ሊቀ ዲያቆናትና ቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ

ውድ የእግዚአብሔር ልጆች እንዴት አላችሁልን? ትምህርት እንዴት ነው? መቼም በክረምቱ የዕረፍት ጊዜያችሁ ትምህርት እስኪከፈት በጣም ጓጉታችሁ እንደነበር እናስባለን! ይኸው ተከፈተላችሁ! እንግዲህ በርትታችሁ ከአሁኑ መማር፣ ማጥናት፣ የቤት ሥራን መሥራት፣ ያልገባችሁን መጠየቅ ይገባችኋል፡፡ ገና ነው እያላችሁ እንዳትዘናጉ ጥናቱን አሁኑኑ ጀምሩ! የጨዋታም ሆነ ቴሌቪዥን የምታዩበት ጊዜ ከትምህርታችሁ ጋር በማይጋጭ መልኩ መሆን አለበት፡፡ ከሁሉም ትምህርታችሁን አስቀድሙ! ውድ እግዚአብሔር ልጆች! ለዛሬ ያዘጋጀንላችሁ የሊቀ ዲያቆናትና የቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስን ታሪክ ነው፡፡

ቅድስት አርሴማ

ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! ለከበረው ጤንነታችሁ እንዴት አላችሁ! የክረምት ወቅት አልፎ አዲሱን ዓመት ተቀብለናልና ለዚህ ያደረሰንን ፈጣሪያችንን ማመስገን ይገባል! ልጆች! መስቀል በዓል እንዴት ነበር? በሰላም በፍቅር አከበራችሁ አይደል? የእኛን ምክርም ተቀብላችሁ ለመጪው የትምህርት ዘመን ዝግጅት ስታደርጉ እንደቆያችሁ ደግሞ ተስፋችን ነው፡፡ አሁን ደግሞ ትምህርት ስለጀመራችሁ በርትታችሁ መማርን እንዳትዘንጉ! ከአሁኑ ጀምራችሁ መምህራን የሚነግሯችሁን በንቃት ተከታተሉ፤ መጻሕፍትን አንብቡ፤ ያልገባችሁን ጠይቁ፤ የቤት ሥራችሁን በአግባቡ ሥሩ፤ የጨዋታ ጊዜያችሁንና ቴሌቪዥን የምታዩበትን ጊዜ መቀነስ አለባችሁ፤ አሁን የእናንተ ተግባር፣ እይታ፣ ሥራ፣ ጉዳይ ሁሉ ትምህርት እና ትምህርት ብቻ ስለሆነ ጎበዝ ተማሪዎች ሁኑ፤ መልካም!

ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! ለዛሬ ያዘጋጀንላችሁ ታሪክ የቅድስት አርሴማን ነው፤

የጽጌ ወር

ምድር በአበቦችና በዕፅዋቶች ተሞልታ የምታሸበርቅበት ወቅት የጽጌ ወር በክርስቲያናዊ ሕይወታችን ውስጥ ትልቅ ትርጉም አለው፡፡ የመዳኛችን ተስፋ የሆነችውና የዓለምን ቤዛ የወለደችን ቅድስት ድንግል ማርያም አበባውን በሚያስገኙት ዕፀዋትና በምድር፣ የተወደደ ልጇ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ በአበባው እንደሚመሰሉ ቀደምት ነቢያት አስተምረውናል፡፡

ጉባኤ ኒቅያ

ጉባኤ ኒቅያ ቤተ ክርስቲያን አንድነቷን የጠበቀችበት፣ አርዮስና አርዮሳውያን የተወገዙበት፣ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት፣ አዳኝነት፣ ጌትነት፣ መድኃኒትነት የተመሠከረበት፣ ኦርቶዶክስ የሚለው ስም ትምክህት የሆነበት ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ይህን ጉባኤ ትቀበላለች፤ ትልቅም ስፍራ አላት፡፡

ቅዱስ መስቀል

ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት አላችሁ? እንኳን ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ አሸጋግሮ በሰላም ለዚህ ዕለት አደረሳችሁ! ዕንቁጣጣሽ እንዴት አለፈ? መቼም ደስ ብሏችሁ እንዳሳለፋችሁ ተስፋችን እሙን ነው፡።  መልካም! የአዲስ ዓመት ትምህርት ለመጀመር እንዴት እየተዘጋጃችሁ ነው? ባለፈው ዓመት በትምህርታችን ደከም ያለ ውጤት አስመዝግበን የነበርን ዘንድሮ በርትተን በመማር በጥሩ ውጤት ከክፍል ክፍል ለመሻገር ከአሁኑ ማቀድና መበርታት አለብን፡፡ እንዲሁም ደግሞ ለአገርና ለቤተ ክርስቲያን እየጸለይን የሰላምን ዘመን ተስፋ እናድርግ! መልካም!

ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! ባለፉት ጊዜያት ለእናንተ ያስተምራሉ በማለት በጻፍንላችሁ በርካታ ቁም ነገሮችን ስንማማር እንደነበር ታስታውሳላችሁ አይደል? አሁን ደግሞ ስለ ቅዱስ መስቀሉ በዓል ጥቂት ልናካፍላችሁ ወደድን፤ መልካም ቆይታ!

ምሕረት ሥጋዊና ምሕረት መንፈሳዊ

የምሕረት አምላክ ቸሩ ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ኃጢአት በደላችንን ሁሉ ታግሦ እንደ ሥራችን ሳይሆን እንደ ቸርነቱ ለአዲሱ ዓመት አበቃን፡፡ ዕድሜ ለንስሓ ዘመን ለፍስሐ ያደለን አምላካችን በሰጠን የተፈጥሮ ጸጋ ተጠቅመን ከክፉ መንገዳችን እንድመልስ፣ ከኃጢአት እንድንነጻ እንዲሁም በጎ ሥራ እንድሠራ ነው፡፡ ምሕረቱ የበዛ ቁጣውም የራቀ ቸርነቱ አያልቅምና በእርሱ ጥላ ሥር ተጠልለን በሥነ ምግባር እንድንኖር መልካም ፈቃዱ ሆነ፡፡ ይህንንም በቅዱሳን ልጆቹ ላይ ፈጽሞ አሳይቶናል፡፡ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ክርስቲያን የተባልን በሙሉም ምሕረትን ስለማድረግ ልናውቅ ያገባናል፡፡ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ምሕረት በሁለት እንድሚከፈል ያስተምሩናል፤ እነርሱም ምሕረት ሥጋዊና ምሕረት መንፈሳዊ ናቸው፡፡

ርእሰ ዐውደ ዓመት

አምላካችን እግዚአብሔር ዕድሜ ለንስሓ ዘመን ለፍስሐ የሰጠን መልካም እንድንሠራበት ነውና በመጪው ዘመን የትላንት ስሕተታችንን አርመን፣ የተጣላን ታርቀን፣ የበደልን ክሰን፣ ያለው ለሌለው እያካፈለ ለመኖር ማቀድ ይገባናል!

የጳጉሜን ወር

በዓመት ውስጥ ካሉት ወራት የተለየች፣ ቀኖቿም ጥቂት እንዲሁም አጭር በመሆኗ የጳጉሜን ወር ተናፋቂ ያደርጋታል፡፡ እግዚአብሔር አምላካችን ለሀገራችን ኢትዮጵያ ካደላት ስጦታ አንዷ የሆነችውም ይህች ወር በዘመነ ዮሐንስ ስድስት ቀናት እንዲሁም ደግሞ በዘመነ ማርቆስ፣ በዘመነ ሉቃስና በዘመነ በማቴዎስ አምስት ቀናት ብቻ አላት፡፡ በቤተ ክርስቲያናችን አስትምህሮ የጳጉሜን ወር የዓመት ተጨማሪ ወር እንላታለን፡፡  ምዕራባዊያኑ ግን ተጨማሪ ቀን እንደሆነች በማሰብ በዓመቱ ባሉ ወራት ከፋፍለዋታል፡፡

ጳጉሜን የሚለው ስያሜ “ኤፓጉሜኔ” ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም “ጭማሪ” ማለት ነው፡፡ በግእዝ “ወሰከ-ጨመረ” ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ተውሳክ (ተጨማሪ) ማለት ነው፡፡ (አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፤ መዝገበ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገብ ቃላት፤ ገጽ ፱፻፭)

ጌቴሴማኒ

ሥርወ ቃሉ ከዕብራይስጥ ቋንቋ የሆነው ጌቴሴማኒ “ጋት እና ስሜኒ” ከሚሉ ከሁለት ጥምር ቃላት የተገኘ ነው፡፡ ትርጉሙም “የዘይት መጭመቂያ”  ማለት ነው፡፡ ጌቴሴማንኒ የአትክልት ቦታ ዙሪያውን በወይራ ዛፎች የተከበበ ነው፡፡…ይህም ስፍራ አምላካችን እግዚአብሔር ፍርዱን የሚያደረግበት እንደሆነ ይታመናል፡፡

ትዕግሥተኛዋ እናት ቅድስት እንባመሪና

ውድ የእግዚአብሔር ልጆች!  ለከበረው ጤንነታችሁ እንዴት አላችሁ? የጾምን ወቅት እንዴት እያሳለፋችሁት ነው? አባቶቻችን ሊቃውንት ስለ ጾም እንዲህ ይላሉ፤ ጾም ማለት ከምግብና ከውኃ መከልከል ብቻ ሳይሆን ከክፉ ሥራም መታቀብ (መከልከል) ነው፤ ጾም የጽድቅ በር ናት፣ ጾም ለመልካም ነገር የምታነሣሣን ናት፤ ውድ እግዚአብሔር ልጆች! ስንጾም ከጸሎትና  ከስግደት ጋር፣ ቤተ ክርስቲያን በመሄድ በማስቀደስ ፣ታዛዦች በመሆን የጾሙን ጊዜ ልናሳልፍ ይገባል፡፡ መልካም!

ውድ እግዚአብሔር ልጆች! ለዛሬ ያዘጋጀንላችሁ ታሪክ የቅድስት እንባመሪናን ነው፡፡