ስለ ቅዱስ ፖትርያርኩ ሥርዓተ ቀብር መግለጫ ተሰጠ
ነሐሴ 12 ቀን 2004 ዓ.ም.
እንዳለ ደምስስ
መካነ ድራችን በግልጥ ባልታወቀ ምክንያት የሲስተም ችግር ገጥሞት ስለነበር መረጃዎችን በወቅቱ ማድረስ ባለመቻላችን ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡
የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፖትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት፣ የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም የክብር ፕሬዚዳንት ሥርዓተ ቀብር በማስመልከት ቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ሰጠ፡፡
መግለጫውን የሰጡት ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ዋና ጸሓፊ፣ የከፋ ቤንችና ማጂ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሲሆኑ
በመግለጫቸውም “ቅዱስነታቸው ሐሙስ ነሐሴ 10 ቀን 2004 ዓ.ም. ከንጋቱ 11፡00 ሰዓት ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ መለየታቸውን በዕለቱ መግለጻችን ይታወቃል፡፡ በቀጣይነትም የቅዱስነታቸውን የቀብር ሥነ ሥርዓት አፈጻጸም ጊዜና ቦታ በተከታታይ የሚገለጽ መሆኑን በሰጠነው ማሳሰቢያ መሠረት የቀብር ሥነሥርዓቱ ሐሙስ ነሐሴ 17 ቀን 2004 ዓ.ም. በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንደሚፈጸም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡ እስከዚያው ድረስ ምእመናንና ምእመናት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ስብከተ ወንጌል አዳራሽ በመገኘት ሃዘናቸውን መግለጽ የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን” ብለዋል፡፡
ስለ አሟሟታቸው ማብራሪያ እንዲሰጡ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄም ቅዱስነታቸው ሱባኤውን ሳያቋርጡ እሑድ ቀድሰው ሰኞና ማክሰኞም ቅዳሴውን እየመሩ መገኘታቸውንና ከሰዓት በኋላ ህመም ስለተሰማቸወ ወደ ሕክምና መሔዳቸውን የገለጹ ሲሆን እረፍት እንዲያደርጉ በሐኪም ከተነገራቸው በኋላ በዚያው የእግዚአብሔር ጥሪ ሆኖ ሌሊት 11፡00 ሰዓት ላይ ማረፋቸውን ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም ስለ ቅዱስነታቸው ሕመም ሲያብራሩ “ብዙ ታመው ቤት አልዋሉም፡፡ ሥራም አላቋረጡም፣ ያልታሰበ ነገር ስለነበር በሞታቸው በጣም ተደናግጠናል፡፡ ሕመማቸው የስኳር ሕመም ጠንቅ ነው፡፡ ቀዶ ጥገናም አልተደገላቸውም በትናንትናው ዕለት እኔ ነኝ አጥቤ የገነዝኳቸው፡፡” በማለት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
የሥርዓተ ቤተ ክርስቲያኑ ቀኖና እንደሚያዘው አንድ ፖትርያርክ ሲያርፍ አቃቤ መንበር በዕለቱ መሠየም እንዳለበት ይገልጻልና ይህ ለምን ተፈጻሚ አልሆነም? ለሚለው ጥያቄ ምላሽ የሰጡ ሲሆን በጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ በፓትርያርኩ ጽ/ቤት ሓላፊ እንዲሁም በቅዱስ ሲኖዶስ ጸሐፊ አማካይነት ሥራዎች እንደሚከናወኑ፣ ከቅዱስ ፖትርያርኩ የቀብር ሥነ ሥርዓት በኋላ አቃቤ መንበር እንደሚሰይምና ይህም በመመካከርና በመስማማት ውሳኔውን መወሰናቸውን አብራርተዋል፡፡
ቅዱስ ሲኖዶስ ቤተ ክርስቲያኑን ለመምራት ምን ያህል ዝግጁ ነው? ለሚለው ጥያቄ ሲመልሱም “ይህ ጸሎት የሚጠይቅ ነው፡፡ እግዚአብሔር
እየረዳን፣ በምዕመናን ጸሎት እየተረዳን የተቻለንን ሁሉ እንጥራለን፡፡” ያሉ ሲሆን ከሰሜን አሜሪካ ካሉ አባቶች ጋር እየተካሄደ የነበረው እርቀ ሰላም እንደሚቀጥል አጽንኦት ሰጥተው ገልጸዋል፡፡
የቅዱስነታቸው የቀብር ቦታን አስመልክቶ እንዳልተናዘዙና በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት ከልጅነታቸው ጀምሮ በቅስና እያሉ ባገለገሉበት፣ በተማሩበት፣ ከእስር ቤት ከተፈቱ በኋላ ክብር ባገኙበት በመንብረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንዲሆን ተወስኗል” ብለዋል፡፡
የቅዱስ ፖትርያርኩ ሥርዓተ ቀብር ዝርዝር መረጃም እንደሚከተለው ሰጥተዋል፡፡
- ረቡዕ ነሐሴ 16 ቀን 2004 ዓ.ም. ከሰዓት በኋላ የቅዱስነታቸው አስከሬን ከመንበረ ፓትርያርክ በግልጽ ሠረገላ ወደ መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ያመራል፡፡
- ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ ጸሎተ ፍትሀት እየተከናወነ ያድራል፡፡
- ሌሊት ሥርዓተ ቅዳሴ በሦስቱም መንበር በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ይቀደሳል፡፡
- ከሥርዓተ ቅዳሴ በኋላ አስከሬናቸው ወደ ዐውደ ምሕረት በማውጣት ምዕመናን በተገኙበት ጸሎተ ፍትሀቱ ይቀጥላል፡፡
- ከውጭ ሀገር የመጡ የአኀት ቤተ ክርስቲያናት ፖትርያርኮች ተገኝተው ንግግር ያደርጋሉ፡፡
- የመንግሥት ባለ ሥልጣናት ንግግር ያደርጋሉ፡፡
- የቅዱስነታቸው የሕይወት ታሪክ በቅዱስ ሲኖዶስ በተፈቀደላቸው ሊቀ ጳጳስ ይነበባል፡፡
- አስከሬናቸው በቤተ ክርስቲያኑ ዑደት ያደርጋል፡፡
- በመጨረሻም ሥርዓተ ቀብራቸው ይፈጸማል፡፡





የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ሊቀ ትጉኀን ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ሥዩም በነሐሴ ወር የሚደረገውን የማኅበሩን ጠቅላላ ጉባኤ አስመልክተው እንደገለጹት ማኅበረ ቅዱሳን ያከናወናቸው የ20 ዓመት ጉዞዎች በጠቅላላ ጉባኤው ላይ አንሥቶ እንደሚገመግም ገልጸዋል፡፡
ያደረገው በ2004 ዓ.ም. መሪ እቅዱ መሠረት መሆኑን የጠቀሱት የክፍሉ ሓላፊ ወይዘሪት መቅደስ ዓለሙ፤ “ይህንን ለማቀድ ምክንያት የሆነን አባቶቻችን ከሰፊ የአገልግሎት ዘመናቸው በኋላ የሚታሰብላቸው የጡረታ አበል አለመኖሩ ነው፡፡ አብዛኛዎቹ አባቶችም በቅርብ የሚረዳቸውና የሚንከባከባቸው ሰው የሌላቸው ናቸው፡፡ ስለሆነም ምንም ዓይነት አገልግሎት እንዳልሰጡ በቂ ትኩረት ተነፍጓቸውና ተረስተው በየመቃብር ቤቱና ንጽሕና በተጓደለባቸው ሥፍራዎች ወድቀው የሚገኙትን አባቶች፤ ከሰንበት ትምህርት ቤቶች ጋር በመተባበር ባካሄድነው ጥናትና ባገኘነው መረጃ መሠረት መርጠን ረድተናል፡፡” በማለት ምክንያቱን አስረድተዋል፡፡
ምእመን ቤት ተጠግተው ለሚኖሩ አንድ አባት ሙሉ የሕክምና ወጪ በመሸፈን እንዲታከሙ አድርጓአል፡፡
በሦስት ሔክታር መሬት ላይ ጤፍ ለመዝራት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት መደረጉን ያወሱት የአገልግሎት ክፍሉ ኃላፊ ወይዘሪት መቅደስ “መሬቱን በትራክተር ከታረሰበት ከመጀመሪያው ቀን አንስቶ ለሦስት ተከታታይ ጊዜያት የአከባቢው ገበሬዎች አርባ ጥማድ በሬዎቹን ይዘው እንዲሁም፤ ምእመናን በገንዘባቸውና በጉልበታቸው አማካኝነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል፡፡ … ከደብሩ አስተዳደር ጀምሮ ሌሎችም መደበኛ አገልጋዮችና ምእመናን ለቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ እድገት በጋራ እንሥራ የሚለውን መርሕ የተቀበሉ ናቸው፡፡ ይህም በሌሎች ቦታዎች ለሚገኙ የቤተ ክርስቲያን አካላት መልካም ተሞክሮ ነው፡፡” በማለት በማጠቃለያ መልእክታቸው በፕሮጀክቱ ትግበራ ላይ የተባበሩትን ሁሉ አመስግነዋል፡፡
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሚገኘው የደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤት ያዘጋጀው መርሐ ግብር ከሐምሌ 12 እስከ ሐምሌ 15 ቀን ተካሄደ፡፡ ዝግጅቱ በሁለት ዐበይት ክፍሎች ተከፍሎ የተካሄደ ሲሆን፡- ይህም ከመክፈቻው ሐምሌ 12-14 በዐውደ ርዕይ፣ እንዲሁም ሐምሌ 15 ቀን 12 ሰንበት ትምህርት ቤቶች የተሳተፉበት መንፈሳዊ መርሐ ግብር የቀረበበት መሆኑ ታውቋል፡፡
“ሰንበት ትምህርት ቤታችን ከዚህ ቀደም የተለያዩ ዐውደ ርዕዮችን ያዘጋጀ ሲሆን ሕፃናትን በተመለከተ ግን ይህ ዐውደ ርዕይ የመጀመሪያው ነው፡፡ ሕፃናትን የተመለከተ ዐውደ ርዕይ እንድናቀርብ የተፈለገበት ዋነኛው ምክንያት ተገቢውን ትኩረት ለሕፃናት እንዲሰጥ ለመቀስቀስ ነው፡፡” በማለት ዐውደ ርዕዩ በሕፃናት ዙሪያ እንዲከናወን ምክንያት ስለሆነው ሁኔታ ያስረዳው ወጣት ዮሐንስ መረቀኝ የደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤት ምክትል ሰብሳቢ ነው፡፡

ምእመናን ተጠቃሚ በሚሆኑበት ሁኔታ ላይም ተወያይቶ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ለተፈጻሚነታቸው በማእከሉ ስር ላለው ቅዱሳት መካናት ልማትና ማኅበራዊ አገልግሎት ክፍል ከባድ ኃላፊነት ሰጥቷል። የጉባኤውን ከፍተኛ ትኩረት አግኝቶ ሰፊ ውይይት የተደረገበት ሌላው አጀንዳ “የአውሮፓ ማእከል አባላት የአገልግሎት ሱታፌ ከማኀበረ ቅዱሳን ተልእኮ አንጻር” በሚል ርእስ የቀረበው ጥናት ነበር። በማእከሉ ሥራ አስፈጻሚ ጉባኤ በተቋቋመው ቡድን ተዘጋጅቶ የቀረበው ይህ ጥናት በሁሉም የአውሮፓ ሀገራት የሚገኙ አባላት በቤተ ክርስቲያን መዋቅር ሥር ታቅፈው በመስጠት ላይ ያሉትን አገልግሎት የዳሰሰ፣ ጥንካሬዎችንና ድክመቶችን ነቅሶ ያወጣ፣ ወደፊት ሊደረግ የሚገባውን ያመላከተ ሰፊ ጥናት ነበር። ጉባኤው በጥናቱ ላይ ሰፊና ሞቅ ያለ ውይይት አድርጎ ውሳኔዎችን አሳልፏል።
በመጨረሻም ጉባኤው በቀረበለት የቀጣዩ የ2005 ዓ.ም. የአገልግሎት ዘመን ዕቅድ ላይ ተወያይቶ የማሻሻያ ዐሳቦችን በመስጠት ካጸደቀ በኋላ ማእከሉን ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት የሚመራ አዲስ የሥራ አስፈጻሚ ጉባኤ መርጦ የጉባኤው ፍጻሜ ሆኗል። ማእከሉ ስምንት የግንኙነት ጣቢያዎች እና አምስት ቀጠና ማእከላት ያሉት ሲሆን በስዊድን ቀጠና ማእከል የተዘጋጀው የዘንድሮው ጉባኤ የተሳካ እንደነበር የጉባኤው ተሳታፊዎች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ቀጠና ማእከሉ ለጉባኤው መሳካት አስተዋጽዖ ያደረጉትን አባላትና ምእመናን እንዲሁም ተቋማት በተለይ ጉባኤው በተመቼ ሁኔታ ይካሄድ ዘንድ መሰብሰቢያ አዳራሽና የተሳታፊዎችን ማረፊያ ቤት ከሙሉ አገልግሎት ጋር በነጻ የሰጠውን በብሬድንግ የስዊድን ቤተ ክርስቲያን አመስግኗል።