ከምርጫው ይልቅ ለቅድመ ምርጫው!!
መስከረም 8 ቀን 2005 ዓ.ም.
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
የረጅም ዘመን ታሪክ ያላት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ይህን ያህል ዘመን ተጉዛ ከዚህ የደረሰችው በተአምር ብቻ አይደለም፡፡ ሁል ጊዜ በጽኑ እምነትና ምግባር እግዚአብሔርን በማመስገንና ሰውን በማገልገል የታወቁ እልፍ አእላፍ ቅዱሳን ካህናትና ምእመናን በውስጧ በመኖራቸው ነው፡፡ በእነዚህ ቅዱሳን አበው በየቦታው ትምህርት ቤቶች እንዲስፋፉና መጻሕፍትም እንዲበዙ የተደረገውም ጥረት ለዚህ ታሪካዊ ዕድገት ያበረከተው አስተዋፅኦ የታሪክ ትዝታ ብቻ ሳይሆን አሁንም በተግባር የሚታይ ሐቅ ነው፡፡

የማኅበረ ቅዱሳን 10ኛ ጠቅላላ ጉባኤ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ስብከተ ወንጌል አዳራሽ ብፁዐን ሊቃነ ጳጳሳት፤ የጠቅላይ ቤተ ክህነት፤ የመምሪያ ሓላፊዎች፤ ቀሳውስትና ካህናት፤ የፌደራል ጉዳዮች የሃይማኖት ተወካዮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ነሐሴ 30 ቀን 2004 ዓ.ም.በድምቀት ተጀመረ፡፡
