የምእመናን ድርሻ በቤተ ክርስቲያን

በክርስቶስ ክርስቲያን ተሰኝቶ ክርስቶሳዊ የሆነ ሁሉ የድርሻውን የሚወጣና ሥርዓቱን የሚጠብቅ ከሆነ በዚህ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ክብሯ ልዕልናዋ ተጠብቆ ትኖራለች፣ ረድኤተ እግዚአብሔርና በረከቱ ዘወትር አይለየንም፤ ሀገር ጽኑ ሰላም ትሆናለች፣ በወዲያኛው ዓለምም የዘለዓለምን ርስት መንግሥተ ሰማያትን እንወርሳለን፤ የድርሻችንን የማንወጣና ቸልተኞች የምንሆን ከሆነ ግን የቤተ ክርስቲያንንም የሀገርንም ክብርም ልዕልናም ማስጠበቅ አንችልም፤

‹‹በደስታ በዓልን አድርጉ›› (መዝ.፻፲፯፥፳፯)

ቀናትን ሁሉ ባርኮ የሰጠን አምላካችን እግዚአብሔር ጊዜ የእርሱ ስጦታ በመሆኑ የከበረ ድንቅ ሥራውን ፈጽሞበታል፡፡ በእያንዳንዱ ዕለት ፍጥረታትን ከመፍጠሩ ባሻገር ለምስጋና፣ ለውዳሴ እና ለድኅነት ያከበራቸው በዓላትም አሉት፤ በእነዚህ ዕለታት ቃል ኪዳን አድርጓል፡፡

የቤተ ክርስቲያን በዓላት አከባባር

ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት አላችሁ? እንኳን ከዘመነ ሉቃስ ወደ ዘመነ ዮሐንስ አሸጋግሮ በሰላም ለዚህ ዕለት አደረሳችሁ! ዕንቁጣጣሽ እንዴት አለፈ? መቼም ደስ ብሏችሁ እንዳሳለፋችሁ ተስፋችን ነው!ልጆች! በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን በዓላት እንዴት እንደሚከበሩ እኛም ደግሞ በምን ዓይነት መልኩ በበዓላት ላይ መሳተፍ አንዳለብን ልንነግራችሁ ወደድን፤ መልካም ቆይታ!

የምእመናን ድርሻ በቤተ ክርስቲያን ከምን ይጀምራል?

ቤተ ክርስቲያን የሁላችንም ቤት ናት፡፡ በቤታችን ሁላችንም የሥራ ድርሻ እንዳለን ሁሉ በመንፈሳዊት ቤታችን በቤተ ክርቲያንም እንዲሁ ሁላችንም ድርሻ ሊኖረን ይገባል፡፡ ቤተ ክርስቲያን የሊቀ ጳጳሳት፣ የካህናት እና በቤተ ክርስቲያን በአስተዳደር ሥራ ላይ የተሠማሩ ሰዎች ቤት ብቻ ሳትሆን የሁላችንም ቤት ናት፡፡

“ተዘጋጅታችሁ ኑሩ’’ (ማቴ.፳፬፥፵፬)

ጌታች አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱሳን ደቀ መዛሙርቱ የነገራችው ኃይለ ነው፤ ‘’ጌታችሁ በምን ሰዓት እንደሚመጣ አታውቁምና እንግዲህ ንቁ፤ እወቁ ባለቤት ሌሊት ሌባ በየትኛው ጊዜ እንደሚመጣ ቢያውቅ ኖሮ በነቃ፤ ቤቱንም እንዲቆፈር ባልተወ ነበር’’ አላቸው፡፡ ስለዚህ እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፤ የሰው ልጅ በማታስቡት ሰዓት ይመጣልና፤

ጾመ ፍልሰታ ለማርያም

ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት ናችሁ? የክረምቱን ወቅት ምን ቁም ነገር እየሠራችሁበት ነው? ወደ ቤተ ክርስቲያን በመሄድ መንፈሳዊ ትምህርት እየተማራችሁ እንደሆነ ተስፋ እናደርጋለን፤ ልጆች! ለዛሬ የምንማረው ስለ ፍልሰታ ጾም ነው፤

‹‹በልቅሶ የሚዘሩ በደስታ ይሰበስባሉ›› (መዝ.፻፳፭፥፭)

የሰው ልጅ በዚህ ምድር ከሚፈራረቁበት የስሜት ነጸብራቆች ዋነኞቹ ኀዘን (ልቅሶ)ና ደስታ ናቸው። እርግጥ ነው እግዚአብሔር የሰውን ልጅ የፈጠረው እያመሰገነው በደስታ ይኖር ዘንድ ነበር፡። ስለዚህም እግዚአብሔር ሰውን የሚያስፈልገውን ሁሉ ካዘጋጀለት በኋላ በአትክልት ሥፍራ ኤደን ገነት በደስታ እንዲኖር አስቀመጠው፡፡ ነገር ግን የሰው ልጅ በገዛ ፈቃዱ ደስታ የሚሰጠውን ሕግ አፍርሶ የደስታ ምንጭ የሆነውን እግዚአብሔርን አጣ፤ በማጣት ብቻም አልቀረም ‹‹…ስለዚህ የተገኘባትን መሬት ያርስ ዘንድ እግዚአብሔር አምላክ ደስታ ከሚገኝባት ገነት አስወጣው…›› (ዘፍ. ፫÷፳፫)። የሰው ልጅ በድሎ ከኤደን ገነት ወደ ምድር (ዓለመ መሬት) ከመጣ በኋላ እግዚአብሔርን አሳዝኖ ጸጋውን አጥቷልና በሕይወቱ ኀዘን (ልቅሶ) ሰፊውን ጊዜ የሚወስድበት ፍጡር ሆነ። ለ፭ሺ ፭መቶ ዘመን የሰው ልጅ ፍጹም በሆነ ኀዘን ውስጥ ከኖረ በኋላ እግዚአብሔር ወልድ በተለየ አካሉ ሥጋን ተዋሕዶ በመገለጥ ለአዳም (ለሰው ልጅ) ካሣ በመሆን ወደ ፍጹም ደስታ መልሶታል።

ተስፋ

ሕይወታችን ያለ ተስፋ ባዶ ነው፤ ያለ ተስፋ መኖር አንችልም፤ ተስፋ ከሌለን ማንኛውንም ዓይነት የኑሮ ገጠመኝና ችግር ማሳለፍ አይቻለንም፡፡ የሰው ልጆች ዋነኛው ብርታት ተስፋ ማግኘትና በተስፋ መኖር ነው፡፡ የመጀመሪያው ሰው አዳም የአምላካችን የእግዚአብሔርን ሕግ ተላልፎ አትብላ የተባለውን ዕፀ በለስ ከበላ በኋላ የሞት ፍርድ ተፈርዶበት በምድር ላይ ሲኖር በኀዘንና በጭንቅ ነበር፡፡ ሆኖም ግን ፈጣሪ የልቡን ጭንቀትና ኀዘን ተመልክቶ ሊምረው ስለወደደ ከልጅ ልጁ ተወልደ እንደሚያድነው ቃል ገባለት፡፡ ይህም ለአዳም ትልቅ ተስፋ ስለነበረ ትንቢቱ ይፈጸም ዘንድ በተስፋ ጠብቋል፡፡

‹‹ትዕግሥትን ልበሱ›› (ቈላ.፫፥፲፪)

በሕይወታችን ውስጥ እጅጉን አስፈላጊ መጨረሻውም አስደሳች የሆነው ነገር ትዕግሥት ነው፤ በማንኛውም ሁኔታና ጊዜ ሆነን የምንጋፈጠውን ችግር፣ መከራና ሥቃይ በብርታትና በጽናት ለማለፍ የምንችለው ትዕግሥተኛ ስንሆን ነው፡፡ መታገሥ ከተቃጣ ሤራ፣ ከታሰበ ክፋት፣ ከበደልና ግፍ ያሳልፋል፤ ልንወጣው ከማንችለው ችግርም እንድንወጣ ይረዳናል፡፡

ትጋት

የክርስቲያናዊ ምግባራችን ጽናት ከሚገለጽባቸው ዋነኞቹ ተግባራት መካከል ትጋት አንዱ ነው፡፡ ጸሎትን፣ ጾምንና ስግደትን በማብዛት የሚገለጸው ትጋታችን ክርስትናችንን የምናጠነክርበት ምግባራችን ነው፡፡ ዘወትር ሥርዓተ ጸሎትና ጾምን ጠብቀን መኖራችን በመንፈሳዊ ሕይወታችን ጠንክረንና ማንኛውንም ፈተና አልፈን እንድናንጓዝ ይረዳናልና ትጋታችንን ማጠንከር የምንችለው ዕለት ከዕለት ስንጸልይ፣ በሥርዓት ስንጾምና አብዝተን ስንሰግድ ነው፡