አዲስ አበባ ማእከል 26 ለሚሆኑ የአብነት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ለተከታታይ አምስት ቀናት ሲሰጥ የቆየው ሥልጠና መጠናቀቁን አስታወቀ
አዲስ አበባ ማእከል 26 ለሚሆኑ የአብነት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ለተከታታይ አምስት ቀናት ሲሰጥ የቆየው ሥልጠና መጠናቀቁን አስታወቀ
ሚያዝያ ፳፮/፳፻፲፰ ዓ.ም
በማኅበረ ቅዱሳን የአዲስ አበባ ማእከል ስብከተ ወንጌልና መንፈሳዊ ትምህርት ቤቶች አገልግሎት ዋና ክፍል ከተለያዩ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ለተውጣጡ 26 የአብነት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ለአምስት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የቆየው ሥልጠና መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ማእከል አስታውቋል።
በሥልጠናው 26 የሚሆኑ የአብነት ትምህርት ቤት ተማሪዎች የተሳተፉ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ አብዛኞቹ የአቡነ ሀብተ ማርያም የአብነት ትምህርት ቤት ተማሪዎች መሆናቸውን በማኅበረ ቅዱሳን የአዲስ አበባ ማእከል የስብከተ ወንጌልና መንፈሳዊ ትምህርት ቤቶች ክፍል ኀላፊ አቶ አዘዘ ፀሐዩ ገልጸዋል።
የሥልጠናው ዋና ዓላማ በአብነት ትምህርት ቤት የሚገኙ ደቀ መዛሙርት ብቁ እና ንቁ መሪ አገልጋይ ሁነው እንዲወጡ ማድረግ መሆኑን የገለጹት ኀላፊው በዚህ በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ላይ ንቁ ተሳትፎ ያላቸው መሪ ይሆናሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ በማንሳት ሥልጠናው ለነገዋ ቤተ ክርስቲያን ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለው ተናግረዋል።
በተጨማሪም ለአብነት ተማሪዎቹ የመጽሐፍ ስጦታ የተበረከተላቸው ሲሆን ነገ ላይ ካህናትና ጳጳሳት ሁነው በቤተ መቅደስ ውስጥ የሚያገለግሉ በመሆኑ ትኩረት ተሰጥቶ ሥልጠናው ሲሰጥ መቆየቱን ገልጸው በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል።
ከዚህ ባሻገር አብነት ትምህርት ቤቶቹ የአልባሳት፣ የመጠለያና የምግብ ችግር ያለባቸው በመሆኑ ማኅበሩ በተለያዩ ጊዜያት ድጋፍ እንደሚያደርግ ያነሱ ሲሆን ዘላቂ መፍትሔ እስኪመጣ ድረስ ምእመናን በተለይም ለዕለት ጉርስ እና ለዓመት ልብሳቸው የሚሆን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
ዘገባው የአዲስ አበባ ማእከል ነው
👇👇👇👇👇👇👇
የማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ሚዲያ አውታሮች ይቀላቀሉ
ቴሌግራም፡- http://t.me/mkpublicrelation
የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት፡- http://www.facebook.com/eotcmkidusan/
ድረገጽ፡- http://www.eotcmk.org
ዩ ቲዩብ፡- http://www.youtube.com/user/EOTCMK
:- https://www.youtube.com/@-zemawetibebzmk7905
