ginbot hamer 1

ሐመር መጽሔት በግንቦት ወር እትሟ….!

ginbot hamer 1

ማኅበረ ቅዱሳን የቴሌቪዥን ሥርጭት አገልግሎቱን በይፋ መጀመሩን አበሰረ

ግንቦት 16 ቀን 2005 ዓ.ም.

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲየን ማኀበረ ቅዱሳን ላለፉት ሃያ ዓመታት በመንፈሳዊ መገናኛ ብዙኃን ሲሰጥ የቆየውን አገልግሎት በማስፋት የቴሌቪዥን ሥርጭት በኦፊሴል መጀመሩን ለምእመናን የሚያበስርበት ጉባኤ ቅዳሜ ግንቦት 17 ቀን 2005 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ስብሰባ ማእከል እንደሚያካሂድ ተገለጸ፡፡

ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ምእመናንና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በሚሳተፉበት በዚህ ጉባኤ ማኅበሩ ዐቢይ ተልዕኮ አድርጎ ይዞት የተነሣውን የስብከተ ወንጌል አገልሎት ለማሳካት መንፈሳዊ መገናኛ ብዙኃንን እንዴት ሲጠቀም እንደቆየና በዘርፉ አገልግሎቱን ለማጠናከር ያለው ዕቅድ በብሮድ ካስት መገናኛ ብዙኃን የቴሌቪዥን ሥርጭት አገልግሎትን ለምን እንደጀመረ፣ ወደፊትም አጠናክሮ ለመቀጠል ያለውን ዕቅድና በአገልግሎቱ ምእመናን ሊኖራቸው ስለሚገባው ተሳትፎ መነሻ የሚሆኑ አሳቦች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው ተጠቁሟል፡፡

ማኅበሩ ከየካቲት 16 ቀን 2005 ዓ.ም. ጀምሮ በኢ.ቢ.ኤስ ቴሌቪዥን ሥርጭት ጣቢያ በየሳምንቱ እሑድ ከረፋዱ 5፡30 እስከ 6፡00 እና ሐሙስ ከጠዋቱ 1 ሰዓት እስከ 1፡30 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ትምህርተ ሃይማኖት፣ ሥርዓተ እምነትና ትውፊት የሚያስተላልፉ ዝግጅቶችን እንደሚያቀርብ ይታወቃል፡፡

img 0442

የቅዱስ ያሬድ 1500ኛ ዓመት መታሰቢያ በድምቀት ተከበረ

ግንቦት 13 ቀን 2005 ዓ.ም.

በእንዳለ ደምስስ

img 0442የቅዱስ ያሬድ 1500ኛ ዓመት መታሰቢያ በዓል “ሕያው ዜማከ ወሕያው ድርሳንከ” በሚል መሪ ቃል ስድስት ኪሎ በሚገኘው የኢትዮጵያ ስብሰባ ማእከል አዳራሽ ግንቦት 11 ቀን 2005 ዓ. ም. በድምቀት ተከብሯል፡፡

ከየአድባራቱና ገዳማት የመጡ ታላላቅ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም ምእመናን የተገኙ ሲሆን የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ቀሲስ ዶክተር ሰሙ ምትኩ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የታሪክ ትምህርት ክፍል መምህር በሆኑት ዶክተር ውዱ ጣፈጠ በቅዱስ ያሬድ ሕይወት ታሪክና ሥራዎቹ ላይ ያተኮረimg 0335 ጥናት አቅርበዋል፡፡ ከሊቃውንቱ መካከልም በጎንደር መንበረ መንግሥት መድኀኔዓለም የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪና የአራቱ ጉባኤያት የመጻሕፍት መምህር ሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ አዲስ የወንጌል ትምህርት ሰጥተዋል፡፡ ከሊቃውንቱ መካከል የቤተልሔም፤ የቆሜና የአጫበር ዜማዎችን በየተራ ያቀረቡ ሲሆን የመርሐ ግብሩ ልዩ ድምቀት ነበር፡፡

በራስ ዳሸን ተራራ ላይ በችግር ውስጥ የሚገኘው የቅዱስ ያሬድ ገዳምን ለመርዳት የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር የተደረገ ሲሆን የማኅበረ ቅዱሳን የቅዱሳት መካናት ልማትና ማኅበራዊ አገልግሎት ክፍል እጅግ አስቸጋሪና የአንድ ቀን ሙሉ የእግር ጉዞ በማድረግ የሚደረስበትን በበረዶ የተከበበው ገዳም ድረስ በመሄድ ገዳሙ ያለበትን ችግር ለማጥናት ጥረት ማደረጉ ተገልጻል፡፡

በገዳሙ ከ70 በላይ መነኮሳትና መናንያን የሚገኙ ሲሆን ከቦታው ተራራማነት የተነሳ ምእመናን የማይደርስበት ቦታ በመሆኑ ገዳማውያኑ የሚረዳቸው በማጣት የአልባሳት፤ የምግብና የመጠለያ ችግር እንዳጋጠማቸው ተጠቅሷል፡፡ በዚህም መሠረት ማኅበረ ቅዱሳን ከገዳሙ አቅራቢያ በ100 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ደባርቅ ከተማ ላይ ለገዳሙ አገልግሎት የሚውል የአንድ ሺሕ ካሬ ሜትር ቦታ ከከተማው አስተዳደር በመረከብ ሕንፃ ለመገንባት ፕሮጀክት ቀርጾ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ በመጀመሪያው ዙርም 1.5 ሚሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ በመገለጹ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብሩ ተካሂዷል፡፡

በዕለቱ ከተገኙ ምእመናንም ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ቃል የተገባ ሲሆን በማኅበረ ቅዱሳን የአሜሪካ ማእከል ለሕንፃጻው ማሠሪያ የሚውል ገንዘብ ለመላክ ቃል ገብቷል፡፡ማኅበረ ቅዱሳን ለአክሱም ጽዮን ማርያም ገዳም የብር መቋሚያና ጸናጽል በስጦታ ያበረከተ ሲሆን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጥቁር አንበሳimg 0363 ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በ2004 ዓ.ም. የተመረቀውና የወርቅ ሜዳልያ ተሸላሚው ዶክተር አምኃ መሸሻ ለቅዱስ ያሬድ ገዳም ሜዳልያውን አበርክቷል፡፡

በመጨረሻም ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የደቡባዊ ትግራይ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በሰጡት ቃለምእዳን “ከየገዳማቱና አድባራቱ በዓሉን ለማክበር በመካከላችን የተገኙት ሊቃውንት አባቶቻችን የቅዱስ ያሬድን ፈለግ በመከተል ቤተ ክርስቲያን ያለተተኪ እንዳትቀር አገልጋዮችን በማምረት ላይ ይገኛሉ፡፡ እነዚህ አባቶቻችን የቤተ ክርስቲያናችን የዜማ ፋብሪካዎች ናቸው” ብለዋል፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ የማኅበረ ቅዱሳን መዝሙር ክፍል አባላት የታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም ገዳም ሰንበት ትምህርት ቤት አባላት እንዲሁም በአዲስ አበባ የሚገኙ ቀዳሚ ዜማ ዘያሬድ የሊቃውንት ማኅበር ያሬዳዊ ዝማሜና ወረብ አቅርበዋል፡፡

st yared 1500 symposium

የቅዱስ ያሬድ ሥራዎችን በዩኔስኮ ማስመዝገብ እንደሚገባ ተገለጸ

የቅዱስ ያሬድ 1500ኛ ዓመት መታሰቢያ በዓልን አስመልክቶ ማኀበረ ቅዱሳን በግዮን ሆቴል ባዘጋጀውና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በተገኙበት አውደ ጥናት ላይ የቅዱስ ያሬድ ሕይወትና ሥራዎቹ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስና የባሕል ድርጅት /UNESCO/ ለማስመዝገብ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተገለጸ፡፡st yared 1500 symposium

ቅዳሜ ግንቦት 10 ሙሉ ቀን በተደረገው በዚህ ዐውደ ጥናት ላይ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የደቡባዊ ትግራይ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ ከየአድባባራቱና ገዳማት ጥሪ የተደረገላቸው ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፤ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ምሁራን፤ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን በብፁዕነታቸው ጸሎትና ቃለምዕዳን ዐውደ ጥናቱ ተከፍቷል፡፡

ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ በሠጡት ቃለ ምዕዳን ማኅበሩ የቅዱስ ያሬድን 1500ኛ መታሰቢያ በዓልን ማዘጋጀት በመቻሉ አመስግነው በአሁኑ ወቅት በቅዱስ ያሬድ የዜማ ትምህርት ከፍተኛ እውቀት ያላቸው አባቶች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተመናመነ መምጣቱንና በሀገረ ስብከታቸው ከሚገኙ 1000 ገዳማትና አድባራት ውስጥ በጣም ጥቂት የድጓ መምህራን ብቻ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡ ይህም አሳሳቢነቱን ከፍ ስለሚያደርገው ከፍተኛ ጥረት መደረግ እንደሚገባው አሳስበዋል፡፡

በባሕልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የሚኒስትሩ ተወካይ የሆኑት አቶ ወርቅነህ አክሊሉ ባቀረቡት ንግግር “ቅዱስ ያሬድ ወደር ያልተገኘለትና ዓለምን ያስደመመ የዜማ ጥበብ ባለቤት እንደመሆኑ የሥራ ውጤቶቹ ዘመን ተሻጋሪ ሆነው እሰካለንበት ዘመን ከነውበታቸውና ከነክብራቸው ሊደርሱ ችለዋል፡፡ ተሸናፊነትን ያሸነፈ የትእግስት ተምሳሌት በመሆን አንድን ስጋዊም ሆነ መንፈሳዊ ተግባር ከዳር ለማድረስ ያለመታከት መሥራትን በማሳየት ለተስፋ ቆራጭ ትውልድ የሕሊና ትንሳኤ አብነት ተደርጎ ሊቆጠር የሚችልና የሚገባውም ታላቅ ሊቅ ነው” በማለት ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም የቅዱስ ያሬድ ሥራዎች ድንበር ተሸጋሪነት ሲገልጹ “ቅዱስ ያሬድን ባሰብን ጊዜ የዘመን ውሽንፍር ያልገደባቸው ድርሰቶቹን እንደናስብ ስለሚያደርገን ዛሬም ድረስ በዚህ ሊቅ የሥራ ውጤቶች እንደ ኢትዮጵያዊነታችን እንኮራበታለን፡፡ የሌሎች ሀገሮች ህዝቦችም እንዲያውቁትና ይህ ጥበብ ድንበር ተሻጋሪ እንዲሆን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር እንሰራለን” ብለዋል፡፡

በአውደ ጥናቱ ላይ አምስት ያህል ጥናታዊ ጽሑፎች የቀረቡ ሲሆን ከእነዚህም መካከል ሊቀ ኅሩያን በላይ መኮንን የቅዱስ ያሬድ ልደቱ፤ እድገቱ፤ የማኅሌታዊና የምናኔ ሕይወቱ በሚል ርዕስ ጥናታቸውን አቅርበዋል፡፡

ዲያቆን ሰሎሞን ወንድሙ በበኩላቸው የቅዱስ ያሬድ ዜና ሕይወቱ በተለያዩ ጸሐፍት ሥራዎች ሲዳሰስ በሚል ርዕስ ባቀረቡት ጥናትም በተለያዩ ጸሐፊያን የልደት ቀኑ፤ የእናትና አባቱ ስም፤ በስጋ ማረፉን ወይም መሰወሩን፤ የመምህራኖቹ ስም፤ . . . ወዘተ የመሳሰሉት ጉዳዮች ወጥነት ኖሯቸው መስተካከል እንደሚገባቸው መረጃ በማጣቀስ አቅርበዋል፡፡

ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ ኦርቶዶክሳዊ ስብከት ከቅዱስ ያሬድ ድርሳናት አንጻር በተሰኘው ጥናታቸውም አንድ ኦርቶዶክሳዊ ስብከት ሊያሟላቸው ከሚገባቸው መሠረታዊ ነጥቦች አንጻር የቅዱስ ያሬድን ድርሰቶች በመመዘን አቅርበዋል፡፡

ሊቀ ጠበብት ተክሌ ሲራክ ባቀረቡት ጥናትም አራቱ የዜማ ዐበይት መንገዶች በሚል አጠር ያለ ዳሰሳ አቅርበዋል፡፡ የቤተልሔም፤ የቆሜ፤ የአጫበርና የተጉለት ዜማዎችን በትውልድ ቅብብሎሽ በመከፋፈል ለማሳየት ጥረት አድርገዋል፡፡ በተለይ የተጉለት ዜማ በመጥፋት ላይ እንደሚኝና በአሁኑ ወቅት አንድ አባት ብቻ እንደቀሩና ለትውልድ ለማሸጋገር ብዙ መሰራት እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡

የመጨረሻው ጥናት በሙዚቃው ዘርፍ ባለሙያ የሆነውና በቅዱስ ያሬድ ሥራዎች ላይ ከፍተኛ ምርምር እያደረገ የሚገኘው ሠርፀ ፍሬ ስብሐት የቅዱስ ያሬድ ዜማ በባሕላዊውና በዘመናዊው ሙዚቃ ያለው ተጽእኖ በማስመልከት አጠር ያለ ጥናታዊ ዳሰሳ አድርገዋል፡፡

በቀረቡት አምስት ያህል ጥናቶች መነሻነት የጉባኤው ተሳታፊ በሆኑት ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን አስተያየቶችና ጥያቄዎች ተስተናግደዋል፡፡st yared 1500  2
የውይይቱ መቋጫ የሆነውም የቅዱስ ያሬድ ታሪክና ሥራዎች በተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና የባሕል ድርጅት /UNESCO/ ለማስመዝገብና ለዓለም ለማስተዋወቅ ጥናቶች እንዲጠኑ በማድረግና በማስተባበር አንድ እልባት ላይ መድረስ እንዲቻል ከጠቅላይ ቤተ ክህነት፤ ከሊቃውንት ጉባኤ፤ ከሊቃውንት አባቶች፤ ከባሕልና ቱሪዝም ሚኒስቴር፤ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲና ከሙዚቃ ባለሙያዎች እንዲሁም ከማኅበረ ቅዱሳን የተውጣጣ 17 አባላትን ያቀፈ ኮሚቴ እንዲዋቀር በማድረግ ዐውደ ጥናቱ ተጠናቋል፡፡

የቅዱስ ያሬድን 1500ኛ የልደት በዓል አስመልክቶ የተዘጋጀ ዐውደ ጥናት ተከፈተ

 ዲ/ን መርሻ አለኸኝ(ዶ/ር)

የቅዱስ ያሬድን 1500ኛ የልደት በዓልን ምክንያት በማድረግ በማኅበረ ቅዱሳን የቅዱሳት መካናት ልማትና ማኅበራዊ አገልግሎት ዋና ክፍል የተዘጋጀ ዐውደ ጥናት በግዮን ሆቴል ሳባ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተከፈተ፡፡ በዐውደ ጥናቱ ላይ  ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ በጠቅላይ ቤተ ክህነት የልዩ ልዩ መምሪያዎች ሓላፊዎች፣ በዋና ዋና አብነት ት/ቤቶች የሚያስተምሩ መምህራንና የመንግሥትና ልዩ ልዩ ተቋማት ተወካዮችና ጥሪ የተደረገላቸው ሊቃውንት ተገኝተዋል፡፡

ቀሲስ ዶክተር ሰሙ ምትኩ የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ባደረጉት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ማኅበሩ ቅዱሳት መካናት ራሳቸውን ችለው የሚተዳደሩባቸውን ዘላቂ የልማት ፕሮጀክቶችን በመቅረጽና በመተግበር ለአብነት መምህራንና ተማሪዎች ድጋፍ በማድረግ ከፍተኛ ሥራ አየሠራ እንደኾነ ከገለጹ በኋላ፤ ሊቁ ለሀገራችን ከሰጠው አበርክቶ አንጻር ማኅበሩ ከፍተኛ ቦታ የሚሰጠውን የቅዱስ ያሬድን የ1500ኛ ዓመት የልደት በዓል በሰፊ ዝግጅት ለማክበር እንደወሰነ ገልጸዋል፡፡

አቶ ተስፋዬ ውብሸት የጠቅላይ ቤተ ክህነት ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ዐውደ ጥናቱን በንግግር ከፍተዋል፡፡ ምክትል ሥራ አስኪያጁ ቅዱስ ያሬድ ለሀገራችን ካበረከተው አስተዋጽዖ አንጻር የልደት በዓሉ በዚህ መልኩ መከበሩ በእጅጉ ተገቢ እንደኾነ በመጥቀስ፤ ያዘጋጀውን ማኅበረ ቅዱሳንን ካመሰገኑ በኋላ ማኅበሩ በተለይ ቅዱሳት መካናትንና አድባራትን በመርዳት በኩል እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንዲያግዝ ጥሪ አድርገዋል፡፡

በመቀጠልም አቶ ወርቅነህ አክሊሉ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ተወካይ የቅዱስ ያሬድ የዜማ ሀብት ከቤተ ክርስቲያኗ አልፎ የሀገር ሀብት በመኾኑ ሁሉም እንክብካቤ እና ጥበቃ እንዲያደርግለት፣ በሕይወት ያሉትን የዜማውን ሊቃውንት ከመንከባከብ ባሻገር መዳከም የሚታይበትን የዜማውን ሽግግር ለማንቃት ተረካቢዎችን ማፍራት እንደሚገባ በመግለጽ የጉባኤውን ታዳሚ ቀልብ የገዛ ንግግር አድርገዋል፡፡

ከዐውደ ጥናቱ መርሐ ግብር ለመረዳት እንደሚቻለው በቅዱስ ያሬድ ሕይወትና ዜማዎቹ ዙሪያ በዘርፉ ሊቃውንትና ተመራማሪዎች አምስት ያህል ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል፡፡

በተያያዘ ዜና ነገ እሑድ ግንቦት 10 ቀን 2005 ዓ፡ም ከቀኑ 7፡30 ጀምሮ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩን ጨምሮ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ሊቃውንትና ምእመናን በተገኙበት በሰፊው እንደሚዘከር ታውቋል፡፡

memher girma

ጠቅላይ ቤተ ክህነት ደብሩ በ‹‹አጥማቂው›› ላይ የጣለውን እገዳ አጸና

በምሥራቅ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ በቤተ ክርስቲያን ቅጽር ግቢ ‹‹ሲያጠምቅ›› በነበረው ግለሰብ ላይ ያሳለፈውን የእግድ ውሳኔ ጠቅላይ ቤተ ክህነት አጸናው፡፡ ከደብሩ ሰበካ ጉባኤ ያገኘውን የእግድ ደብዳቤ መሠረት በማድረግ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በቁጥር 9474/756/2005 በቀን 08/09/05 ያወጣው ደብዳቤ ‹‹መ/ር ግርማ ወንድሙ ሰባኬ ወንጌልና አጥማቂ ነኝ፤ የማዳን ፈውስ አለኝ በማለት በሕገ ወጥ መንገድ እስከ አሁን ድረስ በደብሩ እያጠመቀ›› እንደሚገኝ ይገልጻል፡፡

memher girma
በማከልም ቅዱስ ሲኖዶስ በሕገ ወጥ መንገድ የማዳን ፈውስ አለኝ በማለት በየደብሩ ቅጥር ግቢ በማሰባሰብ የሚያጠምቁትን በተመለከተ ያሳለፈውን የእግድ ውሳኔ በመጥቀስ፤ ‹‹መምህር ግርማ ወንድሙ በደብረ ሰላም ቅዱስ እሰጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚፈጽሙት የማጥመቅ ሥርዓትና የወንጌል አገልግሎት ሕገ ወጥ መኾኑን›› በአጽንዖት በመግለጽ የደብሩ ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት በግለሰቡ ላይ ያሳለፈውን ውሳኔ እንዳጸናው ይገልጻል፡፡ በተጨማሪም ከእግዱ ጋር በተያያዘ ሕዝበ ክርስቲያኑ የፀጥታ ችግር እንዳይገጥመው የደብሩ ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት ጥብቅ ክትትል በማድረግ ውሳኔውን ተግባራዊ እንዲያደርግ አሳስቧል፡፡ ጠቅላይ ጽ/ቤቱ ለውሳኔው ተግባራዊነት አስፈላጊ ትብብር እንዲያደርጉ ለሚመለከታቸው የመንግሥት የፀጥታ አካላት ጥሪ አድርጓል፡፡ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ እና የደብሩ ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት እግዱን ያስተላለፈበት ደብዳቤዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡

 betekihent girma

የአዲስ ዘመን ቆይታችን

ግንቦት 9 ቀን 2005 ዓ.ም.

በእንዳለ ደምስስ

ጸበል ጸዲቅ /ክፍል ስድስት/
የማኅበሩ ጋዜጠኞች ቡድን ወደ ሰሜን ጎንደር፤ ደቡብ ጎንደር፤ ምእራብ ጎጃምና አዊ ዞን የሚገኙ ቅዱሳት መካናትንና የሀገረ ስብከቶቹን የሥራ እንቅስቃሴ ለመዘገብ ከሚያዚያ 3 -20 ቀን 2005 ዓ.ም. ያደረገውን ጉዞ አጠናቅቆ ተመልሷል፡፡ በዚህም መሠረት በጉዟችን ያሰባሰብናቸውን መረጃዎች አቀናጅተን በድረ ገጻችን ማቅረባችንን እንቀጥላለን፡፡

በጉዟችን ወቅት እየዳሰስናቸው የነበሩትን መረጃዎች “ጸበል ጸዲቅ” በሚል ርዕስ ክፍል አምስት ድረስ ማቃመሳችን ይታወቃል፡፡ ከክፍል ስድስት ጀምሮ ያሉትን ደግሞ እነሆ፡-

የጋዜጠኞቹ ቡድን ከዚህ በፊት ብዙም ትኩረት ያልተሰጣቸውና በዝዋይ ሐይቅ  የሚገኙትን የቅዱሳን አበው የሃይማኖት ፍሬ የሆኑት ገዳማትን ቃኝተን ፤ የሰሜን ጎንደር ቆይታችንን በማጠናቀቅ ወደ ደቡብ ጎንደር በማቅናት ሥራችንን ከአዲስ ዘመን ለመጀመር ወስነናል፡፡

አዲስ ዘመን ከተማ የደረስነው በምሽት ስለነበር የወረዳ ማእከሉ ወንድሞችና እህቶች ተቀብለውን፤ ማረፊያ አዘጋጅተው፤ እግራችንን አጥበው፤ ምግብ እያቀረቡልን በጥሩ መስተንግዶ ተንከባክበውናል፡፡

ጉዟችንን ከጀመርንበት ቀን ጀምሮ በየቀኑ ምሽት ከማረፋችን በፊት ውሏችንን በተመለከተ እያንዳንዱ ጋዜጠኛ ለቡድኑ የቃል ሪፖርት ያቀርባል፡፡ ከሪፖርቱም በመነሳት ውይይት በማድረግ ስህተቶች ካሉም ወደፊት በሚሰራው ሥራ ላይ እንዲስተካከል በመመካከር በቀጣዩ ቀን የሚዘገቡ ሥራዎችን እንከፋፈላለን፡፡

በዚህም መሠረት አዲስ ዘመን ውስጥ ለመሰራት ከታቀዱት ቤተ ክርስቲያናትና ገዳማት መካከል ዜና ማርያም፤ ዋሻ አቡነ እንድርያስ፤ ወይን ዋሻ አቡነ ተክለ ሃይማኖት፤ ጣራ ገዳም፤ ሊቦ ቅዱስ ጊዮርጊስንና ሐና ማርያምን ለማዳረስ ቡድኑ ጥረት አድርጓል፡፡

ዜና ማርያም ለመዘገብ ዲያቆን ቴዎድሮስ ኃይሉና መንገዱን ከሚመራው የአዲስ ዘመን ወረዳ ማእከል ወንድም ጋር ለአራት ሰዓታት የእግር መንገድ ቢጓዙም ሳይሳካላቸው ተመልሰዋል፡፡ የጉዟቸውን ሂደትና ያጋጠማቸውን ውጣ ውረድ እንዲህ ነበር የገለጸው፡-

ዜና ማርያም የትውልድ አገሯ ጎጃም ሲሆን በአገራችን ጽላቷ በደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት በአዲስ ዘመን ከተማ አቅራቢያ ብቻ ይገኛል፡፡ ወደ ቤተ ክርስቲያኗ ለመድረስ የፈለገ ሰው ከአዲስ ዘመን ከተማ ከሦስት ሰዓት እስከ አራት ሰዓት የእግር ጉዞ ማድረግ ግድ ይለዋል፡፡

ገዳሟ ተራራ ጫፍ ላይ የተመሠረተች በመሆኗ ገና ከአዲስ ዘመን ከተማ እግራችን መውጣት ሳይጀምር ነው በርቀት የተመለከትናት፡፡ በመንገድ ላይም ጥንታውያን የሆኑ ሁለት አብተ ክርስቲያናትን የደሪጣ መድኀኔዓለምን ደብር እና ደሪጣ ማርያምን ተሳለምን፡፡

እነዚህን አብያተ ክርስቲያናትን ተሳልመን ሜዳማ መንገዱን ጨርሰን ቀጥ ብሎ ከሩቅ ቆሞ ይጠብቀን ወደ ነበረው ተራራ አመራን፡፡ ተራራውን በእጅና በእግር ከመቧጠጥ ባልተናነሰ ሁኔታና ዐሥር ጊዜ እያረፍን ወጣነው፡፡

ወደ ገዳሟ ስንቀርብ መንገድ የሚመራው ዲ/ን ኀይለሚካኤል ጥቅጥቅ ያለውን ጫካ እያመለከተ “እዚህ ተራራ ሥር የዜና ማርያም ጸበል አለ” አለን፡፡ አያይዞም “ጸበሉ በፈዋሽነቱ ስለሚታወቅ በቅርብ ርቀት የሚያውቁት ሁሉ እየመጡ ከተለያዩ ደዌያት እየተፈወሱ ይገኛሉ” በማለት ምስክርነቱን ሰጠን፡፡

እኛም የጸበሉን ቦታ አልፈን ተራራ ለተራራ እየተጓዝን ከገዳሟ መግቢያ በር ደረስንና “በሰላም ከደጅሽ ያደረስሽን” በማለት ጸሎት አደረግን፤ በዙሪያችን ባሉ ድንጋዮች ላይ ቁጭ ስንል ገዳሟ ተራራ ጫፍ ላይ ያለች እንደመሆኗ መጠን ዙሪያ ገባውን ቁልጭ አድርጋ አሳየችን፡፡

ከገዳሙ አባቶች አንድ አባት አገኘንና የሚበላውንና የሚጠጣውን ቀምሰን፤ ከሀገረ ስብከት የተጻፈልንን ደብዳቤም አሳየናቸው፤ የመጣንበትን ዓላማም አወጋናቸው፡፡ እኒህ አባት ደብዳቤውን ደጋግመው አነበቡት፡፡ አብራቸው የነበረች አንዲት እኅትም በርቀት አሻግራ ደብዳቤውን ከጥግ እስከ ጥግ አነበበችውና “እኔ የሚገርመኝ” በማለት ንግግሯን ጀመረች “እኔ የሚገርመኝ ለምንድነው ይህችን ገዳም ሁሉ የሚፈልጋት? ገድሏን እንመልከተው? የሚሉት” በማለት ተናደደች፡፡ እኛም ቅርሶችን ለመጠበቅ መንፈሳዊ ቅንዓት ሊሆን ይችላል በማለት የመገናኛ ብዙኀንን ጥቅም ለማስረዳት ሞክረን ደብዳቤውን ወደ ያዙት አባት ፊታችንን ዘወር አደረግን፡፡ እኒህም አባት “ልጆቼ እዚህ ድረስ በመምጣት ይህችን ታላቅ ገዳም ለማስተዋወቅ መሞከራችሁ የሚያስመሰግናችሁ ነው፤ ነገር ግን ዜና ማርያም እንዲህ ዓይነት ነገር አትወድም፡፡ ከዚህ በፊትም የገዳሟን ታሪክ ለመዘገብ የመጡ ሰዎች ነበሩ፡፡ ግማሾቹ ዐይናቸው ታውሮ ወደ ገዳሙ መግባት ሲያቅታቸው፤ ሌሎቹ ደግሞ ያለእርሷ ፈቃድ ታሪኳን ዘግበው ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ በመንገድ ላይ በመኪና አደጋ ዐረፉ” አሉን፡፡ አያይዘውም “ባህታውያን በየዓመቱ ወደዚህች ቦታ እየመጡ ታሪኳን ለማንም አትንገሩ ብለው አውግዘውናል” በማለት ለሰሚ ግራ የሆነ ንግግር አሰሙን፡፡ እሳቸው እኔ ብቻ የከለከልኳችሁ አይምሰል በሚመስል ሁኔታ “ኑ ወደ አስተዳዳሪው ቤት ልውሰዳችሁና እርሳቸውም የሚሉትን ስሙ” አሉን፡፡

የአስተዳዳሪው ቤት ለመድረስ ተጨማሪ ከዐሥራ አምስት ደቂቃ ያላነሰ መንገድ መሄድ ግድ ሆነብን፡፡ አስተዳዳሪው ይገኙበታል ወደተባለው ቤት ተጉዘን ሳንደርስ በመንገድ “እናንተ እዚህ ጋር ዐረፍ በሉና አስተዳዳሪው ካሉ ጠይቄ ልምጣ” ብለው ይዘውን የመጡት አባት በመንገድ ትተውን ሄዱ፡፡

ብዙ ታሪክ እንዘግባለን፤ ለምዕመናንም እናስተዋውቃለን ብለን ተስፋ ጥለን የመጣንበትን ነገር አንድም ሥራ ሳንሠራ እየመሸ በመሆኑ ተጨነቅን፡፡ እኚህን አባት በዐይናችን ስንከተላቸው በአካባቢው ከሚገኙ የሣር ጎጆዎች ወደ አንዲ ዘለቁ፤ ብዙም ሳይቆዩ ፈጥነው ተመለሱና “ዛሬ ዕድለኞች አይደላችሁም አስተዳዳሪው ስብሰባ ሄደዋል” አሉን፡፡ እኛም “ታዲያ ምን ይሻላል? እርሳቸው የሚፈቅዱልን ከሆነ እዚሁ እናንተ ዘንድ አድረን ጠዋት እናነጋግራቸው” አልናቸው፡፡ እርሳቸው ግን “እዚህ ብታድሩም አሁን ከነገርኳችሁ ውጪ የምትሰሙት ነገር የለም፤ ፈቃድ ለማግኘት የሚቻለው ከአስተዳዳሪው ወይም ከሰበካው ሳይሆን ሕዝቡ ሲፈቅድ ነው፡፡ የሕዝቡን ፈቃድ ለማግኘት ደግሞ ጊዜ ያስፈልጋል፤ ሳይመሽባችሁ ሂዱ” ብለው መንገድ አመላክተው ሸኙን፡፡

እኛም ዝናብና ጨለማ ሳያገኘን አዲስ ዘመን ለመግባት የደከመ ጉልበታችንን ማንቀሳቀስ ጀመርን፡፡ ነገር ግን እግራችን በፈለግነው ፍጥነት መጓዝ ባለመቻሉ ሊወርድ ካለው በረዶና ከሚያስፈራው ጨለማ ማምለጥ ሳንችል ቀረን፡፡ 

እነ ዲያቆን ቴዎድሮስ ኀይሉ የዜና ማርያምን ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ለመዘገብ ሄደው ያጋጠማቸውን ነበር ያወጉን፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንንና የቅዲሳን አባቶቻችን እንዲሁም እናቶቻችን ታሪክና ገድል እንዳይታወቅ በስመ ውግዘት አፍኖ ማስቀረቱ ማንን ነው የሚጠቅመው? ማውገዝ የሚችለውስ ማነው? የውግዘት ምክንያቶች ምን ምን ናቸው? ምላሽ የሚፈልጉ ጥያቄዎች ናቸው፡፡

ወደ ሊቦ ቅዱስ ጊዮርጊስ የተጓዘው ዲያቆን ታደለ ሲሳይና መንገዱን ከሚመራው ወንድም ጋር ከአምስት ሰዓታት በላይ የእግር ጉዞ ወስዶባቸው ነው ቦታው የደረሱት፡፡ በእለቱ መመለስ ባለመቻላቸው አዳራቸውን እዚያው አድርገው በማግስቱ ሲመለሱ መንገድ ተሳስተው ተንከራትተው ነው አዲስ ዘመን የገቡት፡፡ ማካካሻ ይሆናቸው ዘንድ ግን የሚፈለገውን መረጃ ይዘው መምጣታቸው አስደሳች ነበር፡፡

ይቆየን

1024×768

ቅድስት ቤተ ክርስቲያንንና የቅዱሳን አባቶቻችን እንዲሁም እናቶቻችን ታሪክና ገድል እንዳይታወቅ በስመ ውግዘት አፍኖ ማስቀረቱ ማንን ነው የሚጠቅመው? ማውገዝ የሚችለውስ ማነው? የውግዘት ምክንያቶች ምን ምን ናቸው? ምላሽ የሚፈልጉ ጥያቄዎች ናቸው፡፡

ወደ ዲቦ ቅዱስ ጊዮርጊስ የተጓዘው ዲያቆን ታደለ ሲሳይና መንገዱን ከሚመራው ወንድም ጋር ከአምስት ሰዓታት በላይ የእግር ጉዞ ወስዶባቸው ነው ቦታው የደረሱት፡፡ በእለቱ መመለስ ባለመቻላቸው አዳራቸውን እዚያው አድርገው በማግስቱ ሲመለሱ መንገድ ተሳስተው ተንከራትተው ነው አዲስ ዘመን የገቡት፡፡ ማካካሻ ይሆናቸው ዘንድ ግን የሚፈለገውን መረጃ ይዘው መምጣታቸው አስደሳች ነበር፡፡

እኔና የቴሌቪዥን ክፍል አዘጋጁ ቶማስ በየነ ከቪዲዮ ካሜራ ባለሙያው ሙሉጌታ ቢሆነኝ ጋር በሊቀ መንኮራኩራችን /ሾፌራችን/ ነብያት መንግስቴ አብራሪነት ወደ አቡነ እንድርያስ ዋሻና ወይን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ዋሻ ገሰገስን፡፡ መኪና መንገዱን ትተን ጥቂት ወደ ቀኝ እንደታጠፍን ትልልቅ ድንጋዮች አጋጠሙን፡፡

ነብያት መኪናውን አቁሞ “እንዴት በዚህ መንገድ ሂድ ትሉኛላችሁ፤ ለመኪናው አስቡ እንጂ!” በማለት ወርዶ በኩርፊያ ድንጋይ ላይ ቁጭ አለ፡፡

ያለን አማራጭ ለቪዲዮ ቀረጻ የሚያገለግሉንን መሳሪያዎች ከመኪናው ላይ አውርደን በመከፋፈል   ተሸክመን ጉዟችንን ቀጠልን፡፡ ከአርባ ደቂቃ የእግር ጉዞ በኋላ አቡነ እንድርያስ ዋሻ ደረስን፡፡

አቡነ እንድርያስ ገዳም/አቡነ እንድርያስ ዋሻ/፤-

የአቡነ እንድርያስ ገዳም ከአዲስ ዘመን ከተማ በስተሰሜን አቅጣጫ ከተራራ ሥር የሚገኝ የዋሻ ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ በአካባቢው በተለምዶ እንድርያስ ዋሻ በመባል ይታወቃል፡፡

ገዳሙ አራት በሮች ሲኖሩት እያንዳንዳቸው ከአንድ  ወጥ እንጨት ተጠርበው የተሰሩ ናቸው፡፡ እያንዳንዱ ደረጃና የበሩ መቃን በጣና ደሴት ውስጥ ከሚገኙት ከደብረ ሲና ማርያም፤ ከደብረ ገሊላ ኢየሱስ አቡነ ዘካርያስ ገዳም፤ ማን እንደ አባ ያሳይ መድኀኔዓለም ገዳም፤ . . . ጋር ተመሳሳይነት አላቸው፡፡ ገዳሙ ምንም ዓይነት እድሳት ያልተደረገለት ሲሆን ጥንታዊነቱን ጠብቆ የሚገኝ የዋሻ ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡  

ቀሲስ ቢራራ በላቸው ይባላሉ፡፡ የገዳሙ አገልጋይና ቁልፍ ያዥ ናቸው፡፡ ስለ ገዳሙ ካጫወቱንና በገዳሙ ውስጥ ከሚገኘው ከአቡነ እንድርያስ ገድል ካገኘነው በጥቂቱ ላቅርብላችሁ፡፡

ቦታው ከክርስቶስ ልደት በፊት በ899 ዓ.ዓ. በአፄ ባዚን ዘመነ መንግስት የተመሠረተና የአካባቢው ሰዎች በእንጨት ምስል ቀርጸው ጣኦት እያመለኩ ቆይተውበታል፡፡ ለ440 ዓመታትም የኦሪት መስዋዕት ሲሰዋበት የነበረ ሲሆን፤ የአካባቢው ነዋሪዎች ዋሻው ውስጥ የሚኖሩ ሁለት ባልና ሚስት  ዘንዶዎችን እርጎ እየመገቡ ያመልኳቸው እንደነበር በገዳሙ ውስጥ የሚገኘው ገድለ አቡነ እንድርያስ ይገልጻል፡፡

በሩን ከፍተው ወደ ውስጥ ሲዘልቁ ሰፊውን ቅኔ ማኅሌት ያገኛሉ፤ ከፊት ለፊት ቅድስትና መቅደሱ፤ እንዲሁም በትልቁ የተሳሉ የአቡነ እንድርያስ ስእሎች ጎልተው ይታያሉ፡፡ በቤተ መቅደሱ ግራና ቀኝ ሰልፋና ደፈር በተባሉ ሰዎች በጥርብ ድንጋይ የተከለሉ ቦታዎች አሉ፡፡ /ሰልፋና ደፈር የዘንዶዎቹ ቀላቢዎች/ እንደነበሩ ገድለ አቡነ እንድርያስን በመጥቀስ አባቶች ይናገራሉ፡፡

ገዳሙ ከክርስቶስ ልደት በኋላም የአካባቢው ሕዝብ ዘንዶዎቹን በማምለክ የቆየ ሲሆን አቡነ እንድርያስ በ13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በአቡነ ተክለ ሃይማኖት በደቀመዛሙርትነት ተመርጠው ምድረ እንፍራንዝ /የአሁኑ ሊቦ ከምከም ወረዳ አካባቢ/ ሄደው ክርስትና እንዲያስተምሩ፤ ህዝቡንም እንዲያጠምቁ ተልከዋል፡፡

አቡነ እንድርያስ ተልእኳቸውን ለመፈጸም ወደ አካባቢው ሲመጡ ረድአቸውን አቡነ ቶማስን አስከትለው ስለነበር አካባቢውን እንዲቃኙና ለጸሎት የሚመች ቦታ እንዲፈልጉ ላኳቸው፡፡ ይህ ዋሻ በአቡነ እንድርያስ ረድእ በነበሩት በአቡነ ቶማስ አማካይነት የተገኘ ሲሆን ዘንዶዎቹን ሲመለከቱ በመፍራታቸው ቦታው እንደማይሆናቸውና የዘንዶዎቹን አስፈሪነት ለአቡነ እንድርያስ ይገልጹላቸዋል፡፡ አቡነ እንድርያስም “በእግዚአብሔር ኃይል እናሸንፋቸዋለን” በማለት መጥተው በመስቀላቸው በማማተብ በእግዚአብሔር ስም ይገስጻቸዋል፡፡ በዚህ ቅጽበት አቡነ እንድርያስ የያዙት መስቀል ከመሬት ወድቆ የቀኝ በኩል ክንፉ በመሰበሩ ወደ እግዚአብሔር ቢጸልዩ የእግዚአብሔር መልአክ መጥቶ እንደነበረ አድርጎ ሰጥቷቸዋል፡፡ ከዘንዶዎቹ አንዱ ከአካባቢው ማዶ ተምዘግዝጎ ግራርጌ ጉበያ ማርያም ከሚባል ቦታ ላይ ወድቋል፡፡ አንደኛው ግን እስከ ዛሬ ድረስ የደረሰበት ባይታወቅም ወደ ዋሻው ውስጠኛ ክፍል ገብቶ እንደቀረ ይነገራል፡፡

አቡነ እንድርያስ ገዳሙን አቅንተው የአካባቢው ምእመናንን ክርስትና በማስተማር ታላቅ ተድጋሎ የፈጸሙበት ቅዱስ ስፍራ ነው፡፡ ወደ ገዳሙ በተአምራት አብረዋቸው የመጡ አራት በግምት አንድ ሜትር ቁመት ያላቸውና ከ20 እስከ አሥራ አምስት ሣንቲ ሜትር ስፋት ያላቸው ድንጋዮች መካከል ሁለቱ በደወልነት አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ ሲደወሉ ወፍራምና ቀጭን ድምጽ ስለሚያወጡ የወንድና የሴት ደወሎች ይባላሉ፡፡ በአገልግሎት ወቅት ዋሻው ድምጽ እያስተጋባ ስለሚያስቸግር አቡነ እንድርያስ ገስጸውት እስከ ዛሬ ድረስ ዋሻው ምንም አይነት ድምጽ አያስተጋባም፡፡

በገዳሙ ውስጥ ዜና ማርያም የተባለችው ቅድስት እናት ለ25 ዓመታት በጸሎት ተወስና ቆይታበታለች፡፡ ከእንጨት ተፈልፍሎ በቁመቷ ልክ በተሰራ ገንዳ ውስጥ ገብታ የገንዳውን ግራና ቀኝ በደረቷ አቅጣጫ በመብሳት በጠፍር በማሰር ትጸልይ ነበር፡፡/ ዜና ማርያም ትጸልይበት የነበረው የእንጨት ገንዳ ዛሬም በገዳሙ ውስጥ ይገኛል፡፡/

በገዳሙ ውሰጥ በጥንቃቄ ጉድለት እየተበላሹ የሚገኙት ቅርሶች እንደ አልባሌ እቃዎች ተጥለዋል ማለት ይቻላል፡፡ ዘንዶው እርጎ ይጠጣበት የነበረው ገንዳ፤ የዜና ማርያም መጸለያ ገንዳ፤ በእንጨት የተሰራ የኦሪት መሰዊያ፤ የመስዋእተ በግዕ ስጋ ማስቀመጫ፤ የደሙ ማኖሪያ፡ አፄ ዘርዓያዕቆብ ለገዳሙ ከሰጧቸው 6 ነጋሪቶች መካከል ሁለቱ፤  ብዛት ያላቸው የሰው አጽሞች ይገኛሉ፡፡ ከአጽሞቹ መካከል አንዱ ሙሉ ለሙሉ ሳይፈርስ ከራስ ቅሉ እስከ እግር ጥፍሩ በዘመናዊ ሳጥን ተደርጎ ከላይ በመስታወት ታሽጎ ይታያል፡፡ የአጽሞቹን እድሜ መገመ,ት እንደማይቻልና ቀድሞም እንደነበሩ ቀሲስ ቢራራ በላቸው ይገልጻሉ፡፡

የአቡነ እንደርያስ የእጅ መስቀል በገዳሙ ውስጥ በቅርስነት ተጠብቆ ይኖር እንደነበር፤ ብዛት ያላቸው ምእመናን በመስቀሉ ታሽተው ከያዛቸው ደዌ ይድኑ እንደነበር ቀሲስ ቢራራ በላቸው የአይን ምስክር እንደሆኑ ይናገራሉ፡፡ ነገር ግን በቅርቡ በአንድ ግለሰብ የአቡነ እንድርያስ መስቀል መዘረፉንና የግለሰቡ ማንነት ታውቆ ክስ ተመስርቶበት በቀጠሮ ላይ እንደሚገኝ የአቡነ እንድርያስን ዋሻ ቆይታችንን አጠናቀን ስንወጣ የገዳሙ አበምኔት የክሱን ሁኔታ ለመከታተል ከሔዱበት ሲመለሱ አግኝተናቸው ነግረውናል፡፡

ገዳሙ ለስርቆት የተጋለጠ በመሆኑ የገዳሙ ጥንታዊ መጻሕፍት ተሰብስበው በአንድ ታማኝ በሆነ ግለሰብ ቤት ውስጥ እንዲቀመጥ መደረጉንም ቅርሶቹን ለማየት በጠየቅንበት ወቅት ከተሰጠን ምላሽ ለማወቅ ችለናል፡፡ የብራና መጻሕፍት ገድለ ሰማእታት፤ ስንክሳር የአመት /2/፤ ጸሎተ እጣን፤ ግንዘትና . . . ሌሎችም ንዋያተ ቅዱሳት በዚሁ ታማኝ ነው በተባለው ሰው እጅ ላይ ይገኛሉ፡፡ በየአመቱም ቆጠራ እንደሚካሔድ በስፍራው ከነበሩት አባቶች ተገልጾልናል፡፡

የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሀብቶችና ቅርሶች እሰከ መቼ በሰዎች እጅ ይቆያሉ? በተለያዩ ምክንያቶች ቢሰወሩ ተጠያቂው ማነው? መፍትሔ ይሻልና ሀገረ ስብከቱም ሆነ ምእመናን ትኩረት ሊሰጡት ይገባል፡፡

ምእመናን ተጠምቀው ከተያዙበት ደዌ የሚፈወሱበት ጸበል ከገዳሙ በስተ ደቡብ ይገኛል፡፡ ጸበሉ በምንጭነት የሚፈልቅ ሲሆን ምንም አይነት ከለላ ስላልተደረገለት ለከብቶችና ለአራዊት የተጋለጠ ነው፡፡

የኢሱስ፤ የቅዱስ ሚካኤልና የአቡነ እንድርያስ ታቦታት፤ እንዱሁም የአቡነ እንድርያስ መቃብር በዚሁ ዋሻ ቤተ መቅደስ ውስጥ ይገኛሉ፡፡

አቡነ እንድርያስ ግንቦት 20 ቀን ወደ ገዳሙ እንደገቡና ጳጉሜ 3 ቀን እንዳረፉ ገድላቸው የሚገልጽ ሲሆን ዓመተ ምሕረቱን ግን አይናገርም፡፡ በዚህም መሠረት ግንቦት 20 ቀን በየዓመቱ በገዳሙ በዓላቸው ይከበራል፡፡

ገዳሙ ምንም ዓይነት የገቢ ምንጭ የሌለው ሲሆን አገልጋዮቹ የራሳቸውን የእርሻ መሬት እያረሱ በሚያገኙት ይተዳደራሉ፡፡

ተሰጣቸው መልስ ከስርዓተ ቤተ ክርስስቲያን ውጪ የሆነና በግለሰቦች በጎ ፈቃድ ላይ ብቻ የተመሰረተ ነበር፡፡ የቤተ ክርስቲያኑ ታሪክ፤ የዜና ማርያም ታሪክና ገድል በምስል ወድምጽ ወይም በፎቶ ግራፍ መውሰድ መልከሉን፤እንዲሁም በባህታዊያንና በአንድ አባት መወገዙን ተነግሯቸዋል፡፡ ለማሳመን ያደረጉት ጥረትም ሳይሳካ ቀረ፡፡ ሳይሳካላቸው መቅረቱ ብቻ ሳይሆን ወደ አዲስ ዘመን እየተመለሱ በረዶ በቀላቀለ ዝናብ መመታታቸው ደግሞ የሚያበሳጭ ነበር፡፡

ወይን ዋሻ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም፡-

Normal 0 false false false EN-US X-NONE X-NONE

ማእከላት ለኦዲትና ኢንስፔክሽን ሥራዎች ትኩረት እንዲሰጡ ተጠየቀ

ሚያዚያ 22 ቀን 2005 ዓ.ም.

በእንዳለ ደጀኔ

የማኅበረ ቅዱሳን ኦዲትና ኢንስፔክሽን አገልግሎት ክፍል ማእከላት ለኦዲትና ኢንስፔክሽን ሥራዎች ትኩረት እንዲሰጡ የክፍሉ ሓላፊ አቶ የሸዋስ ማሞ አስታወቁ፡፡

በአዲስ አበባ ለሁለት ቀናት ለሀገር ውስጥ ማእከላት ስለ ኦዲትና ኢንስፔክሽን አገልግሎትና አሠራር ዙሪያ ሚያዝያ 12 እና 13 ቀን 2005 ዓ.ም. በተሰጠበት ወቅት ነበር ማእከላት አገልግሎቱን አጠናክረው መቀጠል የሚገባቸው መሆኑን የተገለጸው፡፡

ማእከላት የሒሳብ ክፍል አሠራራቸውንና የኦዲትና ኢንስፔክሽን ክፍሎቻቸውን ይበልጥ  አጠናክረውና በሰው ኃይል አደራጅተው አገልግሎታቸውን መቀጠል እንዳለባቸው በሥልጠናው ላይ ተገልጿል፡፡

ለማእከላት በርካታ ሥልጠናዎችና የግንዛቤ ማስጨበጫ ዝግጅት እየተደረገ ሲሆን የማእከላቱ የግንዛቤ መጠን መጠነኛ ለውጦችን ማምጣት መቻሉን አቶ የሸዋስ ገልጸው ማእከላቱ ለኦዲትና ኢንስፔክሽን ሥራዎች ትኩረት እንዲሰጡና ክፍሉንም በባለሙያ እንዲያጠናክሩ ጥሪያቸውን ያቀረቡት፡፡ የአገልግሎት ክፍሉ እና የሒሳብ ክፍሉ መጠናከር የጎላ አስተዋጽኦ እንደሚኖረውና ለማእከላት ወጥ የሆነ የሒሳብ አያያዝ ሥርዓትም አዎንታዊ ተጽዕኖ ሊኖረው እንደሚችል አስገንዝበዋል፡፡

የአገልግሎት ክፍሉ የማኅበሩን ስልታዊ ዕቅድ ከማስፈጸም አኳያ የተለያዩ ድጋፎችን ለማእከላት የሚያደርግ መሆኑና በዕቅዱም ዘመን የራሱን የአገልግሎት ስልት ዘርግቶ እንደሚሠራ ነው ከሓላፊው ገለጻ የተረዳነው፡፡ ሚያዝያ 12 እና 13 ቀን 2005 ዓ.ም. በተሰጠው ሥልጠና በሀገር ውስጥ ከሚገኙ ማእከላት ተወካዮች በሥልጠናው መሳተፋቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚማሩ አባላት መንፈሳዋ ጉዞ አካሄዱ

ሚያዚያ 21 ቀን 2005 ዓ.ም.

በዳዊት ደስ

የማኅበረ ቅዱሳን የአዲስ አበባ ማእከል “መራሔ ፍኖት” በሚል መሪ ቃል በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እየተማሩ ላሉ የቤተ ክርስቲያን ልጆች መንፈሳዊ ጉዞ ወደ ሱሉልታ ደብረ ምሕረት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ሚያዚያ 20 ቀን 2005 ዓ.ም. አካሄደ፡፡

የጉዞውን ዓላማ አስመልክቶ አስተባባሪ የሆነው ሸዋለም ተክሉ ከዚህ ቀደም በግቢ ሲማሩ የነበሩ ተሞክሮአቸውን የሚያካፍሉበት፣ ተማሪዎች መንፈሳዊም ሆነ በሚማሩት ትምህርታቸው ያለባቸውን ጥያቄ የሚመለስበትና የክርስትና ሃይማኖት ተከታይ ሆነው ወደ ግቢ የማይመጡትን ተማሪዎችን በግቢ እየመጡ እንዲማሩ ለማድረግ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

አያይዘውም ይህ የግቢ ጉባኤ አንድነት መርሐ ግብር ለአራተኛ ጊዜ የተካሄደ ሲሆን ከጉዞው የሚጠበቀው ውጤት በመንፈሳዊ ሕይወታቸው የዛሉ የመንፈስ ብርታት የሚያገኙበት፣ የግቢያት የአባላት ቁጥር ወደተሻለ እድገት እንዲመጣ ለማድረግ ነው ሲሉ አስተባባሪው ተናገረዋል፡፡

በዕለቱ በግቢ ጉባኤ ተማሪዎችና በዘማርያም መዝሙር ቀርቢል፣ ትምህርተ ወንጌል የተሰጠ ሲሆን ግቢያቱ በተለያየ ርዕሰ ጉዳይ የተጠየቁ ጥያቄች ምላሽ ተሰጥተውባቸዋል፡፡ በመርሐ ግብሩ ሲሳተፉ ያገኘናቸው ወጣት ዮዲት ተገኔ የሮያል ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ተማሪ ስትሆን በዚህ ጉዞ ለመጀመሪያ ጊዜዬ ነው የተጓዝኩት፡፡ ጉዞው ትልቅ ነገር አስተምሮኛል፡፡ የሌሎችን ግቢ ጉባኤ ተማሪዎች ጋር አስተዋውቆኛል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ እየተሠራ ያለውን ተግባር እንዳይ አድርጎኛል በማለት ገልጻለች፡፡

ሌላው የ5 ኪሎ ግቢ ጉባኤ ተማሪ የሆነው ናትናኤል ስዮም በጉዞው በመሳተፌ በውስጤ ይመላለስ የነበሩብኝ ጥያቄዎች ተመልሰውልኛል፡፡ እንደዚህ አይነት መርሐ ግብሮች ወጣቱን የሚያንፁ ስለሆነ ማኅበሩ አጠናክሮ ሊሠራበት የሚገባ ተግባር ነው፡፡ ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡ በጉዞው ላይ ከ60 በላይ ከሚሆኑ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የመጡ ከሁለት ሺህ በላይ ተጓዦች ተሳትፈዋል፡፡