የጂንካ ማእከል የመጀመሪያውን የሐዊረ ሕይወት ጉዞ ወደ ስብከት ኬላ አደረገ
ጂንካ ማእከል
በጂንካ ማእከል በማኅበረ ቅዱሳን ጂንካ ማእከል የመጀመሪያውን የሐዊረ ሕይወት ጉዞውን በደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት፣ በበና ጸማይ ወረዳ፣ ጫሊ ቅድስት ሥላሴ ስብከት ኬላ ታኅሣሥ 17 ቀን 2008 ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ ተካሄደ፡፡በጉዞው ላይ የደቡብ ኦሞ ሀ/ስብከት የመምሪያ ሓላፊዎች፣ የጂንካ ከተማ ገዳም፣ አስተዳደርና የአቢያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪዎች እንዲሁም ከአዲስ አበባ የመጡ ተጋባዥ እንግዶች፣ ሰባኬ ወንጌልና ዘማሪያን በአጠቃላይ 1000 ምእመናን ተሳትፈዋል፡፡
ጉዞው ቤተ ክርስቲያን ባልታነፀበት የስብከት ኬላ እና ሁልጊዜም “አጥምቁን እና ቤተ ክርስቲያን ሥሩልን” ወደሚሉት አርብቶ አደር ወገኖቻችን ጋር መደረጉ ከሌሎች ማእከላት ልዩ ያደርገዋል ተብሏል፡፡
ጉዞው ታኅሣሥ 17 ቀን 2008 ዓ.ም ጠዋት 12፡30 ላይ በቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ምእመናን በተገኙበት በአንቀጸ ብፁዓን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም አበምኔት ቆሞስ መ/ር አባ ኤፍሬም ፈቃዴ በጸሎት የተከፈተ ሲሆን በአስተባባሪዎች አማካኝነት ሁሉም ምእመናን ወደተዘጋጀላቸው መኪና ከገቡ በኋላ ጉዞው ተጀመረ፡፡ በጉዞው ላይ በአስተባባሪዎች አማካኝነት በክርስትና ሕይወት ዙሪያ ውይይት እየተደረገ መዝሙር እየተዘመረ እና ከተጓዦች ጥያቄ እየተሰበሰበ የጉዞው ቦታ ላይ ተደርሷል፡፡ በቦታውም ያሉ አርብቶ አደር ምእመናን “ሁሌም አጥምቁን ቤተ ክርስቲያን ሥሩልን” የሚሉን በርካታ ምእመናን በቋንቋቸው በዝማሬ ተጓዦችን ተቀብለዋል፡፡
የጧዋቱ መርሐ ግብር በካህናት ጸሎተ ወንጌል የተከፈተ ሲሆን ትምህርትም በመምህራን ወንጌል ተሰጥቷል ፡፡ከሰዓት በኋላ ከጂንካ አጥቢያ በተገኙ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በቆሞስ መ/ር አባ ኤፍሬም ፈቃዴ የአንቀጸ ብፁዓን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም አበምኔት ከሕዝብ የተነሳውን ጥያቄዎችን፣ ሊቀ ብርሃናት ኤልያስ ዘውዴ በቤተ ክርስቲያን የምእመናን ድርሻ ምንድነው? መሪጌታ ዘመልአክ የበዓታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ የልጆች አስተዳደግ ምን መምሰል አለበት? በሚል ርእስ ለምእመናን በቂ መልስ የሰጡ ሲሆን፣ በጉባኤው ላይ የተገኙት ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ስዩም ደግሞ ስለ ቅዱስ ጋብቻ እና የንስሐ ሕይወት ዙሪያ ከአባታዊ ምክር ና ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ÃÃÃÃÂ ስለ ጫሊ ስብከት ኬላ አመሠራረትና አሁን ስላለው የአገልግሎት እንቅስቃሴ እና ስለ ቀጣዩ ዕቅዳቸው በጥያቄና መልስ የተብራራ ሲሆን፤ ስብከት ኬላውም ጳጉሜ 3 በ1999 ዓ/ም በአቡነ ዕንባቆም እንደተባረከ ተገልጧል፡፡
በመጨረሻም የጂንካ ማዕከል ሰብሳቢ አቶ ዘላለም ጌታቸው አጠቃላይ መልእክት፣ ማሳሰቢያና ለስብከት ኬላው ገቢ በማሰባሰብ እና በጉዞው አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት ምስጋና በማቅረብ በጂንካ ደብረ ቀራኒዮ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ አማካኝነት በጸሎት ተዘግቶ የመርሐ ግብሩ ፍጻሜ ሆኗል፡፡ ከተጓዦች መካከል እንግዶች በሰጡት አስተያየት ጉዞው ቢደገምና ሌሎችም እንዲህ ዓይነቱን ዝግጅት ቢካፈሉ ጠቀሜታው የጎላ ነው ብለዋል፡፡ ማኅበሩም የአገልግሎት ማኅበር መሆኑን ተገንዝበናል ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡




በሌላ መልኩ የአርባ ምንጭ ማዕከል የበገና ተማሪዎች ነፍስን በሚያለመልም ዝማሬ እግዚአብሔርን ያመሰገኑ ሲሆን፤ በ2007 ዓ/ም በጋሞ ጎፋ ሀ/ስብከት፣ በኮንሶ ወረዳ ቤተ ክህነትና በማኅበረ ቅዱሳን ትብብር ተጠምቀው የመንፈስ ቅዱስን ልጅነት ያገኙት የጉኛራና ኮልሜ አዳዲስ ተጠማቂያን በተጋባዥ እንግዳነት መርሐ-ግብሩን ተሳትፈዋል፡፡ እንግዶቹም ከተቋቋመ አንድ ዓመት እንኳን ያልሞላው የሰንበት ት/ቤት በኮንስኛና በአማርኛ መዝሙር በማቅረብ እግዚአብሔርን አመስግነዋል፡፡ በተያያዢነት ተጓዡ ምዕመን የደብሩን አጸደ ሕጻናት ትምህርት ቤት የመናፍቃን ጫና እና የዐቅም ውስንነት ለመቅረፍ ከ7000 ብር በላይ ሰብስቦ በዕለቱ ድጋፍ አድርጓል፡፡ በመጨረሻም ምእመኑ ይህ መሰሉ የሕይወት ጉዞ በተደጋጋሚ ወደተለያዩ ቅዱሳት መካናት መዘጋጀት እንዳለበትና ምአመኑም በሚችለው ሁሉ ከማኅበሩ ጋር አብሮ ለመሥራት ተነሳሽነቱን አሳይቷል፡፡ በመሆኑም 3ኛው ሐዊረ ሕይወት እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በዚሁ ዓመት ወርኃ ሚያዝያ ውስጥ ወደ ዶርዜ ቅ/ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን እንደሚደረግ የጉዞ ኮሚቴው አስታውቋል፡፡ 


በዓመት ሁለት ጊዜ የሚካሄደው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጥቅምት 11 ቀን 2008 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በጸሎት ተጀመረ፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን በኢቢኤስ ቴሌቪዥን እንዲሁም በሬድዮ አያሰራጨ የሚገኘውን መንፈሳዊ መርሐ ግብር በአውሮፓም ምእመናን ባሉበት ሆነው በቀላሉ በስልክ ሥርጭቱን መከታተል እንዲችሉ ማድረጉን የአውሮፓ ማእከል አስታወቀ፡፡