የምእመናን ድርሻ በቤተ ክርስቲያን
እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ከሰጣቸው ትልልቅ ስጦታዎች መካከል ዋነኛው የንስሓ መንገድ ሲሆን የእግዚአብሔር ቸርነቱ በሰፊው የሚገለጥበት የሕይወት መንገድ ነው። ንስሓ ዘማዊውን ድንግል የምታደርግ ቅድስት መድኃኒት ነች።
እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ከሰጣቸው ትልልቅ ስጦታዎች መካከል ዋነኛው የንስሓ መንገድ ሲሆን የእግዚአብሔር ቸርነቱ በሰፊው የሚገለጥበት የሕይወት መንገድ ነው። ንስሓ ዘማዊውን ድንግል የምታደርግ ቅድስት መድኃኒት ነች።
ውድ አንባብያን! እንደምን ሰነበታችሁ? ከዚህ በፊት የእመቤታችንን የስደቷን ነገር አንሥተን ‹‹ሱላማጢስ ሆይ፥ ተመለሽ፥ ተመለሽ›› በሚል ርእስ ከክፍል አንድ እስከ ሦስት አድርሰናችሁ ነበር፡፡ ጥሩ ትምህርት እንዳገኛችሁበት ተስፋ እናደርጋለን፡፡
የዛሬው ትኩረታችን ያን ሁሉ መከራ የተቀበለችበት የስደቷን ምክንያትና ዓላማ መዳሰስ ነው፡፡
ዘንዶውም ሴቲቱ በወለደች ጊዜ ሕፃንዋን እንዲበላ ልትወልድ ባላት ሴት ፊት ቆመ፡፡ አሕዛብንም ሁሉ በብረት በትር ይገዛቸውም ዘንድ ያለውን ወንድ ልጅ ወለደች፡፡……..ሴቲቱም ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን በዚያ እንዲመግቧት በእግዚአብሔር ተዘጋጅቶላት ወደ ነበረው ስፍራ ወደ በረሃ ሸሸች፡፡ (ራእ.፲፪፥፬-፮
አምላካችን እግዚአብሔር ምስጋናይድረሰውና ለእኛ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ውስጥ ለምንኖር ምእመናን ብንቆጥራቸው ከአሸዋ ይልቅ የሚበዙ ድንቅ ምስክሮችን ጻድቃንን በአማላጅነታቸው እንድንጠቀም አድለውናል፡፡ ከእነዚህ መካከል ጥቅምት ፲፬ ቀን በዓላቸውን የምናከብረው ቅዱስ አባታችን አቡነ አረጋዊ እና ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ይገኙበታል፡፡
ጸሎት ሰው ከልዑል እግዚአብሔር ጋር የሚነጋገራት ናት፤ የተበደለ ደኃ ከንጉሥ እንዲጮኽ ሰው ወደ ልዑል እግዚአብሔር የሚጮሃት ጩኸት ነች። ባለፈው እያመሰገነ፣ ለሚመጣው እየለመነ፣ የእግዚአብሔርን ጌትነቱን እየመሰከረ፣ በደሉን እያመነ እግዚአብሔርንም እራሱንም ደስ የሚያሰኝባት ጩኸት ናት። “ጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር ነው” እንዳሉ ፫፻ ምዕት በጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ የበደለውን ይቅር በለኝ እያለ ለሚጸልይ ሰው ብዙ ሥርዓት አለው።
እሾህ በተባለ ጥንተ አብሶ አዳማዊና ሔዋናዊ ኃጢአት መካከል ያበበች የፍሬ ሕይወት ክርስቶስ መገኛ አማናዊት የሃይማኖት አበባ እመቤታችን በዚህ በአበባው ወቅት (በጽጌ ወራት) መራራው የጣፈጠበት፥ ፍሬ ሕይወት ልጇን እንዳይገሉባት መራራውን የስደት ሕይወት የተጋፈጠችበት መታሰቢያ ወቅት ነው፡፡
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት አላችሁ? ትምህርት እንዴት ነው? በአዲሱ ዓመት ከአሁኑ ጀምራችሁ መምህራን የሚነግሯችሁን በንቃት ሁናችሁ በመከታተል፣ ያልገባችሁን በመጠየቅ ትናንት ከነበራችሁ ዕውቀት ተጨማሪ ዕውቀትን ጥበብን ልትቀስሙ ያስፈልጋል! ቤተ ክርስቲያን በመሄድም መንፈሳዊውን ትምህርት በመማር በሥነ ምግባር ልትታነጹ ያስፈልጋል፡፡
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! አሁን ያለንበት ወቅት ወርኃ ጽጌ ይሰኛል፤ (የአበባ ወቅት ነው)…
በብሥራተ መልአክ በድንግልና ፀንሳ በድንግልና የወለደችውን አንድያ ልጇን ሄሮድስ ሊገድልባት በፈለገው ጊዜ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከሀገር ወደ ሀገር መሰደዷን የሚያመለክተውን፣ ከስደትም እንድትመለስ ጠቢቡ በትንቢት ቀድሞ የተናገረው ይህን ቃል ነው፡፡ ወቅቱ አብዝተን ስለ ስደቷና ተያያዥ ታሪኮች የምንማርበት፣ የምንጸልይበት፣ የምናስተምርበትና የምንዘምርበት ወቅት በመሆኑ በዚህ ርእስ ተከታታይ ጽሑፎችን ለማቅረብ እንሞክራለን፤ ተከታተሉን!
ቀናትን ሁሉ ባርኮ የሰጠን አምላካችን እግዚአብሔር ጊዜ የእርሱ ስጦታ በመሆኑ የከበረ ድንቅ ሥራውን ፈጽሞበታል፡፡ በእያንዳንዱ ዕለት ፍጥረታትን ከመፍጠሩ ባሻገር ለምስጋና፣ ለውዳሴ እና ለድኅነት ያከበራቸው በዓላትም አሉት፤ በእነዚህ ዕለታት ቃል ኪዳን አድርጓል፡፡
ቅዱስ መስቀል ቀስት ከተባለ ጠላታችን ዲያብሎስ እንድናመልጥና ድል እንድናደርገው የተሰጠን ነው፤ ቅዱስ መስቀል መድኅን ዓለም ክርስቶስ ተሰቅሎ በክቡር ደሙ ቀድሶ የሰጠን፣ ሰላማችን የታወጀበት ኃይላችን፣ የሰላም አርማችን ነው!