እንኳን ለብዙኃን ማርያም እና ለመስቀል በዓል አደረሳችሁ !!!
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
እንኳን ለብዙኃን ማርያም እና ለመስቀል በዓል አደረሳችሁ !!!
መስከረም ፳፩ ቀን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዐት መሠረት ስለ ሁለት ነገረ በዓሉ ይከበራል ።
፩ኛ. በመስቀል በዓል ጽሑፋችን እንደገለጽነው የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በንግሥት እሊኒ ከተቀበረበት ወጥቶ የከበረበት እና ከእስክንድሪያ ዓፄ ዳዊት ግማደ መስቀሉን ይዘው ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ስናር በተባለ ቦታ በማረፋቸው ልጃቸው ዓፄ ዘርዓያቆብ ተረክቦ ፲፬፻፵፮(1446) ዓ.ም መስከረም ፳፩ ቀን በግሸን ደብረ ከርቤ በመስቀለኛ ቦታ ላይ እግዚአብሔር በገለጠላቸው ራእይ በመመራት በሀገራችን በክብር ያረፈበት ዕለት ነው።
፪ኛ. አባቶቻችን ፫፻፲፰ (318)ቱ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ለአውግዞተ አርዮስ የተሰበሰቡበት ዕለት ነው።
በዚህም ምክንያት የአባቶቻችንን ለጉባኤ መሰባሰብ ለመግለጽ “ብዙኃን ማርያም” ይባላል ።
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት፣የቅዱስ መስቀሉ በረከት፣የአባቶቻችን ጽኑ ሃይማኖት አይለየን አሜን።
👇👇👇👇👇👇👇
የማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ሚዲያ አውታሮች ይቀላቀሉ
ቴሌግራም፡- http://t.me/mkpublicrelation
የማኅበረ ቅዱሳን ሕዝብ ግንኙነት:-https://www.facebook.com/mahiberekidusan.mkusa/
ድረገጽ፡- http://www.eotcmk.org
ዩ ቲዩብ፡- http://www.youtube.com/user/EOTCMK
:- https://www.youtube.com/@-zemawetibebzmk7905
