በዲታ ወረዳ የቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን በአጽራረ ቤተ ክርስቲያን የቃጠሎ አደጋ ደረሰበት
ጥር 5/2004 ዓ.ም
በጋሞ ጎፋ ሀገረ ስብከት፣ በዲታ ወረዳ፣ ጋና ደሬ ቀበሌ፣ የቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን ታኅሣሥ 29 ቀን 2004 ዓ.ም. ከሌሊቱ በስድስት ሰዓት አካባቢ በእሳት ቃጠሎ አደጋ ደረሰበት፡፡

የቦታው አቀማመጥና አደጋው የደረሰበት ሰዓት ሌሊት በመሆኑ በቦታው ምንም ዓይነት ነዋያተ ቅድሳት ማትረፍ እንዳልተቻለ በቦታው የሚገኙት የደብሩ አገልጋይ ገልጸዋል፡፡ የአደጋውን መከሰት ሰምተው የመጡት የአካባቢው ምዕመናን ከሌሊት ጀምሮ ጥልቅ ሀዘናቸውን በለቅሶ ሲገልጹ እንደነበር በቦታው የተገኙት የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ዘግበዋል፡፡

አገልግሎት በአርሲ ሀገረ ስብከት ከኅዳር 29/2004 ዓ.ም እስከ ታኅሣሥ 10/2004 ዓ.ም ለ11 ተከታታይ ቀናት በተለየዩ ወረዳዎች አካሔደ፡፡ 27 አባላት የተሳተፉበት ሐዋርያዊ አገልግሎት በተመረጡ 6 ወረዳዎች ውስጥ በሚገኙ ቤተ ክርስቲያናት እንዲሁም በአሰላ ከተማ በተሳካ ሁኔታ የተከናወነ ሲሆን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ያፈራቻቸው የማኅበረ ቅዱሳን ሰባኪያነ ወንጌል አማካይነት በአውደ ምሕረት ላይ ለምእመናን ሰፋ ያለ የወንጌል ትምህርት ተሰጥቷል፡፡ በማኅበሩ መዝሙር ክፍል አባላት አማካይነት ከአባቶች እግር ስር ቁጭ ብለው የተማሩትን የቤተ ክርስቲያኗን ሥርዓትና ትውፊት የጠበቀ ያሬዳዊ ዝማሬ አቅርበዋል፡፡