ምሥጢረ ቊርባን
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! እንዴት አላችሁልን! በዓለ ሃምሳ ተብሎ የሚታወቀውን ወቅት እንዴት አሳለፋችሁት? እንኳን ለብርሃነ ዕርገቱ እንዲሁም ደግሞ ለበዓለ ጰራቅሊጦስ አደረሳችሁ! አሁን ደግሞ በተለምዶ የሰኔ ጾም እየተባለ የሚታወቀው ጾመ ሐዋርያት ሰኔ ፲፯ (ዐሥራ ሰባት) ቀን ይጀምራል፡፡ ከወዲሁ እንኳን አደረሳችሁ እንላለን!
ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! በሰንበት (በዕረፍት ጊዜያችሁ ሄዳችሁ) ቤተ ክርስቲያን በመሄድ ማስቀደስ እንደሚገባ፣ መጾም መጸለይ እንዳለብን መዘንጋት የለብንም! በዘመናዊ ትምህርታችሁም ሁለተኛውን መንፈቀ ዓመት ጨርሳችሁ የማጠቃለያ ፈተና የተፈተናችሁ አላችሁ! እንዲሁም ደግሞ እየተፈተናችሁም ያላችሁ ትኖራለችሁና በርትታችሁ ማጥናት ሥሩ! መልካም! አሁን ለዛሬ ወዳዘጋጀንላችሁ ትምህርት እናምራ፤ ባለፈው ምሥጢረ ጥምቀትን ተምረን ነበር፤ ዛሬ ደግሞ የምሥጢረ ቊርባንን ትምህርት እንማራለን፤!
