ኒቆዲሞስ/ለሕፃናት/
መጋቢት 21 2004ዓ.ም
በቴዎድሮስ እሸቱ
እንደምን ሰነበታችሁ ልጆች? ደህና ናችሁ? መልካም ይኸው ዘወረደ ብለን በመጀመሪያው ሳምንት የጀመርነው ጾም ዛሬ ኒቆዲሞስ ላይ ደርሷል፡፡ ኒቆዲሞስ የ7ኛው ሳምንት መጠሪያ ነው፡፡

ልጆች የአይሁድ መምህር የሆነ አንድ ኒቆዲሞስ የሚባል ሰው ነበር፡፡ ይህ የአይሁድ መምህር ማታ ማታ እየመጣ ከክርስቶስ እግር ስር ቁጭ ብሎ ትምህርት ይማር ነበር፡፡ ልጆች ማታ ማታ እየመጣ የሚማረው ለምን መሰላችሁ፡፡
አንደኛ የአይሁድ መምህር ስለሆነ ሲማር እንዳያዩት ነው፡፡ ሲማር ካዩት ገና ሳይማር ነው እንዴ የሚያስተምረን እንዳይሉት፡፡ ሁለተኛ አይሁድ ክርስቶስን ያመነና የተከተለ ከሀገራችን /ከምኲራባችን/ ይባረራል ብለው ስለነበር እንዳይባረር ፈርቶ ሦስተኛ ደግሞ ሌሊት ሲማሩ ምንም የሚረብሽና ዐሳብን የሚሰርቅ ነገር ስለሌለ ትምህርት በደንብ ይበገባል ብሎ በማሰብ ነው፡፡ እናንተስ በሌሊት ትምህርታችሁን የምታጠኑት እንዲገባችሁ አይደል ልጆች? በሌሊት ዐሳባችሁ አይበተንም፡፡
ታዲያ አንድ ቀን ማታ ክርስቶስ ለኒቆዲሞስ ስለ ጥምቀት አስተማረው፡፡ “ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በስተቀር የእግዚአብሔር መንግሥት ሊወርስ አይችልም” አለው፡፡ ኒቆዲሞስም “ሰው ከሸመገለ ካረጀ በኋላ እንዴት ድጋሚ ሊወለድ ይችላል” ብሎ ጠየቀ ክርስቶስ ዳግም ልደት ማለት ሰው በጥምቀት የሚያገኘው የእግዚአብሔር ልጅነት እንደሆነ ሰው ተጠምቆ የእግዚአብሔር ልጅ ካልሆነ መንግሥተ ሰማያትን እንደማይወርስ አስተማረው፡፡ ኒቆዲሞስም ስለ ጥምቀት በሚገባ ተረዳ፡፡
አያችሁ ልጆች እንግዲህ በዚህ ሳምንት ከሚነገረው ታሪክ በርካታ ቁም ነገሮችን እናገኛለን ለምሳሌ እኛ ልጆች የእግዚአብሔርን ቃል ቀን ከሌሊት ሳንል ሁል ጊዜ መማር እንዳለብን፤ ያልገባን ነገር ካለ የቤተ ክርስቲያን አባቶችን ጠይቀን መረዳት እንዳለብን ነው፡፡ እንደዚህ በማድረግ ስለ እምነታችን በቂ እውቀት ልንጨብጥ ይገባናል ማለት ነው፡፡ ለዛሬ አበቃሁ ደህና ሰንብቱ፡፡



ና ሰነበታችሁ ልጆች? እንዴት ናችሁ? በጾሙ እየበረታችሁ ነው አይደል? ጎበዞች፡፡ ዛሬ ስድስተኛው ሳምንት ላይ ደርሰናል፡፡ ይህ ሳምንት ገብርኄር ይባላል፡፡ ገብርኄር ማለት ልጆች መልካም አገልጋይ ማለት ነው፡፡ በዚህ ሳምንት በቤተ ክርስቲያናችን ክርስቶስ ስለመልካም አገልጋይ ያስተማረው ትምህርት ይነገራል፡፡ ይህን የተመለከተ ምስጋናም ይቀርባል፡፡
ይጠይቃቸዋል፡፡ አምስት የተሰጠው አገልጋይ ሌላ አምስት መክሊት አትርፌአለሁ አለው፡፡ ጌታውም አንተ መልካም አገልጋይ ነህ ወርቁን ከነትርፉ ውሰድ ወደጌታህም ደስታ ግባ አለው፡፡ ሁለት መክሊት የተሰጠውም ሌላ ሁለት መክሊት እንዳተረፈ ተናገረ ጌታው እሱንም አንተም መልካም አገልጋይ ነህ በጥቂቱ ታምነሃልና በብዙ እሾምሀለሁ ወደጌታህ ደስታ ግባ አለው፡፡ በመጨረሻም አንድ መክሊት የተሰጠው አገልጋይ መጣ እንዲህም አለ “ጌታዬ አንተ ካልዘራህበት የምታጭድ ያልበተንከውን የምትሰበስብ ክፉ ጌታ መሆንህን አውቃለሁ ስለዚህ ሌቦች እንዳይሠርቁኝ አታላዮች እንዳይቀሙኝ ብዬ መክሊትህን ቀብሬ እስክትመጣ አስቀምጨዋለሁ አሁንም እንካ ይኸው አንድ መክሊትህ” ብሎ ሰጠው፡፡ ጌታውም “አንተ ክፉ አገልጋይ መቼ ነው እኔ ያልዘራሁትን ያጨድኩት፣ ያልበተንኩትን የሰበሰብኩት አሁን ወርቁን ተቀበሉትና ለባለ አምስት መክሊቱ ስጡት እሱን ደግሞ ወደ ዘለዓለም ሃዘንና መከራ ወዳለብት ወደጭለማው አውጥታችሁ ጣሉት” አላቸው፡፡ አገልጋዮችም ይህንን ክፉ አገልጋይ ወደ ጭለማው አውጥተው ጣሉት፡፡

-180x180.jpg)
ሁሉም አባታቸው የሚያወርሳቸውን የራሳቸውን ድርሻ ይዘው ለብቻቸው መኖር ይፈልጉ ነበር፡፡ ከዚያም አንድ ቀን አባታቸው በጠና ታሞ አልጋ ላይ ተኛ ልጆቹንም ጠራቸውና አንድ ትእዛዝ አዘዛቸው ትእዛዙም “ሁላችሁም ሒዱና ለየራሳችሁ አንድ አንድ ጭራሮ ይዛችሁ ኑ” የሚል ነበር፡፡ ከዚያም ልጆቹ ወደውጪ ሔደው ለየራሳቸው አንድ አንድ ጭራሮ ይዘው ተመለሱ፡፡
ታላቁ ልጅም ቢሞክር ቢሞክር ቢታገል ጭራሮዎቹን ሊሰብራቸው አልቻለም ሁሉም ልጆች ቢሞክሩ አንድ ላይ የተሰበሰቡትን ጭራሮዎች ሊሰብሯቸው አልቻሉም ከዚያም አባትየው ልጆቹ ወደእርሱ እንዲጠጉ በምልክት ጠራቸውና እንዲህ ብሎ ነገራቸው፡፡
አንድ ላይ ሲሰበሰቡ ከእናንተ ውስጥ ማናችሁም ልትሰብሩ አልቻላችሁም፡፡ እናንተም የምትለያዩ ከሆነ አንድ ላይ የማትሆኑ ከሆነ ጠላት በቀላሉ ያጠፋችኋል ሌባ ይዘርፋችኋል፤ ጠንካራና ጎበዝ ልትሆኑ አትችሉም፡፡ አንድ ላይ ከሆናችሁ ግን ማንም አይደፍራችሁም፡፡ አሁን እኔ ልሞት ነው የማወርሳችሁን ሀብት በጋራ ተጠቀሙበት በመካከላችሁ መለያየት እንዳይኖር አደራ አላቸው፡፡ ከዚያም ትንሽ ቆይቶ ሞተ እነሱም ከዚያች ዕለት በኋላ ሳይጣሉ እርስ በእርስ በመዋደድ በፍቅር አንድ ላይ መኖር ጀመሩ ተባብረው ስለሚሠሩም ሀብታምና ጠንካሮች መሆን ቻሉ፡፡