Entries by Mahibere Kidusan

ጾመ ነነዌ!!

ጥር 25/2004 ዓ.ም.

በገብረእግዚአብሔር ኪደ

ነነዌ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ታሪካቸው በስፋት ከተጻፈላቸው የሜሶፖታምያ ከተሞች አንዷ ናት፡፡ ብዙ የሥነ መለኲት ምሁራን ከዛሬዋ የሞሱል ከተማ በተቃራኒ ከባግዳድ ሰሜን ምዕራብ 350 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ እንደ ነበረች ይስማማሉ፡፡ ምንም እንኳን በ4000 ቅ.ል.ክ. ገደማ በናምሩድ በኩል ብትቆረቆርም /ዘፍ.10፡11-12/ የአሦራውያን ዋና ከተማ የሆነችው ግን በ1400 ቅ.ል.ክ. ነው /2ነገ.19፡36/፡፡ በከተማዋ በጣም ታዋቂ የነበረው የጣዖት ቤተ መቅደስ የአስታሮት ቤተ መቅደስ ይባላል፡፡

ተዋሕዶ ያለ ጥርጥር ታላቅ ምስጢር /1ኛጢሞ 3፥16/

ጥር 23/2004 ዓ.ም.

በዲ/ን ኅሩይ ባየ

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ የሁለት ዓመት የዕሥር ጊዜውን ጨርሶ ከሮም ከተማ ከወጣ በኋላ ጥቂት የአገልግሎት ጊዜ ሲያገኝ በ66 ዓ.ም የመጀመሪያዋን የጢሞቴዎስ መልእክት ጽፏል፡፡

0015“እግዚአብሔር ዓለምን ከፈጠረበት ጥበቡ ዓለምን ያዳነበት ጥበቡ ይበልጣል” እንደሚባለው  በግብር በቃል በሐሳብ ሥነ ፍጥረትን ከፈጠረበት አምላካዊ ጥበቡ ይልቅ ሰው በወደቀ ጊዜ ከወደቀበት የተነሣበት የአምላክ ሰው መሆን ምስጢር ታላቅ በመሆኑ ይኸ ምስጢር ያለጥርጥር ታላቅ ነው ተብሎ ተጽፏል፡፡ “በሥጋ የተገለጠ በመንፈስ የጸደቀ ለመላእክት የታየ በአሕዛብ የተሰበከ በዓለም የታመነ በክብር ያረገ” ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጠባብ ደረት በአጭር ቁመት ተወሰኖ እኛን ያዳነበት ጥበቡ ታላቅ ነው፡፡

የግቢ ጉባኤያት ተማሪዎች የንስሐ አባቶች ሴሚናር ተካሔደ

በ ዲ/ን  ኅሩይ ባየ

kahinatSeltenaበማኅበረ ቅዱሳን አዘጋጅነት ከጥር 16-18 ቀን 2004 ዓ.ም ድረስ  የግቢ ጉባኤያት ተማሪዎች የንስሐ አባቶች ሴሚናር   በማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል  ተካሔደ ፡፡

 

በማኅበረ ቅዱሳን የሀገር ውስጥ ማዕከላት ግቢ ጉባኤያት ማደራጃና ማስተባበሪያ ዋና ክፍል ሓላፊ የሆኑት ዲያቆን አንዱአምላክ ይበልጣል እንደገለጡት የንስሐ አባቶች በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገኙ ተማሪዎችን ዘመኑን የዋጀ ትምህርት እንዲያስተምሩና አባታዊ ተልእኳቸውን እንዲወጡ ሴሚናሩ እንደሚያግዛቸው አብራርተዋል፡፡ በተጨማሪም በሥልጠናው ላይ የተገኙ ካህናት ከተለያዩ ቦታ የመጡ በመሆናቸው በአንድ የሥልጠና ቦታ ተገኝተው ልምዳቸውን እንዲለዋወጡና እንዲመካከሩ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ ሴሚናር መሆኑን ገልጠዋል፡፡

ቃና ዘገሊላ(ለሕፃናት)

ጥር 17/2004 ዓ.ም በአቤል ገ/ኪዳን አንድ ቀን በገሊላ አውራጃ ቃና በሚባል ቦታ የሚኖር አንድ ዶኪማስ የሚባል ሰው ሰርግ ደግሶ እመቤትችን ቅድስት ድንግል ማርያምን እና ሌሎች ብዙ ሰዎችን ጋበዘ፡፡ እመቤታችንም በግብዣው ላይ ከልጇ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር፣ ከሐዋርያት ጋር ተገኘች፡፡ ምግቡና መጠጡ ቀረበ፡፡ ትንሽ ቆይቶ ግን የወይን ጠጁ አለቀ፡፡ በዚህ ጊዜ የሰርጉ አስተናጋጆች በጣም መጨነቅ […]

ቡቱሽና ኪቲ /ለሕፃናት/

ጥር 15/2004 ዓ.ም. በቴዎድሮስ እሸቱ ውድ ሕፃናት እንደምን ሰነበታችሁ ለዛሬ አንድ ተረት አስነብባችኋለሁ፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን ቡቱሽና ኪቲ የሚባሉ ሁለት እኅትማማች እንቁራሪቶች በአንድ ወንዝ ውስጥ ይኖሩ ነበር፡፡ ኪቲ የእናቷን ምክር የምትሠማ ጎበዝ ልጅ ስትሆን ቡቱሽ ግን የእናቷን ምክር የማትሰማ የታዘዘችውን የማትፈጽም ልጅ ነበረች፡፡ እናቷ “ተይ ቡቱሽ ወደ ወንዙ መሐል አትግቢ አደጋ ይደርስብሻል፡፡” ስትላት አትሰማም ነበር […]

የ2004 የከተራ በዓል አከባበር ከዓድባራቱ እሰከ ጃንሜዳ፡፡

ጥር 11/2004ዓ.ም.

በእንዳለ ደምስስ

በቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓት መሠረት ዐበይት በዓላት ተብለው ከሚጠቀሱት መካከል የጥምቀት በዓል አንዱ ነው፡፡ይህንም በዓል ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ፤ በማእከለ ዮርዳኖስ የተጠመቀበትን  ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በየዓመቱ ከዋዜማው ከጥር 10 ጀምሮ በደመቀ ሁኔታ በማክበር ላይ ትገኛለች፡፡ ለእኛ አብነት ይሆነን ዘንድ፤ የእዳ ደብዳቤያችንን እንደ ገል ቀጥቅጦ እንደ ሰም አቅልጦ በደላችንን ይደመስስ ዘንድ ጌታ በዮርዳኖስ ወንዝ ተጠመቀ፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ይህንን መሠረት በማረድግ በየአብያተ ክርስቲያናቱ የሚገኙ ታቦታት በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ፣ በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ በካህናትና ዲያቆናት፤ እንዲሁም በሰንበት ት/ቤቶች መዘምራንና ምእመናን በዝማሬ በመታጀብ በአቅራቢያቸው ወደሚገኘው ታቦት ማደሪያ በማምራት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ በመሔድ በዮሐንስ እጅ ለመጠመቅ ማምራቱን ያበሥራሉ፡፡ ‹‹ያን ጊዜም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከገሊላ ናዝሬት መጣ ዮሐንስም በዮርዳኖሰ ወንዝ አጠመቀው›› እንዲል፡፡/ማቴ.3፡1/

 

dsc01723

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መሥራቿን መድኀኔዓለም ክርስቶስን ለዓለም የምትሰብክበት፣ ከእርሱም ያገኘችውን፣ ይህም ዓለም እንደሚሰጠው ያልሆነውን፣ የእግዚአብሔር ልጅነት፣ ሰላም፣ ፍቅርና ትሕትና ለዓለሙ ትሰብክበታለች፡፡ እንዲሁም ለአገራችን በጎ ገጽታን በመፍጠር ረገድ ከተለያዩ አገራት የሚመጡ ጎብኚዎች ተደንቀው የሚያዩትና አንዳንዶች ልባችውን ለእውነት ክፍት ያደረጉ የሚያምኑበት በመስተንግዶው የሚደመሙበት በመሆኑ ሃይማኖታዊ በዓሉን በልዩ ትኩረት ታከብራለች፡፡

ሁለቱ የዘመነ አስተርዮ ክብረ በዓላት በዳግማዊት ኢየሩሳሌም

ጥር 11/2004ዓ.ም

ዲ/ን ጌታየ መኮንን

የ2004 ዓ.ም የጌታችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ከርስቶስ የልደት (የገና) እና የጥምቀት በዓላት አከባበር እንደወትሮው ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን የጠበቀና ያማረ ነበር፡፡

p1180004

ካህናቱ ከታኅሣሥ 27 ቀን ጀምሮ በመድኀኒዓለም ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት መስጠት የጀመሩ ሲሆን፤ የአማኑኤል በዓል ዋዜማ ጠዋት ደወል ተደውሎ በጣም በደመቀ ሁኔታ ዋዜማው ተቆሞ ውሏል፡፡ 7 ሰዓት ሲሆን ቅዳሴ ተገባ እስከ 9 ሰዓት ቅዳሴ ተጠናቀቀ፡፡ ማታ 2 ሰዓት ማሕሌት ተደውሎ እስከ ለሊቱ 10 ሰዓት የቀጠለ ሲሆን ከ10 ሰዓት እስከ 12 ሰዓት የቅዳሴው ሥርዓት ተከናውኗል፡፡ ጠዋት 3 ሰዓት የልደት በዓል ዋዜማ ተደውሎ እስከ 10 ሰዓት እንደቦታው ትውፊትና ሥርዓት መሠረት የቦታው ቀለም እየተባለ የዋዜማው ቅኔ ለባለ ተራዎቹ እየተሰጠ ተከናውኗል፡፡ ማታ 2 ሰዓት የበዓሉ ደወል ተደውሎ ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የመጡ ምእመናን፣ የውጭ ሀገር ዜጎች፣ የቤተ ማርያምን የውስጥና የውጭ ቦታ ማሜ ጋራ የተባለውን ቦታ ከበው በእልልታ በጭብጨባ ጧፍ እያበሩ ማኅሌቱ በመዘምራኑ፣ በካህናቱ፣ በዲያቆናቱ በድምቀት ቃለ እግዚአብሔሩ እየተዘመረና እየተወረበ አድሯል፡፡

 

ከቦታው ቀለሞች   «ክርስቶስ መጽአ ውስተ ዓለም»

«ኮከብ ርኢነ ወመጽአነ ንሰግድ ሎቱ ለዘፈለጠ ብርሃነ»

 

የጌታ ጥምቀት(ለሕፃናት)

ጥር 10/2004 ዓ.ም.

በእኅተ ፍሬስብሐት

የጥምቀት በዓል ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተጠመቀበትን ዕለት የምናከብርበት በዓል ነው፡፡

 

ጌታችን ከተወለደ በኋላ 30 ዓመት ሲሆነው ዮርዳኖስ ወደሚባለው ወንዝ ሔደ፡፡ በዚያም መጥምቁ ዮሐንስ አጠመቀው፡፡ ጌታችን ሲጠመቅ ከሌሊቱ 10 ሰዓት ነበር፡፡ ሌሊት ደግሞ ርግብ አይኖርም፤ ምክንያቱም ወደ ጎጇቸው ስለሚገቡ ነው፡፡ በዚያች ዕለት ግን ጌትችን ሲጠመቅ ርግብ መጥታ በራሱ ላይ አረፈች፡፡ ከዚያም ከሰማይ አንድ ድምጽ ተሰማ፤ ድምጹም

“የምወደው ልጄ ይህ ነው፡፡ እርሱን ስሙት” የሚል ነበር፡፡ ይህ የእግዚአብሔር ድምጽ ነበር፡፡

በነገር ሁሉ ደስ ልታሰኙ ለጌታ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እንለምናችኋለን ቆላ.1፥19

ጥር 9/2004 ዓ.ም

በዓላት ቤተ ክርስቲያን አገልግሎቷን ከምትፈጽምባቸው ሥርዓቶች መካከል እንደ አንዱ ሆነው ይጠቀሳሉ፡፡ በበዓላት ምእመናን ረድኤት በረከት ከማግኘታቸው ባለፈ ቤተ ክርስቲያን የምትሰጣቸውን አገልግሎቶች የሚቀበሉባቸው መንፈሳዊ መድረኮች ናቸው፡፡ በበዓላቱ መምህራን ትምህርተ ወንጌልን ለምእመናን ያደርሳሉ፡፡ በበዓላት አከባበር ሥርዓት ውስጥ ምእመናን በቤታቸው፤ በአካባቢያቸውና በአደባባይ ሁሉም በጋራ በኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነትና ጌትነት፣ ለሰውም ያደረገውን የማዳን ሥራ የሚመሰክሩበት፣ በቤተ ክርስቲያን እምነትና ሥርዓት ላይ ያላቸውን ጽናት ለየትኛውም ወገን ያለሀፍረት የሚገልጹበት የአገልግሎት ዕድል ነው፡፡

ትምህርተ ጥምቀት በአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ

 

ጥር 7/2004 ዓ.ም
{gallery count=1 width=350 height=300 counter=1 links=0 alignment=center animation=3000}Temkete{/gallery}

መግቢያ

ይህ ጽሑፍ መጽሐፈ ምሥጢር ከሚባለው ከአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ድርሰት የተወሰደ ሲሆን አባ ጊዮርጊስ ጥምቀትን አስመልክቶ የሰጠውን ድንቅ የሆነ አስተምህሮ እናስተውልበታለን፡፡

“…እነሆ ቅዱስ ጳውሎስ መንፈስ ቅዱስን “የክርስቶስ ሕይወት” በማለት ሰየመው መንፈስ ቅዱስ የክርስቶስ ሕይወት ከሆነ እንዴት አያየውም? ከማየት ዐሳብ ይቀድማልና ከውጫዊ እይታ የአእምሮ እይታ ይበልጣልና ዳግመኛ ቅዱስ ጳውሎስ የሰውን ዐሳብ ከራሱ ከሰውየው በቀር የሚያውቅ የለም፡፡ እኛ ግን የተሰወረውን ገልጦ ጥልቁን መርምሮ የሚያውቅ የእግዚአብሔር መንፈስ አለን” 1ቆሮ.2፥11 አለ፡፡ አንተ ግብዝ ሆይ አብን እንደሚያውቀው ዕወቅ /አስተውል/፡፡ በወንጌል እንደተነገረው ወልድ ብቻውን ምንም ምን ሊያደርግ አይችልም ከአብ ያየውን ይሠራል እንጂ፡፡ አብ የሚሠራውን ወልድም ይህንኑ እንደእሱ ይሠራል፣ አብ ልጁን ይወዳልን የሚሠራውንም ሥራ ሁሉ ያሳየዋል፡፡ ከዚህም የሚበልጥ ሥራ ያሳየዋል፣ እናንተም ታውቁና ታደንቁ ዘንድ ስለ መንፈስ ቅድስም  አስቀድመን ነገርናችሁ፡፡ በደለኞች ሆይ ከዛሬ ጀምሮ “ወልድ ከአብ ያንሳል አያህለውም” አትበሉ፡፡ “መንፈስ ቅዱስም ከወልድ ያንሳል አያህለውም ” አትበሉ፡፡