መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
አቡነ ጎርጎርዮስ የሥልጠና ማእከል የበገና ተማሪዎችን አስመረቀ
ሐምሌ 17 ቀን 2005 ዓ.ም.
በታመነ ተክለ ዮሐንስ
ከፍተኛ ውጤት ለማስመዝገቤ ምስጢሩ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ መኖሬ ነው
ሐምሌ 5 ቀን 2005 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
ሰሞኑን ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች በመመረቅ ላይ ይገኛሉ፡፡ ከተመራቂ ተማሪዎች መካከል ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ሁለት የወርቅ ሜዳልያዎች የተሸለመችውን
አንዲት እኅት ለዛሬ እንግዳችን አድርገናታል፡፡ አንዱን የወርቅ ሜዳልያዋንም “በግቢ ጉባኤ ውስጥ በመሳተፍ በመንፈሳዊ ሕይወቴ እንድበረታና ዓላማዬን እንዳሳካ እገዛ አድርጎልኛል” ለምትለው ማኅበረ ቅዱሳን በሥጦታ አበርክታለች፡፡ የዩኒቨርስቲ ቆይታዋን፤ በግቢ ጉባኤ ውስጥ ስለነበራት ተሳትፎ እና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ አነጋግረናታል፡፡ መልካም ቆይታ፡፡
ጥያቄ፡- ራስሽን ብታስተዋውቂን?
ፋንታነሽ ፡- ፋንታነሽ ንብረት እባላለሁ፡፡ የመጣሁት ከሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ሚዛን ግቢ ጉባኤ ነው፡፡ የተመረቅሁት አዲስ የትምህርት ዘርፍ በሆነው በኮፕሬቲቭ አካውንቲንግ /Cooprative Accounting/ በመጀመሪያ ዲግሪ ነው፡፡
ብዙ ከተሰጠው ከእርሱ ብዙ ይፈለግበታል
ሐምሌ 4 ቀን 2005 ዓ.ም.
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ቤተ ክርስቲያናችን ካሏት አህጉረ ስብከት ሁሉ ለየት የሚልበት ባሕርያት አሉት፡፡ ሀገረ ስብከቱ የሀገሪቱ ዋና ከተማ እንደመሆኑ በተለያዩ ምክንያቶች ከሁሉም አህጉረ ስብከት የሚመጡ ክርስቲያኖች አገልግሎት የሚያገኙባቸው ገዳማትና አድባራት ያሉበት ሀገረ ስብከት ነው፡፡ በተለያዩ ቋንቋዎች የሚናገሩ የተለያዩ ባህሎች ያሏቸው የቤተ ክርስቲያን ቤተሰቦች ተገናኝተው በአንድነት መንፈስ አገልግሎት የሚያገኙበትና የሚቀበሉበት ሀገረ ስብከትም ነው፡፡
ሀገረ ስብከቱ በርካታ የቤተ ክርስቲያናችን መምህራን ሊቃውንት የሚገኙበትም ሀገረ ስብከት ነው፡፡ በመንፈሳዊው ትምህርት ብቻ ሳይሆን በዓለሙ የሚሰጠውን ማኅበራዊና የተፈጥሮ ሳይንስ፣ የሙያና የቀለም ትምህርቶች የተማሩ አንቱ የተባሉ የቤተ ክርስቲያኒቱ ልጆችም የሚገኙበት ሀገረ ስብከት ነው፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን በታላቅ ፍቅር የሚጠብቃት፣ አገልግሎቷን ዕለት ዕለት የሚሻ ቸርና የዋህ ሕዝበ ክርስቲያን ያለበት ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ቤተ ክርስቲያን የምትተዳደርበትን ብዙ የገንዘብ የቁሳቁስና የሰው ኃይል ሀብት ይዞ የሚገኝ ነው፡፡ ከዚህም የተነሣ አርአያነት ያለው አግልግሎትን ሊሰጥም እንደሚችል የሚታሰብ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዝርወት
ሐምሌ 3 ቀን 2005 ዓ.ም
በዲ/ን ዶ/ር መርሻ አለኸኝ
የዚህ ጽሑፍ ዓላማ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዝርወት /ከኢትዮጵያ ውጭ/ ያደረገችውን ረጅም ሐዋርያዊ ጉዞ በአጭሩ በመዳሰስ፤ ጉዞዋ ዛሬ የደረሰበትን ምዕራፍ መቃኘት ነው፡፡ የዛሬው ከታየ ዘንድ ግን ጽሑፉ በመጠኑም ቢሆን ጥናታዊ መልክ ይኖረው ዘንድ ዛሬ ቤተ ክርስቲያኗ በውጭው ዓለም ለምትሰጠው አገልግሎት እንቅፋት ናቸው ተብለው ሊጠቀሱ ከሚችሉ ችግሮች ዋና ዋና የሚባሉትን በማቅረብ የይሁንታ አሳብ ይሰነዝራል፡፡
ኢትዮጵያ እንደ ሀገር እምነትን በተመለከተ የግንኙነት መስመሯን ወደ ውጭ መዘርጋት የጀመረችው ቅድመ ክርስትና ከ1000 ዓ.ዓ. ገደማ ጀምሮ ነው፡፡ በቃልም በመጣፍም የቆየን የሀገራችን ወፍራም የእምነት ታሪክ እንደሚነግረን ንግሥተ ሳባ በሕገ ልቡና እግዚአብሔርን ሲያመልክ የነበረ ሕዝቧን በመወከል ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዛ ከንጉሡ ከሰሎሞን ጋር በመወያየት እግዚአብሔር ለእሱና ለሕዝቡ የገለጠውን ሕገ ኦሪት ይዛ ወደ አገሯ ተመልሳለች፡፡ ሕዝቧንም በዚሁ የኦሪት ሕግና እምነት እንዲመራ አድርጋለች፡፡ እሷ የጀመረችው ግንኙነትም በኋላ የመንፈሳዊ ጥበብ ፍለጋ ጉዞዋ ሌላ ውጤት በሆነው ልጇ ቀዳማዊ ምንልክና እሱ ባመጣቸው ሌዋውያን ካህናት አማካይነት ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
ሰዋሰወ ግእዝ ክፍል አራት
ሐምሌ 3 ቀን 2005 ዓ.ም.
በመ/ት ኑኀሚን ዋቅጅራ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
ባለፈው ሳምንት አምዳችን ስለ ግእዝ ፊደላትና ስለ ዝርዋን የግእዝ ፊደላት የአዘራዘር ሥልትና የፊደላት ትርጉም ተመልክተናል፡፡ በዛሬው አምዳችን ደግሞ ስለ አማርኛ ፊደላትና የአማርኛ ዝርዋን ፊደላትን እንመለከታለን፡፡
የአዲስ አበባ ማእከል የግቢ ጉባዔያት ተማሪዎችን አስመረቀ
ሐምሌ 1 ቀን 2005 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
በማኅበረ ቅዱሳን የአዲስ አበባ ማእከል የግቢ ጉባዔያት ማስተባበሪያ ክፍል፤ የቅዱስ ማርቆስ አካባቢ ማስተባበሪያ፤ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የግቢ ጉባኤያት ተማሪዎችን በቅድስት
ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ አዳራሽ ሰኔ 30 ቀን 2005 በድምቀት አስመረቀ፡፡ ተማሪዎቹ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ /ከስድስት ኪሎ፤ ከአምስት ኪሎ ቴክኖሎጂ ፋኩልቲ፤ ከአራት ኪሎ የተፈጥሮ ሳይንስና ከቅዱስ ጳውሎስ/ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች በድኅረ ምረቃና በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቁ ሲሆኑ በግቢ ቆይታቸው መንፈሳዊ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ አንድ ሺህ የሚደርሱ ተማሪዎች ናቸው፡፡
ሰዋሰወ ግእዝ ክፍል ሦስት
ሰኔ 26 ቀን 2005 ዓ.ም.
በመ/ት ኑኀሚን ዋቅጅራ
ባለፈው ሳምንት አምዳችን ከ፳፮ (26)ቱ የግእዝ ፊደላት መካከል የ፲፫(13)ቱን የግእዝ ፊደላት ቅርጽ ከነትርጒማቸው መግለጻችን ይታወቃል፡፡
አቡነ እንድርያስ ገዳም/አቡነ እንድርያስ ዋሻ
ሰኔ 21 ቀን 2005 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
የማኅበረ ቅዱሳን የኅትመትና ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ክፍል አባላት በሰሜንና ደቡብ ጎንደር እንዲሁም በምዕራብ ጎጃም ሀገረ ሰብከቶች በመንቀሳቀስ የአድባራትና ገዳማት እንቅስቃሴዎችን ቃኝተን ከተመለስን ሰነባበትን፡፡ ክፍል ስድስት ድረስ ጸበል ጸዲቅ በሚል ርዕስ ስናቀርብ መቆየታችን ይታወሳል፡፡ በዚህም መሠረት ቀጣዮቹን ክፍሎች ማቅረባችንን እንቀጥላለን፡፡
ስዱዳን ለስዱዳን
ሰኔ 21 ቀን 2005 ዓ.ም
በዲ/ን ዶ/ር መርሻ አለኸኝ
ባለፈው ጽሑፌ በገባሁት ቃል መሠረት በባዕድ ምድር የሚኖሩ ወገኖች፤ የስደት ሕይወትን ከጀመሩበት አንሥቶ የጠበቁትን በማጣታቸው ችግር ውስጥ የገቡትን ወገኖቻቸውን እንዴት መርዳት እንዳለባቸው ለመጻፍ አሳቦቼን እያብላላሁ ነበር፡፡ ግንቦት ሃያ ቀን ምሽት እኔና ቤተሰቤ አልፎ አልፎ በምናየው የኢ.ቢ.ኤስ ቴሌቪዥን ጣቢያ አንድ ቃለ ምልልስ ተመለከትኩ፡፡ ቃለ ምልልሱን ያደረገችው በጣቢያው «ሄለን ሾው» የተሰኘ ሳምንታዊ ፕሮግራም ያላት ሄለን አሰፋ ነበረች፡፡ የዕለቱን ውይይት ያደረገችው ትእግሥት ከተባለች በመካከለኛው ምሥራቅ ነዋሪ ከሆነች ኢትዮጵያዊት ጋር ነበር፡፡ ትዕግሥት በወጣትነት የዕድሜ ክልል ውስጥ ትገኛለች፡፡
ሰዋስወ ግእዝ (ክፍል ሁለት)
ሰኔ 19 ቀን 2005 ዓ.ም.
በመ/ት ኑኀሚን ዋቅጅራ
፩.፪. የግእዝ ፊደላት አካፋፈል
መጀመሪያ ጊዜ ለሄኖስ በጸፍጸፈ ሰማይ (በሰማይ ገበታነት) የተገለጹለት ፊደላት አሁን በፊደል ገበታ ላይ በቅደም ተከተል እንደምናያቸው ሳይሆን ከዚህ በተለየ መልኩ ተዘበራርቀውና የእብራይስጡን የቋንቋ ስልት ይዘው ነው እነሱም አሌፋት በመባል የራሳቸው ስያሜ ነበራቸው
አ – አሌፍ ሐ – ሔት ሠ – ሣምኬት
በ – ቤት ጠ – ጤት ጸ – ጻዴ
ገ – ጋሜል የ – ዮድ ፈ – ፌ
ደ – ዳሌጥ ከ – ካፍ ዐ – ዔ
ሀ – ሄ ለ – ላሜድ ቀ – ቆፍ
ወ – ዋው መ – ሜም ተ – ታው
ዘ – ዛይ ነ – ኖን ረ – ሬስ