መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
‹‹የሚሰማኝ ግን በተስፋ ይኖራል፤ ከክፉም ሁሉ ያለድንጋጤ ያርፋል›› (ምሳ.፩፥፴፫)
የእስራኤል ንጉሥ ጠቢቡ ሰሎሞን በግዛቱ ዘመን ለሕዝቡ በምሳሌ ቃሌን ስሙ እያለ በተደጋጋሚ ይናገር ነበር። ነገር ግን የእርሱን ሳይሆን የእግዚአብሔርን ቃል ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ቃልን መስማት ደግሞ ጥበበኛ ያደርጋል፤ ተስፋን ያለመልማል፤ ከክፉም ይታደጋል። ስለዚህ ‹‹ቃሌን የሚሰማ ግን በተስፋ ይኖራል፤ ከክፉም ሁሉ ያለድንጋጤ ያርፋል›› በማለት ያስረዳናል። በዚህ ኃይለ ቃል የእግዚአብሔርን ቃል መስማት፣ በተስፋ መኖርና ከክፉ መዳን የሚሉ መሠረታዊ ነጥቦችን እናገኛለን፤ እያንዳንዳቸውን እንመልከታቸው። (ምሳ.፩፥፴፫)
‹‹እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን›› (ኢያ. ፳፬፥፲፭)
የሰው ልጅ በመላ ዘመኑ በሚያጋጥመው መከራ እና ሥቃይ ሊፈተን፤ ከባድ ችግርም ሊደርስበት ይችላል፡፡ ነገር ግን ፈተናው ከእግዚአብሔር ሲሆን ለድኅነት እና ለበረከት ከጠላት ዲያብሎስ ሲሆን ደግሞ ለጥፋት የሚመጣ በመሆኑ ፍርሃት ሳይሆን ጥንቃቄና ጽናት ያስፈልጋል፤ ‹‹እመን እንጂ አትፍራ›› እንደተባለው በእምነት ሁሉንም ፈተና ማለፍ ይቻላል፡፡ ይህን እውነት አውቀውና ተረድተው ወደ እግዚአብሔር መመለስ የሚፈልጉ ሰዎች ኢያሱ ‹‹እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን›› ብሎ እንደተናገረው ባዕድ አምልኮን ትተው እግዚአብሔርን ማምለክ ይኖርቸዋል፤ ካልሆነ ግን የዘለዓለም ቅጣት እንደሚጠበቃባቸው እሙን ነው፡፡ (ማር. ፭፥፴፮፤ ኢያ. ፳፬፥፲፭)
‹‹ሕግህ ለእግሬ መብራት ለመንገዴም ብርሃን ነው›› (መዝ፣ ፻፲፰፥፻፭)
የእግዚአብሔር ሕግ ብርሃን ነው፤ ‹‹ሕግህ ለእግሬ መብራት፥ ለመንገዴ ብርሃን ነው›› ብሎ ነቢዩ ዳዊት እንደተናገረው ከዚህ ከጨለማ እና ከተወሳሰበ ዓለም ከፈተና ያወጣን ዘንድ በትእዛዙ ልንኖር ይገባል፡፡ ማንኛውም ፍጡር የአምላኩን ስም የሚሰማበት ጊዜም ሆነ ሥፍራ ይኖራልና ፈጣሪያችን እውነት እና ሕይወትም መሆኑን ተረድተን በመንገዱ መጓዝ የእኛ ፈንታ ነው፡፡ (መዝ፣ ፻፲፰፥፻፭)
‹‹ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ›› (ዮሐ. ፲፬፥፲፭)
ሰው አምላኩ እግዚአብሔርን ከወደደ ሁለተናውን ለእርሱ ይሰጣል፤ ከኃጢአት የነጻ ሆኖ ልበ ንጽሕ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ኃጢአት በምንሠራበት ጊዜ ከፈጣሪያችን ስለምንረቅ ለሌላ ባዕድ ነገር ተገዢ እንሆናለን፡፡ ክርስቶስን በሙሉ ልባችን፤ ነፍሳችን፣ ኃይላችን ከወደድነው ግን ፍቅሩን ተረድተን ሁለመናችን ለእርሱ እንሰጣለን፤ እርሱም ደግሞ ከእኛ ጋር ይሆናል።
ወጣትነት እና የኮሮና ቫይረስ በሽታ ስርጭት
ሰው በእግዚአብሔር አርአያና አምሳል ተፈጥሯል፣ይህም ከጥንተ ተፈጥሮ በበለጠ በአዲስ ተፈጥሮ እግዚአብሔር ሰውን ምን ያክል እንደወደደው በልጁ የማዳን ሥራው ላይ በወንጌል ተምረናል።
‹‹ኑ እንዋቀስ ይላል እግዚአብሔር›› (ኢሳ. ፩፥፲፰)
ብዙ ጊዜ በሕይወት በሚገጥመን ፈተናና ችግር ምክንያት ራሳችንን በመመርመር እግዚአብሔርን መማጸንን የመሰለ መፍትሔ ወይም የድኅነት መንገድ የለም፡፡ እስራኤል ከእግዚአብሔር ርቀው፤ ወደ ቃሉ መጠጋት በአቃታቸው ጊዜ ነቢዩ ኢሳይያስ የመጣባቸው መቅሠፍት የኃጢአታቸው ውጤት ስለነበረ እግዚአብሔር አጥቦ ቅዱሳን ልጆቹ ሊያደርጋቸው የተዘጋጀ አባት በመሆኑ ‹‹ኑ እንዋቀስ ይላል እግዚአብሔር›› አላቸው፡፡ (ኢሳ. ፩፥፲፰)
‹‹ለታመሙት መድኃኒት አንተ ነህ›› (የዐርብ ሊጦን)
መድኃኒት ለሰው ልጅ ፈውስ መሆኑን እንረዳ ዘንድ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ በተገለጠበት ማለትም በዘመነ ሥጋዌው አስተምሯል፡፡ በዚያን ጊዜም ብዙዎች ወደ እርሱ እየቀረቡ ማንነቱን ለማወቅ ይጥሩ እና ትምህርቱንም ይሰሙ ነበር፡፡ እርሱም በመካከላቸው ሆኖ ወንጌልን ይሰበክላቸው፤ የታመሙትንም ይፈውሳቸው፤ የእጆቹን ተአምራት ዓይተውም ሆነ ሰምተው ያመኑትንም ያድናቸው ነበር፡፡ ‹‹ለታመሙት መድኃኒት አንተ ነህ›› እንደተባለው ፈውሰ ሥጋ እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነም ተረዱ፡፡ (የዐርብ ሊጦን)
በኮሌራ በሽታ ጉዳት ለደረሰባቸው ምእመናን ድጋፍ ተደረገ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት በኮሌራ ወረርሽኝ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው የዳሰነች ሕዝበ ክርስቲያን የእርዳታ ድጋፍ ተደረገ፡፡
ግስ
የግስ አርስቶች አልፎ አልፎ በአንዳንድ ጉባኤ ቤቶች በተወሰነ መንገድ ልዩነት አላቸው። ልዩነታቸው ግን የቁጥር ሳይሆን ግሶችን የመለዋወጥ ሁኔታ ነው። በቁጥር ሁሉም ስምንት ያደርጓቸዋል። ይሁን እንጂ በዚህ ጽሑፍ አብዛኛዎቹ የሚከተሉትን እናቀርባለን። ለማሳያ ያህል ሊቀ ሊቃውንት ያሬድ ሽፈራው መጽሐፈ ግስ ወሰዋስው መርኆ መጻሕፍት በተባለ መጽሐፋቸው የግስ አርስቶች የምንላቸው ስምንት ናቸው ። እነርሱም ቀተለ፣ ቀደሰ፣ ተንበለ፣ ባረከ፣ ማኅረከ፣ ሴሰየ፣ ክህለ፣ ጦመረ ናቸው በማለት ይገልጹአቸዋል። (ያሬድ፣ገጽ ፬፻፳፭)
ጾመ ሐዋርያት እና ጾመ ድኅነት
በዚህ ዓመት ጾመ ሐዋርያት ሰኔ ፩፤ ጾመ ድኅነት ደግሞ ሰኔ ፫ ቀን ይጀመራሉ፡፡ በመሆኑም የምንጠቀመው በራሳችን መልካም ተግባር፤ የምንወቀሰውም በራሳችን ኃጢአት መሆኑን ተረድተን ‹ይሄ የቄሶች፤ ይሄ የመነኰሳት ነው› የሚል ሰበብ ሳንፈጥር ሁላችንም በአንድነት ብንጾማቸው ከእግዚአብሔር ዘንድይቅርታ ጸጋና ምሕረትን እናገኛለንና ራሳችንን ለጾም እናዘጋጅ፡፡