Entries by Mahibere Kidusan

የተዘጉ በሮች ይከፈቱ

ብዙዎቻችን ከእኛ ውጭ ስላሉ አካላት ሲነገረን ለማድመጥ የምንፈልገው የሆኑትንና እውነታውን ሳይሆን እኛ ሊሆኑት የምንፈልገውን ነው፡፡ ስለዚህም ስለምንነቅፋቸው አካላት የሚከሰሱበትንና የሚጐነተሉበትን እንጂ እውነታውን መስማት አሁን አሁን የኮሶ ያህል የሚሰቀጥጥ፣ የሞትም ያህል የሚያስደነግጥ ሆኖአል፡፡ እንዲህ ያሉት ነገሮች የሚከሰቱት ደግሞ በሁሉም ማኅበረሰብ መሆኑ ነገሩን የበለጠ አሳሳቢ ያደርገዋል፡፡

የይሁዳ ሰላምታ የቀሪ ሒሳብ ማስተካከያ ነው

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይሁዳን ከሐዋርያት እንደ አንዱ የመረጠበት ምስጢር እጅግ ጥልቅ ነው፡፡ ይህን ባናውቅ፣ ታሪኩ ባይጻፍና መምህራኑም በየጊዜው ባይነግሩን ኖሮ ዛሬ ብዙዎቻችን እንጨነቅ እንታወክም ነበር፡፡ እርሱን እንድናስታውሰው ያደረገን ደግሞ «ሃይማኖተ አበው የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማኅበር» ያቀረበው ተደጋጋሚ ጥያቄ ነበር፤ በቤተ ክርስቲያኒቱ ፈቃድ ተሰጥቶት የመንቀሳቀስ ጥያቄ፡፡ ጉዳዩን በቀጥታ ከማየታችን በፊት ግን ጌታችን ይሁዳን ሐዋርያ አድርጎ በመምረጡ ካስተማረን ትምህርት እንነሣ፡፡

Characters display problem

Problem Descirption The problem with display of characters is based on fonts that are installed on your machine. Fonts can be considered as the drawing instruction/picture for the computer so as to give us the display of the characters we are familiar with. Unfortunately, there are different fonts in use which cover different ranges of […]

ማኅበረ ቅዱሳን አምስት መጻሕፍትን አስመረቀ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የሚዲያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ክፍል አምስት አጻሕፍትን ጥር 30 ቀን 2001 ዓ.ም. አምስት ኪሎ በሚገኘው ብሔራዊ ሙዚየም አዳራሽ አስመረቀ

በቤተ ክርስቲያን ሥዕላት ዙሪያ የውይይት መርሐ ግብር ተካሄደ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የራሷን የአሳሳል ዘይቤ ጠብቃ ተንከባክባ ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ እንዳለባት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ባዘጋጀው የውይይት መርሐ ግቭር ተገለጸ