“ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስን ልከተለው እሄዳለሁ” (መጽሐፈ ስንክሳር)

አምላካችን እግዚአብሔር ምስጋናይድረሰውና ለእኛ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ውስጥ ለምንኖር ምእመናን ብንቆጥራቸው ከአሸዋ ይልቅ የሚበዙ ድንቅ ምስክሮችን ጻድቃንን በአማላጅነታቸው እንድንጠቀም አድለውናል፡፡ ከእነዚህ መካከል ጥቅምት ፲፬ ቀን በዓላቸውን የምናከብረው ቅዱስ አባታችን አቡነ አረጋዊ እና ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ይገኙበታል፡፡

የምእመናን ድርሻ በቤተ ክርስቲያን

ጸሎት ሰው ከልዑል እግዚአብሔር ጋር የሚነጋገራት ናት፤ የተበደለ ደኃ ከንጉሥ እንዲጮኽ ሰው ወደ ልዑል እግዚአብሔር የሚጮሃት ጩኸት ነች። ባለፈው እያመሰገነ፣ ለሚመጣው እየለመነ፣ የእግዚአብሔርን ጌትነቱን እየመሰከረ፣ በደሉን እያመነ እግዚአብሔርንም እራሱንም ደስ የሚያሰኝባት ጩኸት ናት። “ጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር ነው” እንዳሉ ፫፻ ምዕት በጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምኖ የበደለውን ይቅር በለኝ እያለ ለሚጸልይ ሰው ብዙ ሥርዓት አለው።

‹‹ሱላማጢስ ሆይ፥ ተመለሺ፥ ተመለሺ›› (መሓልየ መሓልይ ዘሰሎሞን ፯፥፩)

 እሾህ በተባለ ጥንተ አብሶ አዳማዊና ሔዋናዊ ኃጢአት መካከል ያበበች የፍሬ ሕይወት ክርስቶስ መገኛ አማናዊት የሃይማኖት አበባ እመቤታችን በዚህ በአበባው ወቅት (በጽጌ ወራት) መራራው የጣፈጠበት፥ ፍሬ ሕይወት ልጇን እንዳይገሉባት መራራውን የስደት ሕይወት የተጋፈጠችበት መታሰቢያ ወቅት ነው፡፡

ሥርዓተ ጾም

ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት አላችሁ? ትምህርት እንዴት ነው? በአዲሱ ዓመት ከአሁኑ ጀምራችሁ መምህራን የሚነግሯችሁን በንቃት ሁናችሁ በመከታተል፣ ያልገባችሁን በመጠየቅ ትናንት ከነበራችሁ ዕውቀት ተጨማሪ ዕውቀትን ጥበብን ልትቀስሙ ያስፈልጋል! ቤተ ክርስቲያን በመሄድም መንፈሳዊውን ትምህርት በመማር በሥነ ምግባር ልትታነጹ ያስፈልጋል፡፡

ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! አሁን ያለንበት ወቅት ወርኃ ጽጌ ይሰኛል፤ (የአበባ ወቅት ነው)…

‹‹ሱላማጢስ ሆይ፥ ተመለሺ፥ ተመለሺ›› (መሓልየ መሓልይ ዘሰሎሞን ፯፥፩)

በብሥራተ መልአክ በድንግልና ፀንሳ በድንግልና የወለደችውን አንድያ ልጇን ሄሮድስ ሊገድልባት በፈለገው ጊዜ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከሀገር ወደ ሀገር መሰደዷን የሚያመለክተውን፣  ከስደትም እንድትመለስ ጠቢቡ በትንቢት ቀድሞ የተናገረው ይህን ቃል ነው፡፡ ወቅቱ አብዝተን ስለ ስደቷና ተያያዥ ታሪኮች የምንማርበት፣ የምንጸልይበት፣ የምናስተምርበትና የምንዘምርበት ወቅት በመሆኑ በዚህ ርእስ ተከታታይ ጽሑፎችን ለማቅረብ እንሞክራለን፤ ተከታተሉን!

‹‹በደስታ በዓልን አድርጉ›› (መዝ.፻፲፯፥፳፯)

ቀናትን ሁሉ ባርኮ የሰጠን አምላካችን እግዚአብሔር ጊዜ የእርሱ ስጦታ በመሆኑ የከበረ ድንቅ ሥራውን ፈጽሞበታል፡፡ በእያንዳንዱ ዕለት ፍጥረታትን ከመፍጠሩ ባሻገር ለምስጋና፣ ለውዳሴ እና ለድኅነት ያከበራቸው በዓላትም አሉት፤ በእነዚህ ዕለታት ቃል ኪዳን አድርጓል፡፡

ቅዱስ መስቀል

ቅዱስ መስቀል ቀስት ከተባለ ጠላታችን ዲያብሎስ እንድናመልጥና ድል እንድናደርገው የተሰጠን ነው፤ ቅዱስ መስቀል መድኅን ዓለም ክርስቶስ ተሰቅሎ በክቡር ደሙ ቀድሶ የሰጠን፣  ሰላማችን የታወጀበት ኃይላችን፣ የሰላም አርማችን ነው!

ርእሰ ዐውደ ዓመት

የዘመናት አስገኝ፣ የፍጥረታት ባለቤት፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ ዓመታትን በቸርነቱ የሚያፈራርቅ፣ ከዘመነ ሉቃስ ወደ ዘመነ ዮሐንስ  በቸርነቱ አሻግሮናልና ክብርና ምስጋና ለእርሱ ይሁን!

በዓለ ቅዱስ ሩፋኤል

በዓለ ቅዱስ ሩፋኤል በጳጉሜን ሦስት ቀን የሚዘከር በዓል ነው፡፡ “ሩፋኤል” የሚለው ስያሜ ትርጉም “ደስ የሚያሰኝ፣ ቸር፣ መሐሪ፣ ቅን የዋህ” ማለት ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ከዕብራይስጥ ሁለት ቃላት ጥምረት የተገኘ ቃል ነው፡፡ “ሩፋ” ማለት ጤና፣ ፈውስ፣ መድኃኒት ማለት ሲሆን “ኤል” ሚለው በሌሎቹም መላእክት ስም ላይ የሚቀጸል ስመ አምላክ ነው::

“ተዘጋጅታችሁ ኑሩ’’ (ማቴ.፳፬፥፵፬)

ጌታች አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱሳን ደቀ መዛሙርቱ የነገራችው ኃይለ ነው፤ ‘’ጌታችሁ በምን ሰዓት እንደሚመጣ አታውቁምና እንግዲህ ንቁ፤ እወቁ ባለቤት ሌሊት ሌባ በየትኛው ጊዜ እንደሚመጣ ቢያውቅ ኖሮ በነቃ፤ ቤቱንም እንዲቆፈር ባልተወ ነበር’’ አላቸው፡፡ ስለዚህ እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፤ የሰው ልጅ በማታስቡት ሰዓት ይመጣልና፤