ጥምቀት
በዘመነ ሥጋዌ በናዝሬት ከተማ፤ ዮርዳኖስ ወንዝ የእስራኤል ሕዝብ በመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ እጅ ለመጠመቅ ተራ ይዘው በሚጠብቁበት ጊዜ እርሱ እንዲህ እያለ ይሰብክ ነበር፤ ‹‹እናንተ የእፉኝት ልጆች፥ ከሚመጣው መቅሠፍት ታመልጡ ዘንድ ማን ነገራችሁ? እንግዲህ ለንስሓ የሚያበቃችሁን ሥራ ሥሩ፤ አብርሃም አባታችን አለን በማለት የምታመልጡ አይምሰላችሁ፤ እግዚአብሔር ከእነዚህ ድንጋዮች የአብርሃም ልጆችን ማንሣት እንደሚችል እነግራችኋለሁ፡፡ እነሆ፥ ምሳር በዛፎች ላይ […]