ፊደል
ዲያቆን ዐቢይ ሙሉቀን ፊደል፤ ፈደለ፤ ጻፈ ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ሲሆን፤ ትርጉሙም የጽሕፈት ሁሉ መጀመሪያ፤ ምልክት፤ የመጽሐፍ ሁሉ መነሻ ማለት ነው፡፡ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ፊደል የሚለውን ቃል ሲተረጉሙ በቁሙ ልዩ፤ምርጥ ዘር፤ ቀለም፤ ምልክት፤ አምሳል፤ የድምጽና የቃል መልክ ሥዕል፤ መግለጫ፤ ማስታወቂያ፤ ዛቲ ፊደል፤ ሆህያተ ፊደል፤ ወዘተ በማለት ያብራሩታል፡፡ ካሕሳይ ገብረ እግዚአብሔር ሊቀ ሥልጣናት ሀብተ ማርያም ወርቅነህን […]
