የሐዋሳ ጉዳይ 1
ባለፉት ጥቂት ወራት በሐዋሳ ከተማ፥ በተለይም ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በርካታ ችግሮች ሲከሰቱ ቆይተዋል። ያለውን ሁኔታ በተመለከተ ወደ ሐዋሳ የተጓዘው ሪፖርተራችን ተሥፋሥላሴ የሀገረ ስብከቱን ሥራ አስኪያጅ፥ የሐዋሳ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪንና ምእመናንን አናግሮ ዘገባ አጠናቅሯል። - ብፁዕ አቡነ ገብርኤልም ሆነ እርስዎ ከመጣችሁ ጥቂት ጊዜያት ቢሆንም፥ በሀገረ ስብከቱ ያሉ እንቅስቃሴዎች፣ በጎ ነገሮችና ፈተናዎች ካሉ ቢገልጹልን?
እኔም ሆንኩ የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ተመድበን ከመጣን ወደ 3 ወር የሚጠጋ ጊዜ ብቻ አስቆጥረናል፡፡ እኛ ከመምጣታችን በፊት በቦታው ላይ አንዳንድ አለመግባባቶችና ችግሮች ነበሩ፡፡ እነዚህ ችግሮች እንዳሉ ነው እኛ የመጣነው፡፡ ቢሆንም ከመጣንበት ጊዜ ጀምሮ አብዛኛውን የማረጋጋት፣ የመምከር፣ የቤተ ክርስቲያኒቱን ደንብ፣ መመሪያ፣ ሥርዓትና ሕጉን የማሳወቅ፣ ሰዎች ሁሉ ወደ በጎና ወደ ቀና አስተሳሰብ እንዲመጡ የመመለስ፣ ያልተረዱት ነገር ካለ እንዲረዱ ያላወቁት ካለ እንዲያውቁ፤ አጠቃላይ የቤተክርስቲያኒቱን ሥርዓትና ሕግ በተከተለ መልኩ መንገዶችን የማሳየት፣ የማስተካከል፣ ይሄኛው ያስኬዳል፣ ይሄኛው አያስኬድም በማለት እየነገርንና እያስተካከልን ነው የቆየነው። ችግሮቹ ምን እንደሆኑ፥ አነሣሣቸው ምን አንደሆነ በውል ባናውቀውም ከኛ በፊት አለመግባባቶች ነበሩ፡፡ አሁን ደግሞ ከመጣንበት ጊዜ ጀምሮ ሽማግሌዎችን ካህናትን፣ ማኅበረ ምዕመናንንና፣ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ወጣቶችንና የሚመለከታቸውን አካላት በማነጋገር በተቻለ መልኩ ችግሮች በሰላም፥ በውይይትና በመግባባት የሚፈቱበትን የተቻለውን ያህል ብዙ ጥረት አድርገናል። ከዚህም በኋላ የሀገር ሽማግሌዎችም እንዲሁ ሃሳቡን እንዲያግዙንና ድጋፍ እንዲያደርጉልን አድርገን፤ እነርሱም የሚቻላቸውን በትብብር መልክ ሰርተዋል፡፡ የመንግሥት አካላትም ጭምር በእውነት ለቤተ ክርስቲያናችን በሚያስፈልገው በማንኛውም መልኩ ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጀምሮ በተለያዩ በፀጥታ፣ በፖሊስ፣ በደህንነት በቀበሌም በማንኛውም ሕዝባውያንና መንግስታውያን ድርጅቶች የሚገኙ፥ ቤተክርስቲያኒቷ ሕጓ፣ ሥርዓቷ፣ ደንቧ ተጠብቆ በአግባቡ ሥራዋን እንድታከናውን፤ ከቅዱስ ሲኖዶስ በሚተላለፈው መመሪያና ውሳኔ መሠረት፥ ማንኛውም ሥራ መመሪያና ደምቡ ተጠብቆ እንዲሠራ፣ ሁሉም የሚቻላቸውን ከፍተኛ ድጋፍን እገዛ እያደረጉልን ይገኛሉ፡፡ በዚህ አይነት ነው ሥራዎችን እየሠራንም እያስተካከልን የቆየነው፡፡ እንግዲህ ከቆየታው ማነስ የተነሣ /ከመጣን አጭር ጊዜ ቢሆንም/ በተቻለ መልኩ ችግሩን ከማስወገድ አንፃር ሥራዎችን በተዋረድ እያከናወንን ነው፡፡ ከዚሁ ጎን ለጎን ደግሞ ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር በመተባበር ወደየ ወረዳዎቹ እንቅስቄሴ በማድረግ ለየወረዳዎቹ ሊቃነ ካህናትና ለየወረዳዎቹ ቤተክህነት ኃላፊዎች እንደሁም ለርዕሰ ከተማዋ /ሐዋሳ/ አድባራት አስተዳዳሪዎች ሰባክያነ ወንጌል፣ የሰበካ ጉባኤ ሊቃነ መናብርት፣ ምክትል ሊቃነ መናብርት እንዲሁም ጸሐፊዎች በሁለቱም የብፁዕነታችን ሀገረ ስብከቶች ለሚገኙት፣ ሰበካ ጉባኤን ለማጠናከር፤ ሰንበት ትምህርት ቤትን ለማደራጀት፣ ስብከተ ወንጌልን ለማስፋፋት፣ የአሥራት በኩራትና የሰበካ ጉባኤ ክፍያዎችን ለማጠናከር በብፁዕነታቸው መሪነት የ3 ቀናት ሴሚናር አካሂደናል፡፡
- ከመጣችሁ በኋላ ችግሮችን በመፍታት እንዳሳለፋችሁ ገልጸዋል፡፡ የችግሮቹ አካሄድና አፈጣጠር ምን እንደሆነ ሊነግሩን ይችላሉ?
ክርስትያናትና 13 የወረዳ ቤተ ክህነቶች ይገኛሉ፡፡ በሌሎቹ አብያት ክርስቲያናት ምንም ዓይነት የተለየ ችግር አላጋጠመንም አልፎ አልፎ አንዳንድ ቦታዎች ቢታዩም ይሄን ያህል አይደሉም፡፡ ትልቁና ከፍተኛው ችግር አልፎ አልፎ እየተነሣ ያለው በመንበረ ጵጵስናው ርዕሰ ከተማ በሚገኘው ደብረ ምህረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ነው፡፡ ውሳኔዎች፣ መመሪያዎች፣ ሰርኩላሮች ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ወደ ሃገረ ስብከቱ በተዋረድ ይመጣሉ፤ ተወረዱንም ጠብቆ ወደ አድባራትና ገዳማት ይወርዳሉ፡፡ በደብረ ምህረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም አስተዳዳሪና ሰበካ ጉባኤ በኩል ግን መመሪያን የመፈጸምና የማስፈጸም፥ የቃለ አዋዲውን ሕግ የመጠበቅና የማስጠበቅ፤ በአጠቃላይ ግቢውን ከሁከትና አላስፈላጊ ከሆነ ነገሮች ሁሉ የመጠበቅና የማስጠበቅ ጉዳይ የሰበካ ጉባኤ ጉዳይ ሆኖ ሳለ አባላቱና የደብሩ አስተዳዳሪ ኃላፊነታቸውን ባለመወጣታቸው ምክንያት ነው ይሄ ሁሉ ችግር እየተፈጠረ ያለው። ይሄንንም ችግር እንዲፈቱ ለአስተዳዳሪው በብጹዕነታቸው ከአንድም ሁለት ሦስቴ መመሪያ ተሰጥቷል፡፡ የሰበካ ጉባኤውንም በጋራ አሰባስበን የአቅማቸውን ቃለ ዐዋዲውን ጠብቀው እንዲሠሩ፥ ከአቅም በላይ የሆነ ነገር ሲገኝ ደግሞ ለሃገረ ስብከቱና ለመንግሥት አካላት አቅርበው እንዲያስከብሩ፣ ግቢውን እንዲያስጠብቁ፤ ተደጋጋሚ ውይይቶች የጽሑፍም ሆነ የቃል መመሪያዎች ተሰጥተዋል፤ ነገር ግን ተፈጻሚነት ሳያገኙ እየቀሩ፥ በቸልታ እየታለፈ ችግሩ ወደ አለመወገድና መድረኩ በተለያየ ጊዜ የጭቅጭቅ መድረክ እንዲሆን አድርጎታል፡፡
ከፍተኛው ይሄ ችግር የሚታየው የገዳሙ ሰንበት ት/ቤት ወጣቶች ነን በሚሉት በኩል ነው፡፡ በካህናቱም፣ በማኅበረ ምዕመናኑንም በመላው ሐዋሳ ከተማ በሚገኙ ምዕመናን በእውነት ለቤተ ክርስቲያናቸው የሚያስፈለገውን የሚያደርጉ፣ የሚታዘዙትን የሚፈጽሙ፣ ቅንነት የዋህነት ያላቸው፣ ሃይማኖታቸውን ጠብቀው ይዘው ለቤተ ክርስቲያናቸው አስፈላጊውን ሁሉ የሚፈጽሙ ናቸው፡፡ እንደ ቃለ ዓዋዲው በሰንበት ትምህርት ቤት የሚታቀፉት ከ4 ዓመት እስከ 3ዐ ዓመት ያሉ ናቸው። ነገር ግን በቅዱስ ገብርኤል ሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ የ4ዐ ዓመት የ5ዐ ዓመት ትልልቅ ሰዎች ሁሉ አሉ የእድሜ ገደቡም የሚመለከታቸው አይደለም። ይሄ የሚያሳየው ድርሻቸውን ለይተው አለማወቃቸው ነው ከ3ዐ ዓመት በኋላ ወደ ማኅበረ ምዕመናን ነው መቀላቀል ያለባቸው፡፡ ይህን ማድረግም የሰበካ ጉባኤው የሥራ ድርሻ ነበር፡፡ ሰንበት ትምህርት ቤት በቤተ ክርስቲያን ሊቋቋሙ ከሚገባቸው ከ13 ንዑሳን ክፍሎች ውስጥ አንድ ነው ይሄንን መፈጸም የሰበካ ጉባኤው ድርሻ ነው እኛ ከመምጣታችን በፊት እኛ ከመጣንም በኋላ ተቀላቅለው አንድ ዓይነት ትምህርት ነበር የሚሰጣቸው፡፡ ስለዚህ ድርሻዎችን የመለየት፣ መመሪያዎችን የማወቅና ነገሮችን በቅንነት የመመልከት ሁኔታው የለም፡፡
በሌላ በኩል በቅዱስ ሲኖዶስ ተወስኖ በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደሪጃ መምሪያ በኩል የሚፈጸም መመሪያ አለ፡፡ ያንን ተከትሎ መሄድ ቢቻል ምንም ዓይነት ችግር አይኖርም፡፡ ነገር ግን ሰንበት ትምህርት ቤት ነን ይላሉ ዕድሜአቸው ከጣሪያ በላይ የሆኑ በውስጣቸው አሉ፡፡ እነዚያው ክፍሎች ደግሞ የገዳሙን አውደ ምህረት ይዘን እኛ ነን መስበክ ያለብን ይላሉ፡፡ ለመስበክ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ዶግማ ሥርዓት ቀኖና መማር ከሊቃውንት እግር ሥር ቁጭ ብሎ መጻሕፍትን መመርመር ይገባል፤ ይህ ባልሆነበት ሁኔታ እናስተምራለን እንሰብካለን ማለቱ ደግሞ ወደ ስህተት ትምህርት ይወስዳል፡፡ በአሁኑ ወቅት ደግሞ ሰባክያነ ወንጌል ነን፣ ዘማርያን ነን፣ ባሕታውያን ነን፣ እናጠምቃለን እንዲህ እናደርጋለን የሚሉትንና የመሳሰሉትን በሚመለከት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በ2001ዓ.ም የካቲት ወር ያሳለፈውና ለመላው ስብከት ያስተላለፈው ሰርኩላር አለ፡፡ በዚያ ሰርኩላር ላይ ከመንበረ ፓትርያሪኩ ጠቅላይ ጽ/ቤት ወይም ከሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ፈቃድ ያልተሰጠው ማንም ሰው መስበክ አይችልም፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ በቅዱስ ሲኖዶስ የምትመራና ከቅዱስ ሲኖዶስ እስከ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ድረስ የራሷ የሆነ አስተዳደራዊ መዋቅር ያላት በመሆኗ፥ በዚያው በመዋቅር ውስጥ ተካቶ ሕጋዊ እውቅና ኖሮት፥ በየሃገረ ስብከቱ ያለውም የየሃገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስና የሃገረ ስብከቱ ጽ/ቤት አሊያም ጠቅላይ ቤተ ክህነትም የስብከተ ወንጌል ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያው አውቆት በዚህ አይነት ነው መስበክ ያለበት ይላል መመሪያው። ይሄ መመሪያ የተላለፈው በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቃነ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ፕሬዚዳንትና የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዚዳንት ክቡር ፊርማ ተፈርሞ ነው፡፡ እኛ ደግሞ እንደ ሀገረ ስብከት በቅዱስ ሲኖዶስና ከብፁዕ ወቅዱስ አባታችን የሚሰጠውን መመሪያ የመፈፀም የማስፈጸም ኃላፊነት፣ የቤተክርስቲያን ልጅነትና አደራ አለብን፡፡
እንደ ሀገረ ስብከት ግን እገሌ ይስበክ እገሌ አይሰበክ የሚል አመለካከት የለንም፡፡ በአንዳንድ አካላት ግን እንደዚህ አይነት ሰባክያን ካልመጡልን እንደዚህ ዓይነት መምህራን ካልመጡልን የሚል የግል ጥያቃቄዎች ይነሳሉ፤ ሃሳቦቹ ለምን ኖሩ አንልም፡፡ ነገር ግን ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የሚያሰማራቸው፣ የሚቆጣጠራቸው፣ አንድ ጥፋት ቢያጠፉ ሊጠይቃቸው የሚችል ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ጀምሮ እስከ ገጠሪቱ ቤተ ክርስቲያን ድረስ በቤተ ክርስቲያኒቱ የአስተዳደርን የሥራ መዋቅር ውስጥ የተካተቱ ሊሆን ይገባል፡፡ ደግሞም በርካታ ሠራተኞችና ሊቃውንት አሏት፡፡
እናስተምራለን ለሚሉ ግን ለጠቅላይ ቤተ ክህነት ወይም ለሃገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ መጠየቂያ ቀርቦ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ ጉዳዩን መርምሮና አጣርቶ፥ ይህ ሰው ብቁ ነው ብቁ አይደለም፥ ለማስተማር አስፈላጊውን የትምህርት ሆኔታ ይዟል አልያዘም፥ የሚለውን ሁሉ አይቶ ሲያሰማራ /ሲፈቀድ/ ሊሆን ይችላል፡፡
ለምሳሌ አንድ ሰው በራሱ ተነሳሽነት ተነስቶ ወይ ባሕታዊ ነኝ ወይም ሰባኪ ነኝ ብሎ አንድ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ላይ እሰብካለሁ ቢል፡-
1. የደብሩ አስተዳዳሪ ወይም ሰበካ ጉባኤ አያውቁም፣ የወረዳው ቤተ ክህነት፣ ሀገረ ስብከትና ጠቅላይ ቤተክህነቱም አያውቁም
2. እዚያ ቦታ በአጋጣሚ ሆኖ /እግዚአብሔር አያድርስና/ ችግር ቢፈጠር፡፡ ጠቅላይ ቤተክህነቱም ሀገረ ስብከቱን መጠየቁ አይቀርም ሀገረ ስብከቱም የደብሩን ተጠሪ መጠየቁ አይቀርም፡፡ ስለዚህ እንደኃላፊነት ሀገረ ስብከቱ እያወቀው መሆን አለበት፡፡ ምዕመናንም ምን አልባት የስሕተት ትምህርት እየተላለፈ እንደሆነ፣ ቃለ ዐዋዲውም እየተከበረ እንደሆነ፣ አበው ያቆዩት ሥርዓት እየተጠበቀ እንደሆነ ሊከታተሉ ሊያውቁ ይገባል፡፡
ስለዚህ በአጠቃላይ ችግሮቹ የተፈጠሩት በመጀመሪያ ያለ እድሜያቸው በሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ ተካተው ድርሻቸውን ሳያውቁ የሚኖሩ ስላሉ፣ ቀጥሎም በተናጠልም ሆነ በቡድን ተሰባስበው እኛ መስበክ አለብን ወይም እገሌ ካልሰበከ አይሆንም በማለት እንደግል አመለካከት በመያዝ የሚንቀሳቀሱ ስላሉ ነው፡፡ ይሄንን ደግሞ ሰበካ ጉባኤው ባለው ሥልጣን ማስተካከል ይችላል፡፡
• በአለመግባባቱ ውስጥ ሁለት ዋና ቡድኖች እንደተፈጠሩ ይነገራል፤ የቅዱስ ገብርኤል ወርሃዊ በዓል ማግስትም ግጭቶች እንደተፈጠሩ ይታወቃል፡፡ እነዚህ ቡድኖች ምንድን ነው አካሄዳቸው? ወይም ምክንያታቸው?
ሰዎች በራሳቸው እይታ ሁለት ቡድን አለ ሊሉ ይችላሉ፡፡ እንደ ሀገረ ስብከት ግን እኛ ሁለት ቡድን አለ የምንለው ነገር የለም፡፡ በመሠረቱ ቤተክርስቲያን ዓላማዋ ሰውና እግዚአብሔርን ማገናኘት ነው፡፡ በዚህ ሕይወት ደግሞ ወንጌልን፣ ፍቅርን ትህትናን እርስ በእርስ መከባበርን መተሳሰብን እንዲይዙ ማድረግ ነው፡፡ እንደ ጌታችን መድኅኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርትም የቡድን አካሄድ የመከፋፈል አካሄድ፣ የመለያየት አካሄድ አነ ዘአጵሎስ ወአነ ዘኬፋ የሚለው አነጋገር በቅዱስ ወንጌልም የተደገፈ አይደለም፡፡ እኛ ከመጣን ጀምሮ የምናየው ቅድም እንዳልኩት ነው፡፡ ከችግሮቹ ምንጮች እንደገለጽኩት ከሰንበት ትምህርት ቤት የተውጣጡ የተወሰኑ የእድሜ ገደብ ያለፋባቸውና እኛ ብቻ ነን መስበክ ማስተማር ያለብን የሚሉና ወጣቶችንም ወደ ስሜት ወደ መገፋፋት የሚያመጡና፣ የቤተክርስቲያኗ ደንብ ሥርዓትና መመሪያ ያለመቀበል ሁኔታ የሚያሳዩና እንደ ራሳቸው ሃሳብ የመሄድ ጉዳይ ይታያል በሌላ በኩል መላው ምዕመናን ማለት ይቻላል፤ ሕጉ ሥርዓቱ የሲኖዶሱ መመሪያ ተከብሮ ቤተክርስቲያን ሥራዋን በአግባቡ ታከናውን የሚል ብቻ ነው ያለው፡፡ እንግዲህ አሁን የመለያየትና የቡድን ስሜት የለውም፡፡ ሕጉና መመሪያው ሲነገር ሁሉም ይሰማል፣ ሁሉም ያከብራል እዚህ ቅዱስ ገብርኤል ሰንበት ትምህርት ቤት ያሉ ጥቂት ወጣቶች ግን የልጅነትም ሊሆን ይችላል ከረር የማለትና መድረኩን እኛ ካልያዝነው፣ ስብከቱንም እኛ ካልሰበክነው የሚል የግል አካሄድ ያሳያሉ እንጂ ከሁለት የተከፈለ ቡድን የለም፡፡
የአገር ሽማግሌዎችን አባቶች፣ እባካችሁ ይሄንን መመሪያ እንዲያከብሩ አድርጓቸው፣ ትንሽ እኛን አልሰማ አሉ የሚቻለውን ነግረናል ብለን ስናስረዳ፤ እግዚአብሔር ይስጣችሁ፥ ሸክሙን እንድናግዛችሁ ወደ እኛ ማምጣታችሁ ጥሩ ነው ብለው ብዙ ደክመዋል በዚህ ጉዳይ፡፡ የተቀበሉ አሉ፥ ልክ ነው ያሉ አሉ፡፡ አንዳንዶቹ ግን የለም አይሆንም ያሉ አሉ፡፡ እንደዚህ እንደዚህ አይነት አካሄዶች ናቸው እንጂ እንደ ሰው አባባል ሁለት ቡድን የለም፡፡
ሰው ምን ጊዜም ችግር የሚገጥመው ከሕግ፣ ከሥርዓትና ከመመሪያ ሲወጣ መሆኑ ግለፅ ነው። ያለን ቆይታ አጭር በመሆኑ እስከ አሁን ያየነው ሁኔታ ከላይ የገለፅኩትን ነው የሚመስለው። ከበስተኋላው ምንድን ነው ይሄ ነገር? ምንስ አይነት እንቅስቄሴ አለው? ወይስ የተለየ ዓላማ አለው? ወይስ ሕጉን ያለማወቅ ብቻ ነው? ወይስ ደግሞ ቃለ ዐዋዲውን ያለመቀበል ነው? እስከ አሁን እንደምናየው መመሪያው እየተነገረ እያዩ እየሰሙ ያለመቀበል ነው ያለው? ግን ከበስተኋላ ምን አለው? ተጨማሪ ነገር አለው ወይ? የሚለው ግን ትንሽ ጥናት ይፈልጋል፡፡ ሲነገራቸው ተስተካክለው በመስመር መጓዝ የጀመሩና የሄዱ አሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ የለም እንዲህ ነው እያሉ ክርር የሚሉ አሉ፡፡ ሰው ሕሊናው እያየ አእምሮው ያስባል፡፡ ማንኛውም በአርአያ እግዚአብሔር የተፈጠረ ሰው ሲነገረው ይሰማል፤ ሲያይ ያነባል፥ ግን አንብቦ፣ ተነግሮት ሰምቶ፣ ተረድቶ፣ እውነቱን አውቆ ግን ይሄ ነው ማለት መቻል አለበት፡፡ ይሄንን ካልቻለ ችግሩ ምን እንደሆነ የሰውየው ሁኔታ ነው አላማውን የሚያውቀው፡፡
የቅዱስ ገብርኤል ሰንበት ትምህርት ቤት የራሱ የሆነ መምህር የለውም፡፡ ከዚህም የተነሳ ከብፁዕ የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ ጋር ጉዳዩን በመመካከርና በመነጋገር፣ እንደብፁዕነታቸውም መመሪያ በመቀበል አሁን የሰበካ ጉባኤ ምርጫ ከተካሄደ በኋላ በሂደት ሰንበት ትምህርት ቤቱ በአግባቡ መምህር እንዲኖረው፣ ልጆች ተኮትኩተው የቤተክርስቲያኒቱን ሥርዓትና ደንብ ጠንቅቀው አውቀው እየተገበሩ እንዲያድጉ ለማድረግ፣ ይሄ በእቅድ ደረጃ ተይዟል፡፡ ትምህርትም ሲሰጥ እንደ እድሜ ደረጃቸው ነው። ወጣቶች አሉ፣ ህፃናት አሉ፣ አዋቂዎች አሉ፣ እንደወንጌሉም ግልገሎች፤ ጠቦቶች በጎች፣ ብሎ ይለየዋልና። እዚያ ሰንበት ትምህርት ቤት ደግሞ ተቀላቅለው ነው የሚማሩት ይህ ችግር ይፈጥራል፡፡
ሌላው ቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ ምንም አይነት የሥራ ድርሻ የሌላቸው ያልተቀጠሩ፣ የሥራ ውል የሌላቸው ወይ ዲያቆን፣ ቄስ፣ መነኩሴ፣ መሪጌታ፣ አወዳሽ ቀዳሽ ያልሆኑ፣ እንደ አንድ ምዕመን ጸልየው ወይም ትምህርት ሰምተው መሄድ ብቻ የሚገባቸው ሆነው ሳለ በማይገባቸው አንዳንድ አስተዳደራዊ ጉዳዮች ውስጥ ጣለቃ የመግባት ነገር ይታያል፡፡ በሰንበት ትምህርት ቤትም፣ በስብከተ ወንጌልም፣ በአውደ ምህረትም ጣልቃ የሚገቡ ሰዎች ናቸው ነገሩንም እንዲባባስ እያደረጉት የሚገኙት፡፡
• የቅዱስ ገብርኤል ገዳም አስተዳደርና ሰበካ ጉባኤ ችግሮቹን ለመፍታት ከእናንተ ጋር ያላቸው ተግባቦት ምን ይመስላል?
በእርግጥ አሁን ያለው ሰበካ ጉባኤ እኛ ከመምጣታችን በፊት ጊዜያዊ ተብሎ የተመረጠ ነው፡፡ በዚህ የተነሣ ብዙ ጊዜ፥ አንዳንድ ሥራዎችን ለመሥራት ሲቸገሩ እናያለን፡፡ ጠርተን በጋራ አወያይተናል፥ ተመካክረናል ጊዜያዊ ሆነው እንዴት እንደተመረጡ ለእኛም ግለፅ አይደለም፤ ምክንያቱም ባልነበርንበት ጊዜ ስለነበር፤ አንዳንድ ምዕመናንም አልመረጥንም፤ ጊዜያዊ ናቸው፤ የማለት ያለመተባበር ችግር ይታያል፡፡
እኛ ከመጣን ግን የገዳሙን አስተዳዳሪና ሰበካ ጉባኤውንም በጋራ ቁጭ አድርገን አወያይተናል፥ ማደሪያ ጉዳዩንም አገላብጠን ተመልክተን ጊዜአዊ ሰበካ ጉባኤ መሆናቸውን እነርሱም አውቀውት፥ እነርሱም ባሉበት ሆነው፣ ከወጣቱም፣ ከአገር ሽማግሌዎችም፣ ከልማት ኮሚቴም፣ ከሚመለከታቸው አካላት የተወሰኑ ይዘን የመንግሥት አካላትም በታዛቢነት እንዲገኙልን አድርገን የቃለ ዐዋዲውን ሕግና መመሪያ በጠበቀ መልኩ ተገቢውን ቅስቀሳና ትምህርት ተሰጥቶ የቤተክርስቲያኒቱን አስተዳደራዊ ሥራ በአግባቡ ሊመራና ግቢውን ሊያስከብር ሊጠብቅ የሚችል ሰበካ ጉባኤ ምርጫ እንዲካሄድ የሚል ውሳኔም ስምምነት አድርገናል፡፡
አሁንም ቅድመ ሁኔታዎችን በማመቻቸት ላይ እንገኛለን፡፡ እስከዚያው ድረስ ግን አሁን ያለው ሰበካ ጉባኤ ያለውን ኃላፊነት እንዲወጣና ለአንድ ቀንም ቢሆን ኃላፊነት ስላለው ግቢውን እንዲያስከብር፣ እንዲጠብቅ በተደጋጋሚ ጊዜ ተወያይተናል መመሪያ ተሰጥቷል ብፁዕ አባታችንም በሰፊው ደክመውበታል፡፡ ተፈፃሚነቱ ግን እምብዛም አይታይም፡፡ የአቅም ማደስም፣ ኃላፊነትን በአግባቡ አለመወጣት ሊሆን ይችላል እንግዲህ ምክንያቱ፡፡
በግቢው ያለው ማንኛውም እንቅስቃሴ ሰበካ ጉባኤውንም አስተዳዳሪውን በመጀመሪያ ደረጃ ይመለከታል፡፡ ስለዚህ አዛው አጥቢያው ላይ እንደ ቃለ ዐዋዲው የማስኬድ ፣ መመሪያውን የመጠበቅና የማስጠበቅ፣ መስመሮችን እንዳይለቁ የመከታተልና ቁርጥ ያለ ውሳኔና ፍትሕ የመስጠት አስተዳደራዊ ሥራ ቢሠራ ምንም አይነት ችግር አይኖርም፡፡
ይቆየን



በስምንት ዓመት የጎንደር ቆይታዬ በየዓመቱ በዓሉን የመካፈል ዕድል አግኝቻለሁ። እያንዳንዱ ዓመት የየራሱ የሆነ ለየት ያሉ ትዕይንቶች ነበሩት። በአጠቃላይ ግን የታዳሚው ቁጥር ለማመን በሚያስቸግር መልኩ ከዓመት ወደ ዓመት እየጨመረ መጥቷል። በሌላ መልኩ ደግሞ ወጣቱ በበዓሉ ላይ ያለው ተሳትፎ ለውጥም ከቤተ ክርስቲያን ሥርዓት አንፃር በጣም የሚበረታታ ነው።
ታቦታቱ ከየአብያተ ክርስቲያናቱ በክብር ወጥተው በሕዝቡ እልልታ፣ ሽብሽባ እና በካህናቱ ውብ ያሬዳዊ ዜማ ወደ ወንዝ ወይም የተዘጋጀ የውኃ ቦታ በመውረድ የሚጀምረው ይህ በዓል ሕዝቡን በሰፊው የሚያሳተፍ ነው።
በበዓሉ ላይ ትልቅ ተሳትፎ ያደርጋል። በዓሉ ከመከበሩ ከወራት በፊት በየሰንበት ትምህርት ቤቱ በልዩ ኮሚቴዎች የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ሲያደርግ ቆይቷል።

በያዝነው የፈረንጆች አመት መጋቢት ወር ላይም በፋሽን፣ በፈንጠዝያ፣ በሙዚቃ፣ በመንገድ ላይ ቲአትሮችና በካርኒቫል ለማክበር እቅድ ተይዟል። 
መርካቶ የሚለውን ቃል እዚህ ጋር ስናነብ መቼም በየሕሊናችን የሚመጡ ብዙ የመርካቶ ሥዕሎች ይኖራሉ ፡፡ በተለይ ግርግሩ፣ ማጭበርበሩ፣ ሌብነቱ፣ በቀላሉ የማይገታዉ አመጹ፣ ምንም ነገር ፈልጎ የማይታጣበት መሆኑ፣ ቆሻሻው….በነዚህ ሁሉ ነገሮች እንደ መርካቶ ቅድሚያዉን የሚይዝ አካባቢ የሚኖር አይመስለኝም፡፡
ዛሬ የመርካቶን ሌላኛውን መልክ እንይ፡፡ በመርካቶ ውስጥ የሚኖሩ ነዋሪዎች፣ ነጋዴዎች እና ወጣቶች በደንብ ከሚታወቁባቸዉ ነገሮች መካከል አንዱ መንፈሳዊ አገልግሎታቸው ነዉ፡፡ ሁለት ወይም ሦስት ሆነው ሙሉ ቤተ ክርስቲያን የሚያሠሩ፣ ነዳያንን የሚያበሉ፣ የሚያለብሱ፣ በየዓመት በዓሉ የተቸገሩ ወገኖቻችን ከሌላው ወገናቸው ባልተናነሰ መንገድ በዓሉን እንዲያከብሩ በገንዘብ እና ለበዓላት በሚያስፈልጉ ነገሮች የሚረዱ በትክክል ገንዘባቸው ከየት እንደተገኘ የተረዱ ወገኖችን የያዘ አከባቢ መርካቶ ነው፡፡
መርካቶ ለሀገሪቷ ኢኮኖሚ ዋልታ አንዱ መሆኑ አይዘነጋም፡፡ ይሁን እንጂ ለቤተ ክርስቲያንም ትልቅ የገንዘብ እና የሰው ኀይል ምንጭ እንደሆነ ቤተ ክርስቲያኒቷ ምን ያህል እንደተገነዘበች እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ በአራቱም ማዕዘን የሚገኙ የገጠር አብያተ ክርስቲያናት ሕልውና እንዳይጠፋና በነዚሁ አከባቢ ለሚኖሩ ምዕመናን ተስፋ በመሆን እያገለገሉ ያሉ የቤተ ክርስቲያን አለኝታ የሆኑ የክርስቲያን ወገኖችን የያዘ ቦታ መርካቶ ነው፡፡
የመርካቶ መሬት ወትሮ ከሚታወቅበት ቆሻሻነት ጸድቶ እሱም እንደ አዲስ ክርስቲያን ተጠምቆ በቄጠማ፣ በምንጣፍ አምሮበት ለሚያይ የወትሮው መርካቶ ነው ብሎ ለማመን በጣም ያስቸግራል፡፡ አየሩ በዕጣን መዓዛ ተሞልቶ፣ በመዝሙርና ዕልልታ ደምቆ ልዩ ልዩ ቀለማት ባሏቸው ፊኛዎችና ጥቅሶች ተውቦ ለሚያየው እውነት ይህ መርካቶ ነው ብሎ እንዲጠይቅ ያደርገዋል፡፡
ወጣቶች በልዩ ልዩ ቲሸርቶችና ጥቅሶች ደምቀው ቄጠማ በመጎዝጎዝ፣ ርዝመቱ በውል የማይታወቀውን ምንጣፍ በመጠቅለል እና በመዘርጋት ታቦታቱን ያከበሩ ካህናት በባዶ አስፓልት ላይ እንዳይራመዱ የሚፋጠኑትን ወጣቶች ስናይ የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራ ሳናደንቅ አናልፍም፡፡
ታዲያ ቤተ ክርስቲያን፣ የሰንበት ትምህርት ቤቶች እና ሌሎች የሚመለከታቸዉ የመንፈሳውያን ማኅበራት ይህንን ጊዜ ትልቅ የቤት ሥራ እንደሚጠብቃቸው ልብ ሊሉት ይገባል፡፡ ጌታችን ወደኔ የመጣውን ወደውጭ አላወጣውም ብሏልና እነዚህን ወጣቶች አሳልፈን እንዳንሰጥ የተቀበልነውን አደራ እናስታዉስ፡፡ ስለዚህ ቢታሰብላቸው፡፡
የ2003 ዓ.ም የጌታችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት ዋዜማ የከተራ በዓል በታላቅ ድምቀት ተከብሯል። በዋናው በዓል ዋዜማ፥ ከሥርዓተ ቅዳሴው ፍጻሜ በኋላ ታቦታተ ሕጉ ከመንበረ ክብራቸው ተነስተው በየምዕራፉ በሊቃውንት አባቶች ስብሐተ እግዚአብሔር እየተደረሰ በሰንበት ት/ቤት አባላትና ምዕመናን መዝሙር እየተዘመረ ወደ ባሕረ ጥምቀቱ አምርተዋል።
መረዋሕ የያዙ ዲያቆናት፥ በሰልፍ ሆነው የሚዘምሩ ጥንግ ድርብና ካባ የለበሱ መዘምራን፥ የደንብ ልብስ የለበሱ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች፥ ፀአዳ የለበሱ የማኅበረ ቅዱሳን መዘምራን የጌታችን ጥምቀት የሚመለከቱ መዝሙሮችን በመዘመር፥ ወጣቶች ግራና ቀኝ እጅ ለእጅ በመያያዝ ሕዝበ ክርስቲያኑን ወደ ቀኝና ወደ ግራ ከፊትና ከኋላ በማድረግ ያለ ምንም ትርምስና ግርግር የተለያዩ ጥምቀትን የሚመለከቱ መዝሙሮችን በመዘመር፣ ወጣቶችም ፊት በመቅደም ለታቦታቱ ክብር ያዘጋጁትን ምንጣፍ በማንጠፍና ቄጠማ በመጎዝጎዝ የእግዚአብሔር ማደሪያ ለሆኑት ታቦታተ ሕጉና ለአባቶቻችን ካህናት ልዩ ክብር በማሳየት ወደ ባሕረ ጥምቀት/ጃንሜዳ/ ደርሰዋል።
ይህም በዓል መገለጥ/epiphany/ ይባላል። በዕለቱ ደግሞ ነገ ጌታችን በተጠመቀ ጊዜ መገለጥ ሆኗል። የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ አንድነትና ሦስትነት ተገልጿል። ክርስቲያኖችም ይህንን በዓል የምናከብረው ለበረከትና ለረድኤት ነው። ምዕመኑ በተለየ ሁኔታ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ማራኪና አስደናቂ ነገር ለቤተ ክርስቲያኒቱ እያበረከተ መሆኑንና ይህ ደግሞ የቤተ ክርስቲያኒቱንም የአገሪቱንም መልካም ገፅታ የሚያንፀባርቅ ይሆናል። አገራዊና ዓለም አቀፋዊ ገጽታውም በጣም ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጠው መሆኑንና በዓሉ በነገው ዕለትም በከፍተኛ ድምቀት እንደሚከበር ገልጸዋል።
በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም የተገኙት የጠቅላይ ቤተ ክህነት ምክትል ሥራ አስኪያጅ ንቡረ እድ ኤልያስ አብርሃ በሰጡት ትምህርት «ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ማን አጠመቀው ብንባል ማን እንላለን? ዮሐንስ አጠመቀው እንበል? እኔ ግን ቅዱስ ዮሐንስ አምላክን በማጥመቁ የሰዎች ልጆች ሁላችን ነው ያጥመቅነው ብየ አምናለሁ። ኃይሌ ገ/ሥላሴ ሩጫ ቢያሸንፍ ኢትዮጵያ አሸነፈች እንደሚባለው፣ ሁሉም እንደሚደሰተው። «ተጠምቀ ሰማያዊ በእደ መሬታዊ» እንደተባለው ሰማያዊው አምላክ እግዚአብሔር ወልድ በመሬታዊው በዮሐንስ እጅ ተጠመቀ። ፈጣሪን የምናጠምቅ ሆነን አይደለም ምን ያህል እንደወደደን ያሳያል እንጂ። ብዙ ሰማያውያን ሠራዊት ነበሩ፣ በእነርሱ እጅ መጠመቅ ይችል ነበር፤ በባሕርይ አባቱ መጠመቅ ይችል ነበር፤ በባሕርይ ሕይወቱም መጠመቅ ይችል ነበር። ፈጣሪ አምላካችን በሰው እጅ ተጠመቀ እኮ? በእውነት ምን አይነት ፍቅር ነው? ምንስ አይነት መውደድ ነው? እኛም ፈጣሪ አምላክን ለማጥመቅ በቃን እኮ!» ብለዋል።

የጎንደር መንበረ መንግሥት መድኅኔዓለም ደብር አስተዳዳሪና የአራቱ ጉባኤያት /የብሉይ፣ የሐዲስ፣ የሊቃውንትና የመጻሕፍተ መነኮሳት/ የጉባኤ መምህር ከሆኑት ከሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ሐዲስ ጋር የጥምቀትን በዓል አስመልክተን በ09/05/03 ዓ.ም አጭር ቃለ ምልልስ በስልክ አድርገናል፡፡ ለሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ሐዲስ ከፍተኛ ምስጋናችንን እያቀረብን ለአንባቢዎቻችን የታላቁን ሊቅ ቃለ ምልልስ በማቅረብ እንኳን አደረሳችሁ እንላለን፡፡ መልካም ንባብ፡፡
አማርኛ መካነ ድር፡- የጥምቀትን በዓል ለምን እናከብራለን? ለክርስቲያኖች ያለው ፋይዳ ምንድን ነው?
ድርቡሽ /Mahdists of sudan/ የጎንደርን አብያተ ክርስቲያናትን ካቃጠለ በኋላ ግን 8 ታቦታት ብቻ ይወርዳሉ፡፡ እነዚህም-

