‹‹ማእከለ አሥዋክ ዘጸገየት ጽጌ ሃይማኖት፤ በእሾሆች መካከል የበቀለች የሃይማኖት ተክል- ቤተ ክርስቲያን››
ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ‹‹ማእከለ አሥዋክ ዘጸገየት ጽጌ ሃይማኖት፤ በእሾሆች መካከል የበቀለች የሃይማኖት ተክል›› በማለት ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስቀድሞ በድጓው እንደተናገረው ቅድስት ቤተክርስቲያን ከቀደመው ዘመን ማለትም በክርስቶስ ደም ከተመሠረተችበት ጊዜ ጀምሮ አኗኗሯ ሁሉ ውድቀቷንና ጥፋቷን በሚሹ በአሕዛብ በመናፍቃንና በዓላውያን ነገሥታት በእነዚህ እሾሆች መካከል ነው፡፡