የዩኒቨርሲቲዎች የታሪክ እይታ ከድጥ ወደ ማጡ
በመጀመሪያ ደረጃ ቤተ ክርስቲያን መንግሥትን እየተከተለች፣ በጦር እያስፈራራች ሃይማኖቷን እንዳስፋፋች አድርጎ ማቅረብ የተዛባ አስተሳሰብ የወለደው መሆኑን መናገር እንፈልጋለን። ይህ ብቻ ሳይሆን የቤተ ክርስቲያኗን ታሪክ በማዛባት የቀረበው ሐሳብ እንዲስተካከል እንጠይቃለን። እውነቱ ግን በተቃራኒው ነው። ቤተ ክርስቲያን ያለሰለሰችው የአረማውያን እና የአሕዛብ ልቡና ወደ ማእከላዊ መንግሥት ለመታቀፍ እንዳላስቸገረ እና መንግሥት የራሱን ሥራ ለመሥራት እንዳገዘው መረዳት ይገባል። ያለፈው ሥርዓት ፈጽሞታል ለሚሉት ጥፋት ቤተ ክርስቲያንን ተጠያቂ ማድረግ አንደበቷን ዘግታ እንድትቀመጥ ለማድረግ የተሸረበ ሴራ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል። ገለጻው እውነታን ያላገናዘበ መሆኑን መረዳት እና ተገቢውን መልስ መስጠት አስፈላጊ ሲሆን በሕግ መጠየቅ ይገባል።