መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
ማኅበረ ቅዱሳን የቴሌቪዠን መርሐ ግብር ሊጀምር ነው
መስከረም 12 ቀን 2005 ዓ.ም.
በዲ/ን ዮሴፍ ይኲኖ አምላክ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ ማኅበረ ቅዱሳን ከጥቅምት 4 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በየሳምንቱ እሑድ ጧት ከ3፡30 እስከ 4፡00 ሰዓት የሚቆይ መርሐ ግብር በኢትዮጵያ ብሮድ ካስቲንግ ሰርቪስ ቴሌቪዠን (EBS TV) ለመጀመር ሙሉ ዝግጅት ማጠናቀቁ ተገለጠ፡፡
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጠ
መስከረም 12 ቀን 2005 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ በቤተ ክርስቲያኒቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መስከረም 11 ቀን 2004 ዓ. ም. መግለጫ ሰጠ፡፡ መግለጫውን የሰጡት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ሓላፊ የሆኑት እስክንድር ገብረ ክርስቶስ ሲሆኑ በመግለጫቸውም “በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥና ዙሪያ ተሸሽገው የተዛባ መረጃን በማቀበል የሽግግር ወቅት ሂደቱን ሰላማዊ በሆነ መልኩ እንዳይራመድ የሚጥሩ ወገኖች ሁሉ ከዚህ አፍራሽ እንቅስቃሴያቸው እንዲታቀቡ እያሳሰብን ይህ ባይሆን ግን የሽግግር ሂደቱን ሰላማዊ ለማድረግ ሲባል ቤተ ክርስቲያኒቱ ሕጋዊ እርምጃዎቸን ለመውስድ የምትገደድ መሆኑን አጥብቃ ለማሳሰብ ትወዳለች፡፡” ብለዋል፡፡
የተቀጸል ጽጌ በዓል ተከበረ
መስከረም 11 ቀን 2005 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በየዓመቱ የሚከበረው የተቀጸል ጽጌ በዓል በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል መስከረም 10 ቀን 2005 ዓ.ም. በድምቀት ተከበረ፡፡
ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክና የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል፤ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፤ የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች፤ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፤ አረጋውያን አርበኞች፤ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አባላትና ምእመናን በተገኙበት የተከበረው ይኸው በዓል ከቅዳሴ በኋላ በጸሎተ ወንጌል የተጀመረ ሲሆን የዕለቱ ተረኛ በሆነው በርዕሰ አድባራት ወገዳማት አዲስ ዓለም ደብረ ጽዮን ማርያም ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ያሬዳዊ ዜማ ቀርቧል፡፡ በተጨማሪም የአጫብር ወቆሜ ወረብ፤አንዲሁም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት መዘምራን ያሬዳዊ ዜማ ያቀረቡ ሲሆን በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን የቅኔ መርሐ ግብር ተካሂዷል፡፡
ውጤታማ ለመሆን በውይይት ማመን
መስከረም 10 ቀን 2005 ዓ.ም.
ወልደ ማርያም
የአምስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ሥርዓተ ቀብር ከተፈጸመ ሳምንታት ተቆጠሩ፡፡ ፓትርያርኩ ዐርፈው መንበረ ፕትርክናው ባዶ መኾኑ ከተረጋገጠበት ዕለት ጀምሮ መንበሩን ለመጠበቅና ለማስጠበቅ ይበቃል ያለውን አካል የመሾም፤ የቤተ ክርስቲያኗን መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት የማስቀጠል ሓላፊነት የተጣለበት ቅዱስ ሲኖዶስ አምስት ዋና ዋና ተግባራትን ፈጽሟል፡፡
የመጀመሪያው ፓትርያርኩ ማረፋቸው እንደተሰማና እንደተረጋገጠ በፓትርያርኩ በኩል ቤተ ክርስቲያኗ የሰበሰበቻቸውን ሀብታት በአግባቡ እንዲጠብቁ ማድረግ ነው፡፡ ለዚህም ፓትርያርኩ ረቡዕ ለሐሙስ አጥቢያ ከንጋቱ 11 ሰዓት አካባቢ ዐርፈው በዕለቱ ወደ 7፡30 አካባቢ ይኖሩበትና በቢሮነት ይገለገሉባቸው የነበሩትን ቤቶች አሽጓል፡፡ ሁለተኛው ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን በሚያዘው መሠረት መንበረ ፕትርክናውን የሚጠብቅ፤ ቀጣዩ የቤተ ክርስቲያኗ ፓትርያርክ እስኪመረጥ ድረስ ሲኖዶሱን በበላይነት የሚመራ፣ /ህየንተ ፓትርያርክ/ ኾኖ የቤተ ክርስቲያኗን መንፈሳዊ አስተዳደር የሚመራ ዐቃቤ መንበር መምረጥነው፡፡ በዚሁም ነሐሴ 11 ቀን 2004 ዓ.ም ብፁዕ አቡነ ናትናኤልን ከያዙት የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጵጵስና በተጨማሪ ዐቃቤ መንበር ኾነው እንዲያገለግሉ መርጧቸዋል፡፡
የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን የፖትርያርክ ምርጫ የሚመለከት ረቂቅ ሕግ
መስከረም 10 ቀን 2005 ዓ.ም.
ወልደ ማርያም
ምዕራፍ 1
የዐቃቤ መንበሩን ምርጫ በተመለከተ
አንቀጽ 1
መንበረ ፓትርያርኩ በሞት ወይም በሌላ ምክንያት በመንበሩ ላይ ባይኖር ቅዱስ ሲኖዶስና ሚሊ ካውንስሉ /የምዕመናን ጉባኤ/ በዕድሜ አንጋፋ በሆነው ጳጳስ በሚጠራው ጉባኤ ሰብሳቢነት ቅዱስ ሲኖዶሱ ተሰይሞ ከ7 ቀን ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ዐቃቤ መንበር ይሰይማል፡፡ የተመረጠውም አባት ዐቃቤ መንበር በመሆን ያገለግላል፡፡ ብሔራዊ ዐዋጅ /republican decree/ ታውጆ በቤተ ክርስቲያኒቱ ሕግ፣ ትውፊትና ሥርዓት መሠረት ሕጋዊ የሆነው ፓትርያርክ ሹመት ይፈጸማል፡፡
ሃይማኖታውያን መስለው ከሚመጡ መናፍቃን ተጠንቀቁ ማቴ 7፥15
መስከረም 8 ቀን 2005 ዓ.ም.
አባ ዘሚካኤል
ትላንት ተዋሕዶን በማናናቅ ምእመናኑን ለማስኮብለል ያልተሳካላቸው መናፍቃን፣ ዛሬ ደግሞ ስልት ቀይሰው የተዋሕዶን ታሪክ፣ ግዕዝ ጠቀሳና ያሬዳዊ ዜማን ያደነቁ በመምሰልየመፈታተናቸው አንድምታው ምን ይሆን? የተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለዘመናት ያቆየችውን ትውፊት፣ ቅርስና ሀብት የመቀራመቱ ድፍረትሳ ተመሳስሎ ተጠግቶ ማንነትዋን ለመጋራት ይሆን?ዓላማው መጀመሪያ ምእመኑን የማዘናጋት ቀጥሎ አንድነን ለማለትና ወደመናፍቅነት ለመሳብ ከዚያም እንደ ሰለጠነው ዓለም ፍጹም ዓለማዊ ለማድረግ ይሆንን?
ከምርጫው ይልቅ ለቅድመ ምርጫው!!
መስከረም 8 ቀን 2005 ዓ.ም.
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
የረጅም ዘመን ታሪክ ያላት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ይህን ያህል ዘመን ተጉዛ ከዚህ የደረሰችው በተአምር ብቻ አይደለም፡፡ ሁል ጊዜ በጽኑ እምነትና ምግባር እግዚአብሔርን በማመስገንና ሰውን በማገልገል የታወቁ እልፍ አእላፍ ቅዱሳን ካህናትና ምእመናን በውስጧ በመኖራቸው ነው፡፡ በእነዚህ ቅዱሳን አበው በየቦታው ትምህርት ቤቶች እንዲስፋፉና መጻሕፍትም እንዲበዙ የተደረገውም ጥረት ለዚህ ታሪካዊ ዕድገት ያበረከተው አስተዋፅኦ የታሪክ ትዝታ ብቻ ሳይሆን አሁንም በተግባር የሚታይ ሐቅ ነው፡፡
የማኅበረ ቅዱሳን 10ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ
መስከረም 3 ቀን 2004 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
ሪፖርታዥ
ነሐሴ 29 ቀን 2004 ዓ.ም.
በዋዜማው ነሐሴ 29 ቀን 2004 ዓ.ም. ከቀኑ ስድስት ስዓት ጀምሮ ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የመጡ የማኅበሩ አባላት ማኅበሩ እያስገነባው በሚገኘው ሕንጻ ውስጥ በመገኘት የሕንጻው ግንባታና በማኅበሩ የአንዳንድ አገልግሎት ክፍሎችን እንቅስቃሴ በመጎብኘት ማብራሪያ እየተሰጣቸው ቆይተዋል፡፡ ከምሽቱ 12፤00 ስዓት ጀምሮ የጠቅላላ ጉባኤው አስተባባሪ ኮሚቴ ባዘጋጀው ትራንስፖርት ከማኅበሩ ዋናው ማእከል አቧሬ ወደሚገኘው አቡነ ጎርጎርዮስ የትምህርትና ሥልጠና ማእከል በመጓዝ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት፤ የመርሐ ግብር ትውውቅ፤ ሕጽበተ እግርና የእራት መርሐ ግብር ተከናውኗል፡፡
የማኅበረ ቅዱሳን 10ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ተጠናቀቀ
ጳጉሜን 5 ቀን 2004 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
ነሐሴ 30 ቀን 2004 ዓ.ም. የተጀመረው የማኅበረ ቅዱሳን መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ በታቀደለትና በወጣለት መርሐ ግብር መሰረት በማካሔድ ጳጉሜን 2 ቀን 2004 ዓ.ም. ከለሊቱ 9፡00 ስዓት በድምቀት ተጠናቀቀ፡፡
ጳጉሜን 2 ቀን 2004 ዓ.ም. ለሊት በተካሔደው የጠቅላላ ጉባኤው ቀጣይ ውይይት በቀኑ መርሐ ግብር የአራት ዓመት ስልታዊ እቅድ ረቂቅ ላይ የተካሔደውን የቡድን ውይይት ውጤት በየቡድኖቹ ሰብሳቢዎችና ጸሐፊዎች አማካይነት እንዲቀርቡ በማድረግ በጠቅላላ ጉባኤው ውይይት ተካሒዶበት ጸድቋል፡፡ በቀጣይነትም የማኅበረ ቅዱሳን ዋና ዋና የአገልግሎት ክፍሎች ስለክፍሎቻቸው እንቅስቃሴ ለጠቅላላ ጉባኤው ግንዛቤ የማስጨበጥና አሁን ያሉበትን ደረጃ አቅርበዋል፡፡
የሐዋሳ ማእከል በአፍ መፍቻ ቋንቋ ያሠለጠናቸውን ሰባኪያነ ወንጌል አስመረቀ
ጳጉሜን 5 ቀን 2004 ዓ.ም.
በዳዊት ደስታ
የማኅበረ ቅዱሳን ሐዋሳ ማእከል ትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት የገጠር ስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ ንዑስ ክፍል በአፍ መፍቻ ቋንቋ ለአንድ ወር ያሠለጠናቸውን ሠልጣኞች ነሐሴ 1 ቀን 2004 ዓ.ም. አስመረቀ፡፡
የሲዳማና ቦረና ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ ገብርኤል “በሕዝቡ ቋንቋ ባለማስተማራችን በማኅሌት ብቻ በመወሰናችን ቤተ ክርስቲያን የተሰወረች ሆና በዚህ በደቡብ ክፍለ ሀገር ትታያለች፡፡ ይህ ትልቅ ጉድለት ነው፡፡ ለቤተ ክርስቲያናችን የቆመ ማኅበር ማኅበረ ቅዱሳን በየትኛው በኩል ጉድለት እንዳለብን የተገነዘቡ ልጆቻችን ይህንን የሥልጠና መርሐ ግብር መጀመራቸው ያለብንን ጉድለት ይሞላል” በማለት በምረቃው ዕለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡