ከትርፍ ነፃ የሆኑ የምስልና የድምጽ ሲዲዎች እንደሚሠራጩ ተገለጠ፡፡
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን በኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ክፍል የተዘጋጁ 3 ሺህ የሚሆኑ የምስልና የድምጽ ሲዲዎች ኅዳር 8 ቀን 2004 ዓ.ም በማኅበሩ ጽ/ቤት እንደሚሠራጭ የምክረ ሐሳቡ አስተባባሪ ኢንጂነር ሙሉጌታ ጌትነት አስታወቁ፡፡
ኢንጅነር ሙሉጌታ እንደገለጡት የምስልና የድምጽ ሲዲዎችን ለማግኘትና ለማሠራጨት ምንም ዐይነት ትርፍ ታሳቢ ሳይደረግ የሲዲውን ዋጋ ብቻ በመሸፈን ማግኘት ይቻላል፡፡ በማያያዝም የሥርጭቱ ዋና ዓላማ ስብከተ ወንጌልን በተፋጠነ መንገድ ለምእመናን ማዳረስ ሲሆን በገበያ ላይ የሚገኙት የምስልና የድምጽ ሲዲዎች የምእመናንን ምጣኔ ሀብት የሚጎዱ በመሆናቸው በቀላሉ ቃለ እግዚአብሔር የሚስፋፋበትን መንገድ ለማመቻቸት፣ የተሐድሶ መናፍቃን ስሑት ትምህርቶች በሕዝበ ክርስቲያኑ ሰርገው ስለገቡ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ ያላቸውን የስብከት ሲዲዎች ምእመናን እንዲያገኙና ስለ ሃይማኖታቸው እንዲያውቁ ለመደገፍ፣ በከተማ የሚኖሩ ጥቂት ምእመናን የመካነ ድር አገልግሎት ተጠቃሚዎች ቢሆኑም አገልግሎቱ ውድና ዝቅተኛ ፍጥነት ስላለው የምስልና የድምጽ ዝግጅቶችን መመልከትና መስማት ስለማይችሉ ችግሩን አስወግዶ ተደራሽነትን ለማስፋፋት እንዲቻልና የቪሲዲ አገልግሎት ከገጠር እስከ ከተማ እየተስፋፋ በመምጣቱ ንጹህ የቤተ ክርስቲያን ትምህርቶችን ለሁሉም እንዲዳረስ ለማድረግ እንደሆነ አስተባባሪው አስገንዝበዋል፡፡

ያለ ነውርና ነቀፋ በመገኘቷ የተመረጠች ነበረች፡፡
 አክብሮት ባይኖራችሁ ትዳር ግሩም ምሥጢርና የታላቅ መንፈሳዊ ምሥጢር ምሳሌ ነው ፡፡ ቅዱስ    ጳውሎስ ስለዚህ ሲያስተምር “ይህ ምሥጢር ታላቅ ነው”   ይልና ጨምሮ “እኔ ግን ስለ ክርስቶስና    ስለ  ቤተ ክርስቲያን እላለሁ” ይላል   ፡፡(ኤፌ.፭፥፴፪) ጋብቻ የቤተ ክርስቲያንና   የክርስቶስ ምሳሌ ነው ፤  እንዲህ በከበረ    ምሥጢር ላይ ዳንኪረኞችን በመጋበዝ   ዝሙትን ታስተዋውቁበታላችሁን ? ነገር   ግን  ከእናንተ መካከል አንዱ እኔን፡- እንዲህ ስትል ደናግል ወይም ያገቡት አይጨፍሩ እያልክ ነው ፤  እንግዲያ እነርሱ በዚህ ሰርግ ላይ ካልጨፈሩ ማን ሊጨፍር ነው ? ብሎ ሊጠይቅ ይችላል ፡፡ ማንም  አይጨፍር ነው መልሴ ፡፡