ሰማዕታተ ጽድቅ ዘኢትዮጵያ!

አንጀትሽ አልችል ብሎ ሆድሽ ሲባባ

ፊትሽ ጠቊሮ ዓይንሽ የደም ዕንባ ሲያነባ

እናት ዓለም እማማ

አንቺ የክርስቲያኖች መለያ አርማ

አንቺ ስንዱ እመቤት ባለማዕረግ

የዕውቀት ምንጭ የጥበባት አፍላግ

እምነት ማንነትሽ በነጭ እንዲታደስ

መርዙ ከገበታሽ በማር እንዲለወስ

ሠገነትሽ በደም ዕንባ ሲታጠር

ኑፋቄ ከደጅሽ በዝቶ ሲቆጠር

የዓለምን ብልጽግና ግሳንግሱን

ንቀን ተጸይፈን ሹመት ሽልማቱን

ወርቅ ብር ቢመነዘር አያወጣምና ዋጋ

ስለ እናት ፍቅር እጃችን ለሰንሰለት ተዘረጋ

ሞት በአጋፋሪ ቢደገስልን

 ጦርነትም በዝቶ ሲያታክተን

እንደ መብረቅ ብልጭልጭታ እንደ ነጐድጓድ ቢያስፈራ

ክርስቲያኖች ከፊት ቆመናል ስለማይበግረን መከራ

እናቴ የነፃነትሽ ትርጉም የማንነትሽ መለያ

ለሃይማኖት ሟች ሰማዕታተ ጽድቅ ዘኢትዮጵያ!