‹‹አንተም÷ የሰው ልጅ ሆይ÷ ጡቡን ወስደህ በፊት አኑራት፤ የኢየሩሳሌምንም ከተማ ስዕል ሳልባት፤ ክበባት›› (ሕዝ.፬፥፩)
ቅዱሳት ሥዕላትን ለጸሎት እና ለተለያዩ አገልግሎቶች በምንጠቀምበት ጊዜ ልናስተውላቸው የሚገቡ ነገሮች አሉ፡፡ በዋነኛነትም እንዳይበላሹ እና እንዳይደበዝዙ በክብር ማስቀመጥ አስፈላጊ ነው፡፡ ሥዕላቱ የሚገልጹት የሥዕሉ ባለቤት የሆነውን አምላክ ወይም ቅዱስ፤ ጻድቅ ወይም ሰማዕት ስለሆነ ተገቢውን ክብር እና ሥርዓተ አምልኮ ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡ ምእመናን ትክክለኛዎቹን የሥዕሉን ባለቤቶች አውቀው እንዲያከብሩ እና እንዲማጸኑባቸው ሠዓሊዎች የሚሥሉትን ቅዱስ ሥዕል በትክክል መሣልም አለባቸው፡፡