የሀዋሳ ማእከል ሕግና ዕቅበተ እምነት ዋና ክፍል ተጠሪ የነበሩት አቶ አስማማው ታመነ አረፉ
በማኅበረ ቅዱሳን የሀዋሳ ማእከል ሕግና ዕቅበተ እምነት አገልግሎት ዋና ክፍል ተጠሪ የነበሩት አቶ አስማማው ታመነ ሐምሌ 18 ቀን 2012 ዓ.ም በደረሰባቸው ድንገተኛ የትራፊክ አደጋ ሕይወታቸው እንዳለፈ የሀዋሳ ማእከል አስታወቀ፡፡
This author has not written his bio yet.
But we are proud to say that Mahibere Kidusan contributed 1094 entries already.
በማኅበረ ቅዱሳን የሀዋሳ ማእከል ሕግና ዕቅበተ እምነት አገልግሎት ዋና ክፍል ተጠሪ የነበሩት አቶ አስማማው ታመነ ሐምሌ 18 ቀን 2012 ዓ.ም በደረሰባቸው ድንገተኛ የትራፊክ አደጋ ሕይወታቸው እንዳለፈ የሀዋሳ ማእከል አስታወቀ፡፡
ጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት በተጋድሏቸው ዘመን በአባ በጸሎተ ሚካኤል ገዳም ለዐሥር ዓመት በነበሩበት ጊዜ አገልጋዮቹ ወደ እርሳቸው መጥተው ይመክሯቸው ዘንድ ለመኗቸው፤ እርሳቸውም ‹‹ትዕግሥትን፣ ትሕትናን እና እግዚአብሔርን መፍራት ገንዘብ አድርጉ፤ እነዚህ ሦስት ነገሮች ሰውን ወደ ዘለዓለማዊ ሕይወት ያደርሱታል፡፡ እየጎተቱ ወደደይን ጥልቅነት የሚያወርዱ ሦስቱ የጥፋት ገመዶች እርሳቸውም ቅናት፣ ትዕቢትና ትምክሕት እንዳይጥሏችሁ ደግሞ ተጠበቁ›› ብለው መከሯቸው፡፡ (ገድለ ተክለ ሃይማኖት ፵፫፥፬-፮)
ከኤዶም ፈልቀው ምድርን ከሚያጠጡት አራት ወንዞች ኤፌሶን፣ ጤግሮስ፣ ኤፍራጥስ፣ መካከል ሁለተኛው ግዮን ወይንም ዓባይ ወንዝ የሀገራችን ሲሳይ /በረከት/ እንደሆነ ቅዱሳት መጻሕፍት ምስክሮች ናቸው፡፡ ‹‹ወንዝም ገነትን ያጠጣ ዘንድ ከኤዶም ይወጣ ነበር፤ ከዚያም ለዐራት መዓዝን ይከፈል ነበር፡፡ የአንደኛው ወንዝ ስም ኤፌሶን ነው፤ እርሱም ወርቅ የሚገኝበትን የኤውላጥ ምድርን ይከብባል፡፡ የዚያችም ምድር ወርቅ ጥሩ ነው፡፡ በዚያም የሚያብረቀርቅ ዕንቊ አለ፡፡ የሁለተኛውም ወንዝ ስም ግዮን ነው፤ እርሱም የኢትዮጵያን ምድር ሁሉ ይከብባል፤ የሦስተኛውም ወንዝ ስም ጤግሮስ ነው፤ እርሱም በአሶር ላይ የሚሄድ ነው፡፡ አራተኛውም ወንዝ ኤፍራጥስ ነው›› እንዲል፡፡ (ዘፍ. ፪:፲-፲፬)
የሰው ዘር በሙሉ ምድራዊ ሕይወቱ የሚፈጸምበት ዕለተ ሞቱ በመሆኑ ከዚህች ዓለም ይለያል፡፡ ነፍሳችን ከሥጋዋ ስትለይም ሥጋችን ሕይወት አይኖረውምና በድን ይሆናል፤ ሥጋ ፈራሽ እና በስባሽ ስለሆነም ወደ መቃብር ይወርዳል፤ ይህም ሥጋዊ ሞት ነው፡፡ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ በሚል መጽሐፋቸው ‹‹መሞት፣ መለየት፣ በነፍስ ከሥጋ፣ በሥጋ ከነፍስ መራቅ፣ እየብቻ መሆን፣ መድረቅ፣ መፍረስ፣ መበስበስ፣ መነቀል፣ መፍለስ፣ መጥፋት፣ መታጣት›› ሲሉ ስለሞት አስረድተዋል፡፡ (ኪዳነ ወልድ፣ገጽ፣፭፻፹፩)
መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ ለቅዱስ ቂርቆስና ለቅድስት ኢየሉጣ ተረዳኢ የሆነበት ሐምሌ ፲፱ ቀን ታላቅ በዓል በመሆኑ ቅድስት ቤተ ከርስቲያናችንም ታከብረዋለች፡፡ የእነዚህም ቅዱሳን ታሪክ በስንክሳር እንደተመዘገበው እንዲህ ይተረካል፡፡
እግዚአብሔር አምላክ ኃያልና ገናና ነው፤ የሚሳነውም የለምና ሁሉን ነገር በምክንያት ያደርጋል፡፡ ሰዎችም በሥነ ተፈጥሯችን የእርሱን ህልውና በማወቅ ለፈጣሪያችን እንገዛ ዘንድ ይገባል፡፡ ድኃም ሆነ ሀብታም፣ ባለሥልጣንም ሆነ ተራ ሰው በፈጣሪው መመካት ይችል ዘንድም ተገቢ ነው፡፡ በትንቢተ ኤርምያስም እንደተገለጸው ‹‹ጠቢቡ በጥበቡ አይመካ፤ ኃያልም በኃይሉ አይመካ፤ ባለጠጋም በብልጥግናው አይመካ፤ ነገር ግን የሚመካው፡- ምሕረትንና ፍርድን፥ ጽድቅን በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚያሰኘኝ ይህ ነውና›› ሲል አምላካችን እግዚአብሔር ነግሮናል፡፡ (ኤር. ፱፥፳፫)
በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የረጅም ዘመን ሐዋርያዊ ጉዞ ላይ በጎ ተፅዕኖ ካላቸው የአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አባቶች መካከል አንዱ ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬም ነው፡፡ ይህ አባት ምንም እንኳን በቋንቋ ውሱንነትና በቦታ ርቀት በርካቶች ሥራዎቹና ጽሑፎቹ የታወቁለት ባይሆንም ሕይወቱን በብሕትውና የመራ የትርጓሜ መጻሕፍትን፣ የቅኔ፣ የግጥምና የወግ ጽሑፍ በማዘጋጀት የኖረ ባለ በጎ ገድል አባት ነው፡፡
ሰዎች የዋህነት ወይንም ትሕትና ሲጎላቸው ከፍቅር ይልቅ መጥፎነት ያስባሉ፡፡ በቤተሰባዊም ሆነ በማኅበራዊ ግንኙነታቸው መከባበር እንዳይኖር፣ መናናቅ እንዲፈጠርና ክፋት እንዲስፋፋ ይጥራሉ፡፡ በዚህም ፍቅርና ሰላም አጥተው ዘወትር በስጋትና በጥላቻ ስሜት ይኖራሉ ማለት ነው፡፡
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በጅማ ሀገረ ስብከት የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል የተላለፍወን አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሽፋን በማድረግ አግባብ ያልሆነ እስርና እንግልት በምእመናንና በአባቶች ላይ እየተፈጸመ መሆኑን በማኅበረ ቅዱሳን የጅማ ማእከል አስታወቀ፡፡
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሜታ ሮቢ ወረዳ ቤተ ክህነት ሥር የሚገኘውን የሙጤ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያንን ቅርስ ዘርፈው እጅ ከፍንጅ የተያዙ አራት ግለሰቦች በፍርድ ቤት ትእዛዝ ከእስር መፈታታቸውን የወዳ ቤተ ክህነቱ ሥራ አስኪያጅ መሪጌታ ክፍሌ ቱቦ አስታወቁ፡፡
