መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::




ግብረ ፊልጶስ ሲምፖዚየም ተካሄደ
ታኅሣሥ 16 ቀን 2006 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
በማኅበረ ቅዱሳን የትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት ዋና ክፍል የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ መርሐ ግብር “ግብረ ፊልጶስ” የተሰኘ ሲምፖዚየም ታኅሣሥ 12 እና 13 ቀን 2006 ዓ.ም. በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ግቢ ውስጥ አካሄደ፡፡
የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር ደብረ መድኀኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን
ታኅሣሥ 9 ቀን 2006 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
ሪፖርታዥ፡-
ከዋዜማው ጀምሮ መርሐ ግብሩን የተሳካ ለማድረግ የማኅበሩ ሐዊረ ሕይወት አዘጋጅ ኮሚቴ በሚመድበው መሠረት የየክፍሉ አገልጋዮች በአገልግሎት ተጠምደዋል፡፡ መርሐ ግብሩን የተሳካ ለማድረግ ሁሉም ይጣደፋል፤ የጎደለውን ይሞላል. . . ፡፡
ከሌሊቱ 12፡00 ጀምሮ አምስት ኪሎ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አጠገብ ከሚገኘው ከማኅበረ ቅዱሳን ሕንፃ ጀምሮ በተለምዶ ሰባ ደረጃ እስከሚባለው ሠፈር ድረስ ሰባ 1ኛ ደረጃ የሚሆኑ የከፍተኛ አገር አቋራጭ አውቶቡሶች መስመራቸውን ይዘው ተሰልፈው የምእመናንን መምጣት ይጠባበቃሉ፡፡
የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር በድምቀት ተካሔደ
ማኅበረ ቅዱሳን ለ5ኛ ጊዜ ያዘጋጀውን የሐዊረ ሕይወት መርሐ ግብር ደብረ ዘይት በሚገኘው ደብረ መድኃኒት ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ታኅሳስ 6 ቀን 2006 ዓ.ም. ከ 5000 ምዕመናን በላይ በተገኙበት አካሔደ፡፡ ዝርዝሩን እንደደረሰን እናቀርባለን፡፡
“ግብረ ፊልጶስ” የተሠኘ ሲምፖዚየም እንደሚዘጋጅ ተገለጸ
ታኅሣሥ 05 ቀን 2006 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
“ግብረ ፊልጶስ – ሐዋርያዊ ጉዞ በኢትዮጵያ በቀድሞው፤ በመካከለኛውና በአሁኑ ዘመን” በሚል መንፈሳዊ ጉባኤ በማኅበረ ቅዱሳን ትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት ዋና ክፍል የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ አማካይነት ሲምፖዚየም እንደሚዘጋጅ ተገለጸ፡፡
ተኅሣሥ 12 እና 13 ቀን 2006 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ስብከተ ወንጌል አዳራሽ በሚካሔደው ሲምፖዚየም ላይ ከዚህ በፊት በተልተሌ፤ ጂንካ፤ ከረዩ፤ መተከልና ግልገል በለስ አካባቢዎች ተጠምቀው የእግዚአብሔር ልጅነትን ያገኙ ምእመናን በአካል በመገኘት በጉባኤው ላይ አሁን ያሉበትን ሁኔታ ያቀርባሉ፡፡
የመስቀል በዓል አከባበር በዩኔስኮ ቅርስነት ተመዘገበ
ኅዳር 26 ቀን 2006 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
የኢትዮጵያ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን የኢትዮጵያ የመሰቀል በዓል አከባበር በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፤ የሳይንስና የባሕል ድርጅት (ዩኔስኮ) በማይዳሰሱ ቅርሶች (Intangible) በቅርስነት መመዝገቡን አስመልከቶ ኅዳር 26 ቀን 2006 ዓ.ም. በባለሥልጣኑ አዳራሽ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጠ፡፡
የመስቀል በዓል በዓለም ቅርስነት ተመዘገበ
የኢትያጵያ የመስቀል ክብረ በዓል በዓለም ቅርስነት መመዝገቡን UNESCO /ዩኔስኮ/ አስታወቀ፡፡ ዝርዝሩን እንደደረስን እናቀርባለን፡፡
ሐዊረ ሕይወት (የሕይወት ጉዞ)
ማኅበረ ቅዱሳን ከስደት ተመላሾችን ለመደገፍ እንደሚሠራ አስታወቀ
ኅዳር 24 ቀን 2006 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
ማኅበረ ቅዱሳን ከሳውዲ አረቢያ ተመላሽ ወገኖቻችንን ለመደገፍ ቀጣይ ሥራዎችን እንደሚሠራ አስታወቀ፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዝርወት ክፍል ሦስት
በዲ/ን ዶ/ር መርሻ አለኸኝ
ባለፈው ዕትማችን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ በዝርወት /ከኢትዮጵያ ውጪ/ ያደረገችውን ረዥም ሐዋርያዊ ጉዞ የሚዳስስ ጽሑፍ ማውጣታችን ይታወሳል፡፡ ቀጣዩን ደግሞ እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡
1.1. ውስጣዊ ችግሮች
ቤተ ክርስቲያን በረጅሙ የታሪክ ጉዞዋ ያጋጠሟት ችግሮች ወደ ኋላ ሲቃኙ በብዛት ከልዩ ልዩ አረማውያንና አላውያን ነገሥታት የመጡባት ውጫዊ ፈተናዎች በርከት ብለው ይታያሉ፡፡ እሷን ለመፈተን የማይታክተው ዲያብሎስ በዚህ ዘመን ደግሞ ከውጫዊው ፈተና ባልተናነሰ መልኩ አንዳንድ ክፍተቶችን በመግቢያነት እየተጠቀመ ቤተ ክርስቲያኗ በተለያዩ ውስጣዊ ችግሮች እንድትፈተን በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ እነዚህን ችግሮች አንድ በአንድ እንደሚከተለው እንዳስሳለን፡፡
በንብና ነብር የምትጠበቀው ሥዕለ ማርያም “ወይኑት”
ኅዳር 10 ቀን 2006 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታላላቅ ገዳማት መካከከል በምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ውስጥ የሚገኙት የመርጡለ ማርያም እና ደብረ ወርቅ ገዳማት በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳሉ፡፡ ሁለቱም ገዳማት ጥንት መሥዋዕተ ኦሪት ይከናወንባቸው የነበረና ታላላቅ ታሪካዊ ቅርሶችንም ለትውልድ በማስተላለፍ ረገድ ትልቁን ድርሻ ከያዙት ቅዱሳት መካናት መካከል ይመደባሉ፡፡
መስከረም 29 ቀን 2006 ዓ.ም. በምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ማርቆስ ጥሪ መሠረት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የሚመራና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የሚገኙበት የልዑካን ቡድን መርጡለ ማርያም ገዳም አዲስ ለሚሠራው ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን የመሠረት ድንጋይ ለማኖር፤ እንዲሁም በደብረ ወርቅ ማርያም ገዳም የተገነባውን መንበረ ጵጵስና ለመመረቅና ለዘመናዊ ትምህርት ቤት ግንባታ የመሠረት ድንጋይ ለማኖር ከሄደው ልዑክ ጋር ተጉዣለሁ፡፡