‹‹የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙርያ ይሠፍራል፤ ያድናቸውማል›› (መዝ. ፴፬፥፯)

ኃያሉ ሊቀ መላእክ ቅዱስ ገብርኤል በሐምሌ ፲፱ ቀን ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ ቅዱስ ቂርቆስ እና ቅድስት ኢየሉጣ ከእሳት አድኗቸዋል፡፡ በቅዱሳት መጻሕፍት እንደተመዘገበውም ታሪኩን ይዘንላልችሁ ቀርበናል፤ መልካም ንባብ፡፡

ቅድስት ሥላሴ

የሁሉ ፈጣሪ የዓለም ገዢ አምላካችን እግዚአብሔር በሐምሌ ፯ ቀን ወደ ጻድቁ አብርሃም ቤት በመግባት በአንድነትና በሦስትነት ክብሩ ተገለጠለት፡፡ምሥጢረ ሥላሴን በሚገባ መርምሮ መረዳት ለማንም ቢሆን ባይቻልም ምሥጢረ ሥላሴ በምሥጢረ ጥምቀት ተገልጧል፡፡…

ብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስ ወቅዱስ ጳውሎስ

ቅዱሳን ሐዋርያት ገድላቸው የተጻፈላቸው፣ በዓላቸው የተከበረላቸው የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች ናቸው። በቤተ ክርስቲያናችን በሐምሌ ፭ ቀን በታላቅ ድምቀት በዓላቸው ከሚከበረው ሐዋርያት መካከል የሐዋርያው የቅዱስ ጴጥሮስና የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስን ታሪክ እንደሚከተለው አቅርበነዋል።…

ልደቱ ለቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ

ጌታችን ኢየሱስም ቅዱስ ዮሐንስ ‹‹ሴቶች ከወለዱአቸው መጥምቁ  ዮሐንስን የሚበልጠው የለም›› ብሎ የመሠከረለት ነቢይ፣ ሐዋርያ፣ ሰማዕት ነው፡፡ 

ሕንጸታ ቤታ

በሀገረ ቂሣርያ፣ ኬልቄዶንያ አውራጃ የመጀመሪያዋ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን የታነጸችበት ዕለት ሰኔ ፳ ‹‹ሕንጸታ ቤታ›› የተከበረ ነው፤ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያለ እንጨት፣ ያለ ጭቃና ያለ ውኀ በሦስት ድንጋዮች ቤተ ክርስቲያኗን ያነጸበት ዕለት ነውና፡፡

አባ ገሪማ ዘመደራ

…አባ ገሪማ መጽሐፍ እየጻፉ ከቆዩ በኋላ መምሸት በመጀመሩ ፀሐይ ሊጠልቅ ተቃረበ፤ ያን ጊዜም በጸሎታቸው ጽሕፈታቸውን እስኪፈጽሙ ድረስ ፀሐይን በቦታው እንዲቆም አደረጉ፤ በኋላም ከእጃቸው የወደቀው ብዕር ወዲያው በቅሎ፣ አቈጥቍጦ አደገ፡፡ ምራቃቸውን ትፍ ያሉበት ሥፍራም እስከ ዛሬ ድረስ ሕሙማንን ይፈውሳል፡፡

ርደተ መንፈስ ቅዱስ

ርደተ መንፈስ ቅዱስ ወይንም የመንፈስ ቅዱስ መውረድ በብሉይ ኪዳን በትንቢት የተነገርና  በሐዲስ ኪዳን የተፈጸመ ነው፡፡ ነቢዩ ኢዮኤል ስለ መንፈስ ቅዱስ ወደዚህ ዓለም መውረድ፣ በመንፈስ ቅዱስ ጸጋና ሀብትነት ዓለም እንደሚታነጽና ሃይማኖት እንደሚጸና እንዲህ ሲል ተናግሯል፤ ‹‹ከዚህም በኋላ እንዲህ ይሆናል፤ መንፈሴን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ካይ አፈሳለሁ፡፡›› (ኢዩ. ፪፥፳፰)

የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓል

አንድ አምላክ በኾነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሰኔ ዐሥራ ሁለት፤ በዚች ዕለት የከበረ የመላእክት አለቃ የመልአኩ የሚካኤል የመታሰቢያውን በዓል ያከብራሉ፡፡ የሚያከብሩበትም ምክንያት እንዲህ ነው፤…

‹‹ጌታችን በመለከት ድምጽ ዐረገ›› (መዝ. ፵፮፥፭)

ነቢዩ ዳዊት ለመዘምራን አለቃ የቆሬ ልጆች አስቀድሞ በመንፈሰ ትንቢት ‹‹አምላካችን በዕልልታ፥ ጌታችንም በመለከት ድምጽ ዐረገ፥ ዘምሩ፥ ለአምላካችን ዘምሩ፤ ዘምሩ፥ ለንጉሣችን ዘምሩ››  በማለት እንደተናገረ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ሥራውን ፈጽሞ ከሙታን ተለይቶ ከተነሣ በኋላ በዐርባኛው ቀን ዐርጓል፤ እኛም ይህንን ቃል በማሰብና በማክበር የጌታችንን የዕርገት በዓል ተስፋ መንግሥተ ሰማያትን አመላካች በመሆኑ በዝማሬ እና በዕልልታ እናከብር ዘንድ ይገባል፡፡ (መዝ.፵፮፥፭)

ደብረ ምጥማቅ

ግብጽ በምትገኘው በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም በተሠራችው ደብረ ምጥማቅ ቤተ ክርስቲያን ጉልላት ላይ ድንግል ማርያም ከግንቦት ፳፩ ጀምሮ እስከ ፳፭ ቀናት በተከታታይ በመገለጧ ሕዝበ ክርስቲያን በዓሏን ያከብራሉ፡፡