቢያ በመንፈቀ ሌሊት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ክፈቱልኝ መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል ከመቃብር ተነሣ፤ ነቢዩ ዳዊትም ‹‹እግዚአብሔርም ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ›› ብሎ እንደተናገረው አምላካችን ከሙታን ተለይቶ ተነሥቶአል፡፡ ትንሣኤ ሙታንን እናከብርም ዘንድ ይገባልና ክርስቲያኖች በሙሉ ደስ ይበለን! (መዝ. ፸፯፥፷፭)

የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞት (ሰሙነ ሕማማት)

ጌታችን በመስቀል ላይ ሳለ ዘጠኝ ሰዓት ሲሆን ‹‹ሁሉ ተፈጸመ›› አለ፡፡ ያን ጊዜም   ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው በፈቃዱ ለየ፡፡ አይሁድም ቀጣዩ ቀን ሰንበት ነውና እኒህ ሰዎች እንደተሰቀሉ አይደሩ ብለው ጭን ጭናቸውን ሰብረው ያወርዷቸው ዘንድ ጲላጦስን ጠየቁት፤ እርሱም ፈቀደላቸው፡፡ ጭፍሮቹም የሁለቱን ወንበዴዎች ጭናቸውን ሰብረው አወረዷቸው፡፡ ወደ ጌታችንም ሲቀርቡ ፈጽሞ ሞቶ አገኙት፤ በዚህም ‹‹ከሥጋውም አንዳች ከቤት ወደ ሜዳ አታውጡ፤ አጥንቱንም አትስበሩ›› ተብሎ የተነገረው ምሳሌያዊ ትንቢት ፍጻሜ ያገኝ ዘንድ ጭኑን ሳይሰብሩት ቀሩ፡፡ (ዘፀ.፲፪፥፵፮)

በእንተ ዕለተ ስቅለት

ጨረቃ ደም ሆነች፤ ፀሐይም ጨለመ
ከዋክብት ረገፉ፤ ሐኪሙ ታመመ
ልዑል ተዋረደ፤ ጌታ ሎሌ ሆነ
ፈጣሪ ሠራው ፍጡሩ በየነ…

ቀራንዮ

ቀራንዮ … ቀራንዮ …ቀራንዮ ጎልጎታ

የተለየሽው ከሁሉ ቦታ

የመከራ ቤት የደም ማማ

የመስቀል ዙፋን የግፍ አውድማ…

ዕለተ ዓርብ በሰሙነ ሕማማት

ዕለተ ዓርብ አዳምን ከሰይጣን ባርነት ነፃ ለማውጣትና የእርሱን የበደል ዕዳ ለመክፈል አምላካችን መከራ መስቀሉን የተሸከመበት ዕለት፣ የኀዘን ዕለት፣ የድኅነትም ዕለት ነው፡፡ ዓርብ ማለት ዐረበ ገባ (ተካተተ) ካለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጕሙም መካተቻ ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ፍጥረቱን ከእሑድ ጀምሮ በስድስተኛው ቀን ዓርብ አዳምን በመፍጠር ሥራውን ሁሉ አጠናቋልና (አካቷልና)፡፡ በኋላም በኦሪት ሕዝበ እስራኤል ከሰማይ የሚወርድላቸውን መና በሙሴ ትእዛዝ መሠረት ዓርብ ዕለት የቅዳሜን ጨምረው (ቅዳሜ ሰንበት ስለሆነ እህል መሰብሰብ ስለማይገባ) አካተው ይሰበስቡ ነበር፡፡  (ዘፀ.፲፮፥፬)

ሰሙነ ሕማማት

በዚህ ሳምንት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጅ በሙሉ ያደረገውን ትድግና ቅዱሳት መጻሕፍት በተለይም ግብረ ሕማማት የተባለው የቤተ ክርስቲያናችን መጽሐፍ ነገረ ሕማማቱን መከራ መስቀሉን በሰፊው ይናገርለታል፡፡ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችንም መድኃኒታችን ክርስቶስ አንዳች በደል ሳይኖርበት በሰውነቱ የደረሰበትን ሕማሙንና መከራውን ሞቱንም እያሰብን ይህንን የዐቢይ ጾምን መጨረሻ ወቅት ወይም ስምንተኛውን ሳምንት በካህናቱ መሪነት ሁላችን ምእመናን በተረጋጋ ኅሊና  አብዝተን በመጾም፣ በመጸለይና በመስገድ እንድናከብር ሥርዓትን ሠርታልናለች፡፡ ለዚህም ነው ዛሬ ኦርቶዶክሳውያን ምእመናን ሁሉ ይህንን የጌታን የሕማማት ሰሙን ከተድላ ከደስታ በመራቅ ነገረ መስቀሉን እያሰቡ በኀዘንና በልቅሶ ሆነው የሚያሳልፉት፡፡