ትሩፋን

ኀዳር ፳፮፤፳፻፲፰ ዓመተ ምሕረት

 ቅዱሱ መጽሐፍ ትሩፋን ከጦርነት፣ ከስደት፣ ከምርኮ የተረፉትን ሰዎች እንደሚያመልክት ይነግረናል፡፡ “ትሩፍ” ጥሬ ቃሉ “የቀረ፣ የተረፈ፣ ቀሪ፣ ትርፍ” የሚል ትርጓሜ አለው፡፡ (መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ፣ ገጽ ፱፻፫) ናቡከደነፆር እስራኤልን ወደ ባቢሎን ማርኮ ከወሰዳቸው ከሰባ ዘመን በኋላ በባቢሎን የቀሩት ከተማረኩት ሽማግሎች ትሩፋን ይባላሉ። በንጉሡ ዘመነ መንግሥት ከኢየሩሳሌም ተማርከው ሰባ ዘመን በፋርስ በባቢሎን የሚኖሩ የእስራኤል ሕዝብ ትሩፋነ ባቢሎን እንደሆኑም መጽሐፍ ያስረዳናል። (ዕዝራ ፪፥፩)

በተለያዩ ዘመናት በአንድም በሌላ ምክንያት በሰዎች፣ በጎሳ፣ በማኅበረሰብ ዘንድ እንዲሁም በሀገራት መካከል በሚከሰት ጦርነት እልቂት አልያም የግፍ ግድያና ጭፍጨፋ የተነሣ የብዙዎች ሕይወት ይጠፋል፤ ታሪክ ለዚህ ቀደምት ምስክር እንደሆነ የምናውቀው እውነት ነው፡፡ የጦርነት ወሬ ደግሞ ለእኛ አዲስ የሆነ ነገር አይደለም፡፡ እራሱ ጌታ በወንጌል ሲናገር  ‹‹ጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠበቁ፤ አትደንግጡ፤ ዳሩ ግን መጨረሻው ገና ነው። ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፥ ራብም ቸነፈርም የምድርም መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል›› እንዳለው ምድር ላይ እነዚህ ሁሉ መከራዎች እየተከሰቱ እንደሆነ ለማንም የተደበቀ አይደለም፡፡ (ማቴ.፳፬፥፮-፯)

ታዲያ የጦርነት አስከፊ ገጽታው እንጂ መልካም ጎኑ ምን አልባት እርሱ ባወቅና በፈቀደ ጠላትን ከሀገር የማስወጣቱ ተግባር ነው፡፡ በዚህም አብዛኛዎቻችን ጦርነትን በውዴታ ሳይሆን በግዴታ የምንቀበለው ነው፡፡ ከሁሉም አስከፊው ደግሞ ቤተሰቦቻቸውን፣ ዘመድ አዝማዳቸውንና ወዳጆቻቸውን የሚያጡ ትሩፋን የሚገጥማቸው ሥቃይና ጉዳት ነው፡፡ በአንድ በኩል ከአሰቃቂ ግድያ አልያም ከሞት መትረፍ ቢያስደስትም በሌላ በኩል ግን የሚወዱትን ማጣት እጅግ አስከፊ ነው፡፡ ከምንም በላይ ግን የሞት ሞት የሆነው የነፍስ ሞት አሰቃቂ ነው፡፡

ሰዎች ሞትን እንፈራለን፤ የሥጋ ሞት አስጨናቂ እንደሆነ ማንም የማይክደው ሐቅ ነው፡፡ ነገር ግን ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ‹‹ኢትፍርህዎ ለሞት፤ ፍርህዋ ለኃጢአት፤ ሞትን አትፍሩ፤ ኃጢአትን እንጂ›› ይለናል፡፡ ሊያስጨንቀን የሚገባው በኃጢአት ምክንያት የሚመጣብንን የነፍሳችን ሞት እንጂ የሥጋ ሞት ሊሆን እንደማይገባ በዚህ ቃል እንረዳለን፡፡ ‹‹አፈር ነህና ወደ አፈር ትመለሳለህ›› በሚለው አምላካዊ ቃል ሥጋዊ ሞት አይቀሬ በመሆኑም ምንም ለማንቀይረው  ነገር መጨነቁ ጥቅም የለውም፡፡ (ዘፍ.፫፥፲፱) 

የነፍስ እንጂ የሥጋ ጦርነት ትሩፋን ባንሆን እጅጉን ይመረጣል፡፡ ቃሉን ተረድተው፣ በሕጉ ኖረው ትእዛዙን የጠበቁ ጻድቃን ሁሉ በነፍሳቸው አትርፈው ከዚህ ዓለም ድካምና ዕረፍት በክብር እንደተለዩ ቅዱሳት መጻሕፍት ምስክር ናቸው፡፡ (ገድለ ቅዱሳን) አብነት መሆናቸውን ደግሞ በክርስቶስ ክርስቲያን የተባልን የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ሁላችን ማወቅ አለብን፡፡   እውነት ስለሆነው አንድ ጌታና አንዲት እውነተኛ ሃይማኖት ሲሉ መከራን በመቀበል በቀናው መንገድ ተጉዘው መልካም ፍሬን ያፈሩ ቅዱሳን፣ ጻድቃን፣ ሰማዕታት የነፍስ አትራፊዎች/ትሩፋን/ ናቸው፡፡

የልባችን መሻት የሁላችንም ምኞት መሆን ያለበት ይህ ነገር ሆኖ ሳለ፣ በመንፈስ ውጊያ ለማሸነፍ የሚያስችለንን ስንቃችንን ደግሞ ማከማቸት አስፈላጊ በሆነበት ሰዓት፣ እኛ ግን እየተጨነቅን ያለነው በጊዜያዊ ችግርና ወቅታዊ የእርስ በርስ ጦርነት ላለመሞት ነው፡፡ የሥጋዊ ሞትን ፈርተን በምንዘናጋበት ጊዜ ግን ነፍሳችንን እንደ አንበሳ ነጥቀው ሊጥሏት ይችላሉና ይህንን እንፍራ!

ነፍስ ዘለዓለማዊ ስትሆን ሥጋ ግን ጊዜያዊ ነው፤ አላፊ ጠፊ የሆኑ ምድራዊ ነገሮችን ለሟሟላት በሚል በምድር ለመኖር ስንሻ ከሁለት ያጣም የመሆን ሁኔታ ሊኖር ስለሚችል መጠንቀቅ ይገባል፡፡ ስለ ሥጋዊ ሞት ስናስብ መንፈሳዊ ዝለት ያጋጥመናል፤ በዚህም ጊዜ ነፍሳችን ትጎዳለች፤ ታድፋለች፤ ትመነምናለች፡፡

ሰው ጦርነትን ፈርቶ ሊሸሽ ይችላል፤ መሰደደም ሆነ መደበቅም አይከፋም፤ ግን ግልጽ የሆነውን አስከፊ ሁኔታና እየተካሄደ ያለውን ጦርነትም ይሁን እልቂት ማስቆም ካልተቻለ ሃይማኖታችን በሚፈቅድልን ተገቢ መንገድ ድምጻችንን ማሰማቱና መልእክት ማስተላለፍ እንጂ የጠላት ወገን ከሆኑ አካላት ጋር ግብ ግብ መፍጠር አልያም ጦርነት ውስጥ መግባት አላስፈላጊ ነው፡፡ ጠላት ፊት ለፊት መጥቶ ሊገለን ቢፈልግ እንኳን “ማኅተባችንን አንበጥስም” ብለን አንገታችንን ለሰይፍ ሰውነታችንን ለሞት አሳልፈን መስጠት ሰማዕትነት ነው፤ የክብር ሞትም ያሰጠናል፡፡

በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በተለይም በዕረፍት በዓሏ በየወሩ ፳፩ ቀን የሚነበበው መልክአ ማርያም ‹‹ኃጥአን ከታላቅ የደስታ አደባባይ በተሰደዱ ጊዜ ምርኮ እሆንሽ ዘንድ ከእነርሱ ለይተሽ አስቀሪኝ›› ይለናል፡፡ (መልክአ ማርያም) ይህ ድንቅ ጸሎት የሚያመለክተን ከጦርነት ምርኮኝነት ለማምለጥ ማቀድ ሳይሆን ከኃጥአን ጎራ ላለመቆጠር መሻት እንዳለብን እንዲያውም የፍቅር ምርኮ መሆን እንደሚገባ ነው፡፡

ንጽሕት ቅድስት ከምትሆን የአምላክ እናት የተለመነው ይህ መማጸኛ ለሁላችን እንደሚሆን  እናምናለን፡፡ የነፍሳችንን ጥፋት የማይፈልገው አምላካችን አንዲያ ልጁን አሳልፎ ሰጥቶ ያዳነን ክብርት በሆነች እናቱ ድንግል ማርያም ነውና ታማልደን፣ ትለምንልን እና ትራዳን ዘንድ መማጸን የተገባን ነን፡፡ ከጠላት ሰይጣን የመንፈስ ውጊያ እንድታተርፈን፣ ምርኮዎቿ  እንድታደርገንን እንለምናት፡፡

ስብሐት ለእግዚአብሔር

ወለወላዲቱ ድንግል

ወለመስቀሉ ክቡር አሜን!!!

 

በጎ መካሪ

የሰውን ልጅ የውድቀት ታሪክ ስንመለከት፣ የመጀመሪያው መንሥኤ የክፉ ምክር ውጤት እንደሆነ እንረዳለን። አባታችን አዳም የእግዚአብሔርን ሕግ ጠብቆ ለሰባት ዓመታት ያህል በገነት ቢኖርም፣ በሰይጣን ክፉ ምክር ተታሎ እግዚአብሔርን ያህል ጌታ ገነትን የመሰለ ቦታ አጥቷል። ይህ የሆነው በክፉ ምክር ምክንያት ነው። ዛሬም በዚህች ምድር፣ እንደ ጥንቱ ሁሉ፣ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ በክፉ ምክር የሚያታልሉና ላልተገባ ነገር የሚዳርጉ ክፉ አማካሪዎች አይጠፉም።

በተቃራኒው ደግሞ ለበጎ ነገር የሚያነሣሱ፣ ትክክለኛውን መንገድ የሚያሳዩ፣ መርተው ወደ እግዚአብሔር የሚያደርሱ እንደ ሐዋርያው ፊልጶስ ያሉ መልካም አማካሪዎችና የልብ ወዳጆችም ብዙ ናቸው። (ዮሐ ፩፥፵፮-፶፩)

ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት አላችሁ? ክረምቱንስ እንዴት እያሳለፋችሁት ነው? የዚህን ዓመት የትምህርት ጊዜ ጨርሳችሁ ዕረፍት ላይ ናችሁና በዚህ ወቅት ከቤት ስትወጡ፣ ከቦታ ቦታ ስትንቀሳቀሱ በጥንቃቄ መሆን አለበት፡፡ ከበድ ያለ ዝናብ ሲጥል ድንገት ጉዳት ሊያደርስ ስለሚችል ሁሉን በጥንቃቄ ልናደርገው ይገባል፤ ደግሞም ይህንን ወቅት ቴሌቪዥን ብቻ በማየት ወይም በጨዋታ ማሳለፍ የለብንም፤ ለቀጣዩ የትምህርት ዘመን ሊረዱን የሚችሉ መጻሕፍትን ልናነብ ይገባል እንጂ፡፡

ሌላው ደግሞ በአቅራቢያችሁ ባለው ቤተ ክርስቲያን በመሄድ የአብነትና የሥነ ምግባር ትምህርት መማር አለባችሁ፤ ልጆች! ባሳለፍነው የትምህርት ዘመን ጥሩ ውጤት ያላመጣን ካለን በሚቀጥለው በርትቶ በመማርና በማጥናት በመጪው ዓመት የፈተና ወቅት ጥሩ ውጤት ማምጣት ያስፈልጋል፡፡ መልካም!

ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! ባለፈው ስለ መልካም ምግባራት ተምረናል፤ እንዲሁም ከመልካም ምግባራት (ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር) መካከል ስለ ፍቅርና፣ ስለ መታመን ተምረን ነበር፤ ለዛሬ ደግሞ ስለ መታዘዝና ይቅርታ እንማራለን፡፡

‹‹አትጨነቁ…›› (ማቴ.፮፥፴፬)

ሰዎች  መልካምና ክፋ ነገርን ለማሳካት ይጨነቃሉ፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹አትጨነቁ›› ያለን ለክፋትና ለኃላፊው ዓለም ተጨንቀን መፍትሔ ለማናመጣለት ነገር ነው፡፡ (ማቴ.፮፥፴፬) ፈጣሪያችን ለእኛ ለልጆቹ በዚህ ምድር በእንግድነት ስንኖር ምን እንደሚያስፈልገን ያውቃል፤ የሚያሻንንም ይሰጠናል፤ እናስብ ዘንድ አስተዋይ አእምሮ ሰጥቶናል፤ ማሰብ ከሚገባን በላይ ደግሞ ልንጨነቅ ስለማይገባ ‹‹አትጨነቁ›› አለ፡፡ አበው በብሂላቸው ‹‹…አስብ እንጂ አትጨነቅ..›› የሚሉን ለዚህ ነው፡፡ በምድር ስንኖር በማሰብ በመጠንቀቅ፣ በመጠበቅ እንደ ርግብ የዋህ እንደ እባብ ደግሞ ብልህ ሆነን ልንኖር ያስፈልጋል፡፡ ልንፈራና ልንጨነቅ እንደማይገባ ግን ክርስትናችን ያስተምረናል፡፡ ጌታችን ለአባቶቻችንን ቅዱሳን ሐዋርያት ስለሚቀበለው መከራ፣ ስለሞቱ ሲነግራቸው ባዘኑ ጊዜ ‹‹…ልባችሁ አይታወክ፤ በእግዚአብሔር እመኑ በእኔም ደግሞ እመኑ…›› በማለት በአንዳች ነገር እንዳይጨነቁ ልባቸው እንዳይታወክ ነገራቸው፡፡ (ዮሐ. ፲፬፥፩)

“እግዚአብሔርን የምትወዱ ክፋትን ጥሉ” (መዝ.፺፯፥፲)

በባሕርይው ፍጹም፣ ቅዱስ፣ ንጹሕ የሆነና ምንም ዓይነት ርኩሰት የማይስማማው አምላካችን እግዚአብሔር መልካም አባት ነው፡፡ ዓለም ሳይፈጠር አስቀድሞ የነበረ፣ አሁን ያለ ወደ ፊትም ዓለምን አሳልፎ የሚኖር በመሆኑም ለዘለዓለም በቅድስና ይኖራል፡፡ ፍጥረቱን በሙሉም በቸርነቱ ከመፍጠሩ በፊት ሲቀደስ ሲለስ ይኖር የነበረ፣ አሁንም በፍጥረቱ እንዲመሰገን፣ እንዲቀደስ፣ እንዲወደስ የፈቀደ፣ ወደፊት ደግሞ በክብር ምስጋና በመንግሥቱ ሊገዛ የሚወድ ፈጣሪያችን ክብሩንና ቅድስናውንም ለፍጥረቱ በተለይም ለቅዱሳን መላእክት እና ሰው የሚያደርግ ነው፡፡ ይህን ሁሉም በቸርነቱ፣ በመልካምነቱ፣ በበጎነቱ፣ ስለ ቅዱስ ፈቃዱ አድርጓል፡፡

ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር

ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት አላችሁ? የባለፈው የትምህርት ቆይታችሁ ውጤታችሁ እንዴት ነው? መቼም ጠንክራችሁ ስትማሩ ስለነበር በጥሩ ውጤት እንዳለፋችሁ ተስፋ እናደርጋለን! ወርኃ ክረምቱንስ እንዴት ተቀበላችሁት? እንዴትስ ልታሳልፉት አቀዳችሁ! ይህንን ከወዲሁ ማሰብ አለባችሁ! የዕረፍት ጊዜ ነው ብላችሁ በጨዋታ ማሳለፍ የለባችሁም፡፡ በአቅራቢያችሁ ባለው ቤተ ክርስቲያን በመሄድ በሰ/ት/ቤት በመግባት በአብነት ትምህርቱንና የሥነ ምግባር  ትምህርትን መማር አለባችሁ፤ ውድ ልጆች! ባሳለፍነው የትምህርት ዘመን ጥሩ ውጤት ያላመጣን ካለን በሚቀጥለው በርትቶ መማርና፣ ለማጥናት በመጪው ክረምት ወቅት ማጥናት ያስፈልጋል፡፡ 

ውድ ልጆች! ለዛሬ ያዘጋጀልናችሁ ባለፉት ጊዜያት ስንማራቸው የነበሩትን ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባራትን ክለሳ ነው፤ አሁን የተወሰነውን በቀጣይ ደግሞ ቀሪውን እንማራለን! ታዲያ ጥያቄና መልስ  ለመለሱ ተማሪዎች እንደተለመደው ሽልማት ስለምናዘጋጅ በደንብ አንብቡና ተዘጋጁ፤ መልካም!

ይቅርታ

ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት አላችሁልን? በፈቃደ እግዚአብሔር የጀመርነው የዐቢይ ጾም ሁዳዴ (ጾመ ክርስቶስ) ስድስተኛውን ጨርሰን ስምንተኛው ሳምንት ኒቆዲሞስ ላይ እንገኛለን፡፡ በአቅማችሁ በመጾም በጸሎት በርቱ!

ቤተ ክርስቲያንም ሄዳችሁ መንፈሳዊ ትምህርትን መማር አትዘንጉ! ዘመናዊ ትምህርታችሁንም ቢሆን በርትታችሁ ተማሩ! የሁለተኛው መንፈቀ ዓመት እየተገባደደ ነው! በርትታችሁ አጥኑ! ያልገባችሁን ጠይቁ! አብዛኛውን ጊዜያችሁን በትምህርታችሁ ላይ ትኩረት አደርጉ!፤ መልካም! በዛሬው ክፍለ ጊዜ  “ይቅርታ” በሚል ርእስ እንማራለን፡፡

አገልግሎቴን አከብራለሁ!

ሕንጻ ቤተ ክርስቲያንን እንዲሁም መንፈሳዊ ተቋማትን ለመገንባት ከሚቻልባቸው መሠረታዊ ተግባራቶች የምሕንድስና ሙያ ቀደምት ተጠቃሽ እንደመሆኑ በሀገራችን እንዲሁም በውጭ ሀገር ለሚገኙት የቤተ ክርስቲያናትና አድባራት ግንባትና መልሶ ማቋቋም ሥራ መሐንዲሶች እጅጉን ተፈላጊዎች ናቸው፡፡ በተለይም በሀገራችን ውስጥ ያሉ ቤተ ክርስቲያናት በጠላቶች ሥውር ደባና ጥቃት፣ ምዝበራ፣ ቃጠሎ እንዲሁም መራቆት የደረሳበቸው በመሆኑ እነዚህን ቤተ ክርስቲያናት መልሶ ለመንባትና አዳዲሶችን ለማነጽ በታቀደው ሥራ መሠረት የማኅበረ ቅዱሳን የምሕንድስና ባለሙያዎች ሰፊ አገልግሎት አበርክተዋል፡፡

የኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂን በማበልጸግም ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚውሉ በርካታ ድረ ገጾችን አዘጋጅቶ በማቅረብ ለስብከተ ወንጌል ተደራሽነትና ለመንፈሳዊ አገልግሎት ጥንካሬ ለመጨመር ጉልህ አስተዋጽኦ እያደረገ ነው፡፡ በመደበኛና በኢ-መደበኛ ዳታቤዝና ሲስተም ዴቨሎፕመንት ባለሙያ በሆኑ አገልጋዮች በመታገዝ ከተካተቱት ዋና ተግባራት በጥቅል ሲገለጽ የኮምፒዩተር ሲስተም እና የመረጃ ቋት ፍሎጎቶች ላይ ተስማሚ ቴክኖሎጂ በመጠቆም፣ በማበልጸግ እና ለብልሽቶች እንዲሁም ለጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ ይሰጣል፡፡

ማኅበራዊ አገልግሎትን በተመለከተ ለምእመናን በልዩ ልዩ መንገዶች ግንዛቤ በመስጠት የማኅበራዊ አገልግሎት ተሳትፏቸውን ያሳድጋል:: ኦርቶዶክሳዊያን በማኅበራዊ አገልግሎት ያላቸው ተሳትፎ እንዲያድግ ስልት ቀይሶ ይተገብራል፤ የከፍተኛ ትምህረት ተቋማት ኦርቶዶክሳዊያን ተማሪዎች በማኅበራዊ፣ በሥራ ፈጠራና በኢኮኖሚ ተጽእኖ ፈጣሪ የሚሆኑበትን ትምህርት ክፍል እንዲመርጡ የተለያዩ ግንዛቤ እና ሥልጠና ይሰጣል::

አገልግሎቴን አከብራለሁ!

ቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ ክርስቲያን ለተባልን ሁሉ መሰብሰቢያችን በመሆኗ ቅድስት ቤታችንን ልናንጽና ልንጠብቅ እንደሚገባ ቅዱስ ቃሉ እንዲህ ሲል አስተምሮናል፡ ‹‹ቤቴንም ሥሩ፡፡›› የእግዚአብሔር ቤት ቅድስናው ተጠብቆና ሥርዓቱ ሳይፋለስ ለሕዝበ ክርስቲያኑ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደሙ ዋጅቶ የመሠረታት ቅድስት ቤቱን በአምሳለ ግብሩ ተምሳሌት ሕንጻ ቤተ ክርስቲያንን እናንጻለን፡፡ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችንን የመገንባት ወይም የማስገንባት ሥራን የማካነወን ተልእኮ ማኅበረ ቅዱሳን ሥራዬ ብሎ የያዘው ተግዳሮት ነው፡፡ ማኅበሩ ለምእመናንና ለአብያተ ክርስቲያናት የሙያ አገልግሎት እንዲሰጥ ዕቅድና ስትራቴጂ በማውጣት በተለይም በገጠር ያሉ አብያተ ቤተ ክርስቲያናትንና ሕንጻ ግንባት ያንጻል፤ ያሳንጻል፡፡ (ሐጌ.፩፥፰)

‹‹እግዚአብሔር ፍቅር ነው›› (፩ኛ ዮሐ.፫፥፱)

ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት አላችሁ? የዓመቱ አጋማሽ ፈተናስ እንዴት ነበር? መቼም በርትቶ ሲማርና ሲያጠና ለነበረ ተማሪ ፈተናው እንደሚቀለው ተስፋ አለን፤ ጎበዝ ተማሪ የሚያጠናው ፈተና ሲደርስ ብቻ አይደለምና! መምህራን ሲያስተምሩ ተግቶ በአግባቡ የሚከታተል ያልገባውን የሚጠይቅ፣ መጻሕፍትን የሚያነብ የበለጠ ዕውቀት ለማግኘት ተግቶ የሚያጠና ነው!

ታዲያ እንደዚህ አድርጎ ትምህርቱን የሚከታተል ጥሩ ውጤትን ያመጣል! እንግዲህ በተለያየ ምክንያት በግማሽ ዓመቱ ፈተና በደንብ ያልሠራችሁ በቀሪው የትምህርት ዘመን በርትታችሁ በማጥናት ዕውቀትን እንድታገኙና ጥሩ ውጤት እንድታመጡ አደራ እንላለን!

ልጆች! ሌላው ደግሞ በመንፈሳዊ ሕይወታችሁም ጎበዞች መሆን አለባችሁ! ቤተ ክርስቲያን በመሄድ ተማሩ! መልካም! ባለፈው ትምህርታችን ‹‹ተስፋ››  በሚል ርእስ  ስለ ተስፋ ተምረናል፤ ዛሬ ደግሞ ስለ ፍቅር እንማራለን!