ሦስቱ ነገሥታት
ኢየሩሳሌም ከተማ ከወትሮው በተለየ መልኩ የፍርሃት ድባብ ተንጸባርቆባታል፤ በንጉሥ ሄሮድስ ቤተ መንግሥት ዙሪያ በሠራዊቱና በቤተ መንግሥቱ የቅርብ ሰዎች የሰሞኑ ወሬ የሦስቱ ነገሥታት ጉዳይ ነው፡፡ ከሩቅ ምሥራቅ ሠራዊቶቻቸውን አስከትለው የመጡት ማንቱሲማር፣ በዲዳስፋ፣ እና ሜልኩ የተባሉ ነገሥታት በእስራኤል ምድር መምጣታቸው ብቻ ሳይሆን ተወልዷል ለተባለው ንጉሥ እጅ መንሻ ለመስጠት እንደመጡ መናገራቸው ንጉሥ ሄሮድስን ቅር አሰኝቶታል፤ ፍርሃት በልቡ እንዲነግሥም አድርጎታል፡፡…