Entries by Mahibere Kidusan

ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት ሰነበታችሁ? ትምህርት እንዴት ነው? መቼም ከመጀመሪያው የዓመቱ አጋማሽ ትምህርት ውጤታችሁ በመነሣት የበለጠ ጎበዝ ለመሆን እየተማራችሁ እንደሆነ ተስፋ እናደርጋለን! “ብልህ ልጅ ከስሕተቱ ይማራል” እንዲሉ አበው ከትናንት ድክመታችሁ በመማር የበለጠ ውጤታማ ተማሪ ለመሆን መሥራት ይገባል፡፡ ወላጆቻችን እኛን ለማስተማር ምን ያህል ዋጋ እንደሚከፍሉ አስተውሉ! ልጆች የእነርሱ ድካም እኛ መልካምና ጎበዝ እንድንሆን ነውና በርቱ! ለዛሬ የምንማማረው ስለ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ነው፤ መልካም ቆይታ!

መሠዊያው

በእስራኤል ምድር በሰማርያ ላይ አክዓብ ነገሠ

ጣዖትን አቆመ …መለከትን ነፋ …ለበኣል ደገሠ

የቤተ መቅደሱ መሠዊያው ፈረሰ

የእግዚአብሔር ካህናት ደማቸው ፈሰሰ

ምኵራብ

ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የዐቢይን ጾም ሦስተኛ ሳምንት ምኩራብ ብላ ትጠራዋለች። ዓመት እስከ ዓመት ያለውን ይትበሃል በያዘው ድጓ ዐቢይ ጾም በገባ በሦስተኛው ሳምንት መጀመሪያው ቀን ቅድስት በሆነች በሰንበት በሚዘመረው በጾመ ድጓው ክፍል “ቦአ ኢየሱስ ምኩራበ አይሁድ ወመሀረ ቃለ ሃይማኖት፤ ጌታችን ኢየሱስ ወደ አይሁድ ምኩራብ ገባ፤ የሃይማኖት ቃልን አስተማረ” ሲል እናገኘዋለን።

ዜና ዕረፍት

ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ በአብነት መምህርነታቸው አያሌ የቤተ ክርስቲያን አባቶችን በማፍራታቸውና ባበረከቱት የረዥም ዘመን አገልግሎት የመቀሌ ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራልና የከሣቴ ብርሃን ሰላማ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ኃላፊ ሆነው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ተሹመው በተመደቡበት ኃላፊነት ሲያገለግሉ ከቆዩ በኋላ የካቲት ፳፩ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ከዚህ ዓለም ድካም ዐርፈዋል።

የብፁዕነታቸው በረከት ይደርብን!

“ሰውን በአርአያችንና በአምሳላችን እንፍጠር” (ዘፍ.፩፥፳፮)

በዕለተ ዐርብ እግዚአብሔር አራት ፍጥረታትን ፈጠረ፡፡ እነርሱም በእግር የሚሽከረከሩ፣ በክንፍ የሚበሩና በልብ የሚሳቡ፣ በየብስ፣ የሚኖሩ በደመ ነፍስ ሕያዋን የሆኑ ፍጥረታትን ነው፡፡ በመጨረሻም እግዚአ ዓለም ሥላሴ “ሰውን በአርአያችንና በአምሳላችን እንፍጠር” ብለው በነግህ አራቱን ባሕርያተ ሥጋ አምስተኛ ባሕርየ ነፍስን አዋሕደው የሠላሳ ዓመት ጎልማሳ አድርገው በማዕከለ ምድር በቀራንዮ ፈጠሩት፡፡ (ዘፍ.፩፥፳፮)

ጌታችን ጾመ፤ በዲያብሎስም ተፈተነ (ማቴ.፬)

ጌታችን በገዳመ ቆሮንቶስ ሲጾም “ወቀርበ ዘያሜክሮ፤ ሰይጣን ሊፈትነው ቀረበ” ይላል፡፡ በመጀመያም እንዲህ አለው፤ “እመሰ ወልደ እግዚአብሔር አንተ በል ከመ እላ አዕባን ኅብስተ ይኩና፤ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፥ እነዚህ ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆኑ በል አለው።” (ማቴ. ፬፥፫) ሰይጣን የመጀመርያውን ሰው አዳም በመብል ድል ነሥቶት ስለነበር በለመደበት ክርስቶስን ድል ሊነሣ መጣ። ይኸውም አብ በደመና “የምወደው ልጄ እርሱ ነው” ሲል ሰምቶ ነበርና ይህን ተናግሯል። (ማቴ.፫፥፲፯) ሰይጣን እንዲህ ያለው በትርጓሜ ወንጌል እንደምናገኘው በአንድ እጁ ደንጋይ ይዞ በሌላ እጁ ደግሞ ዳቦ ይዞ በመቅረብ ነበር። ምን ነው ከያዝከው አንበላም ቢለኝ አዳምን ድል እንደነሣሁት እርሱንም ድል እነሣዋለሁ። ቢያደርገው ደንጋዩን ወደ ዳቦ ቢቀይረው ለሰይጣን ታዛዥ ብየ እዳ እልበታለሁ ብሎ ቀረበ። (የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፫ አንድንምታ ትርጓሜ)

ኪዳነ ምሕረት!

ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት አላችሁ? የዕረፍት ጊዜ እንዴት ነበር? መቼም ቁም ነገር ሠርታችሁበት እንዳሳለፋችሁ ተስፋችን ነው፡፡ ልጆች! ዛሬ የምንማማረው ስለ እመቤታችን ኪዳነ ምሕረትና ከአምላካችን ስለተሰጣት ቃል ኪዳን ነው፡፡

ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! ወር በገባ በ፲፮ኛው (ዐሥራ ስድስት) ቀን “ኪዳነ ምሕረት” ብለን የምናከብረውና የምንዘክረው ታላቅ በዓል አለ፡፡ ይህ በዓል ለምን የሚከበር ይመስላችኋል?