ዝርዝር  ርባታ

መምህር በትረማርያም አበባው

መጋቢት ፳፰ ቀን ፳፻፲፬ ዓ.ም

የተወደዳችሁ አንባብያን! እንደምን ሰነበታችሁ? የእግዚአብሔር አምላካችን ስም የተመሰገነ ይሁን! በተከታታይ በሁለት ክፍል የግሥ ዝርዝር ርባታ እንዳቀረብንላችሁ ይታወቃል፤ በዚህ የትምህርት ክፍለ ጊዜያችን ደግሞ የመጨረሻውን ክፍል ይዘንላችሁ ቀርበናል፤ በጥሞና ተከታተሉን!

አንቲ ውእቱን ስትወጂ፦

አፍቀርኪዮ/አፍቀርክዮ፤ወደድሽው

ታፈቅሪዮ/ታፈቅርዮ፤ትወጅዋለሽ

ታፍቅሪዮ/ታፍቅርዮ፤ትወጂው ዘንድ

አፍቅሪዮ/አፍቅርዮ፤ውደጅው

አንቲ ውእቶሙን ስትወጂ፦

አፍቀርኪዮሙ/አፍቀርክዮሙ፤ወደድሻቸው

ታፈቅሪዮሙ/ታፈቅርዮሙ፤ትወጃቸዋለሽ

ታፍቅሪዮሙ/ታፍቅርዮሙ፤ትወጃቸው ዘንድ

አፍቅሪዮሙ/አፍቅርዮሙ፤ውደጃቸው

  •  

አንቲ ይእቲን ስትወጂ፦

አፍቀርኪያ/አፍቀርክያ፤ወደድሻት

ታፈቅሪያ/ታፈቅርያ፤ትወጃታለሽ

ታፍቅሪያ/ታፍቅርያ፤ትወጃት ዘንድ

አፍቅሪያ/አፍቅርያ፤ውደጃት

  •  

አንቲ ውእቶንን ስትወጂ፦

አፍቀርኪዮን/አፍቀርክዮን፤ወደድሻቸው

ታፈቅሪዮን/ታፈቅርዮን፤ትወጃቸዋለሽ

ታፍቅሪዮን/ታፍቅርዮን፤ትወጃቸው ዘንድ

አፍቅሪዮን/አፍቅርዮን፤ውደጃቸው

አንቲ አነን ስትወጂ

አፍቀርኪኒ/አፍቀርክኒ፤ወደድሽኝ

ታፈቅሪኒ/ታፈቅርኒ፤ትወጅኛለሽ

ታፍቅሪኒ/ታፍቅርኒ፤ትወጂኝ ዘንድ

አፍቅሪኒ/አፍቅርኒ፤ውደጂኝ

  •  

አንቲ ንሕነን ስትወጂ፦

አፍቀርኪነ/አፍቀርክነ፤ወደድሽን

ታፈቅሪነ/ታፈቅርነ፤ትወጂናለሽ

ታፍቅሪነ/ታፍቅርነ፤ትወጂን ዘንድ

አፍቅሪነ/አፍቅርነ ውደጅን

 

አንትን ውእቱን ስትወዱ፦

አፍቀርክናሁ፤ወደዳችሁት

ታፈቅራሁ፤ትወዱታላችሁ

ታፍቅራሁ፤ትወዱት ዘንድ

አፍቅራሁ፤ውደዱት

  •  

አንትን ውእቶሙን ስትወዱ፦

አፍቀርክናሆሙ፤ወደዳችኋቸው

ታፈቅራሆሙ፤ትወዷቸዋላችሁ

ታፍቅራሆሙ፤ትወዷቸው ዘንድ

አፍቅራሆሙ፤ውደዷቸው

አንትን ይእቲን ስትወዱ፦

አፍቀርክናሃ፤ወደዳችኋት

ታፈቅራሃ፤ትወዷታላችሁ

ታፍቅራሃ፤ትወዷት ዘንድ

አፍቅራሃ፤ውደዷት

  •  

አንትን ውእቶንን ስትወዱ፦

አፍቀርክናሆን፤ወደዳችኋቸው

ታፈቅራሆን፤ትወዷቸዋላችሁ

ታፍቅራሆን፤ትወዷቸው ዘንድ

አፍቅራሆን፤ውደዷቸው

  •  

አንትን አነን ስትወዱ፦

አፍቀርክናኒ፤ወደዳችሁኝ

ታፈቅራኒ፤ትወዱኛላችሁ

ታፍቅራኒ፤ትወዱኝ ዘንድ

አፍቅራኒ፤ውደዱኝ

  •  

አንትን ንሕነን ስትወዱ፦

አፍቀርክናነ፤ወደዳችሁን

ታፈቅራነ፤ትወዱናላችሁ

ታፍቅራነ፤ትወዱን ዘንድ

አፍቅራነ፤ውደዱን

  •  

አነ ውእቱን ስወድ፦

አፍቀርክዎ፤ወደድኩት

አፈቅሮ፤እወደዋለሁ

አፍቅሮ፤እወደው ዘንድ

አፍቅሮ፤ልውደደው

አነ ውእቶሙን ስወድ፦

አፍቀርክዎሙ፤ወደድኳቸው

አፈቅሮሙ፤እወዳቸዋለሁ

አፍቅሮሙ፤እወዳቸው ዘንድ

አፍቅሮሙ፤ልውደዳቸው

  •  

አነ ይእቲን ስወድ፦

አፍቀርክዋ፤ወደድኳት

አፈቅራ፤እወዳታለሁ

አፍቅራ፤እወዳት ዘንድ

አፍቅራ፤ልውደዳት

  •  

አነ ውእቶንን ስወድ፦

አፍቀርክዎን፤ወደድኳቸው

አፈቅሮን፤እወዳቸዋለሁ

አፍቅሮን፤እወዳቸው ዘንድ

አፍቅሮን፤ልውደዳቸው

  •  

አነ አንተን ስወድ፦

አፍቀርኩከ፤ወደድኩህ

አፈቅረከ፤እወድሃለሁ

አፍቅርከ፤እወድህ ዘንድ

አፍቅርከ፤ልውደድህ

  •  

አነ አንትሙን ስወድ፦

አፍቀርኩክሙ፤ወደድኳችሁ

አፈቅረክሙ፤እወዳችኋለሁ

አፍቅርክሙ፤እወዳችሁ ዘንድ

አፍቅርክሙ፤ልውደዳችሁ

አነ አንቲን ስወድ፦

አፍቀርኩኪ፤ወደድኩሽ

አፈቅረኪ፤እወድሻለሁ

አፍቅርኪ፤እወድሽ ዘንድ

አፍቅርኪ፤ልውደድሽ

  •  

አነ አንትንን ስወድ፦

አፍቀርኩክን፤ወደድኳችሁ

አፈቅረክን፤እወዳችኋለሁ

አፍቅርክን፤እወዳችሁ ዘንድ

አፍቅርክን፤ልውደዳችሁ

  •  

ንሕነ ውእቱን ስንወድ፦

አፍቀርኖ/አፍቀርናሁ፤ወደድነው

ናፈቅሮ/ናፈቅራሁ፤እንወደዋለን

ናፍቅሮ/ናፍቅራሁ፤እንወደው ዘንድ

ናፍቅሮ/ናፍቅራሁ፤እንውደደው

  •  

ንሕነ ውእቶሙን ስንወድ፦

አፍቀርኖሙ/አፍቀርናሆሙ፤ወደድናቸው

ናፈቅሮሙ/ናፈቅራሆሙ፤እንወዳቸዋለን

ናፍቅሮሙ/ናፍቅራሆሙ፤እንወዳቸው ዘንድ

ናፍቅሮሙ/ናፍቅራሆሙ፤እንውደዳቸው

  •  

ንሕነ ይእቲን ስንወድ፦

አፍቀርና/አፍቀርናሃ፤ወደድናት

ናፈቅራ/ናፈቅራሃ፤እንወዳታለን

ናፍቅራ/ናፍቅራሃ፤እንወዳት ዘንድ

ናፍቅራ/ናፍቅራሃ፤እንውደዳት

ንሕነ ውእቶንን ስንወድ፦

አፍቀርኖን/አፍቀርናሆን፤ወደድናቸው

ናፈቅሮን/ናፈቅራሆን፤እንወዳቸዋለን

ናፍቅሮን/ናፍቅራሆን፤እንወዳቸው ዘንድ

ናፍቅሮን/ናፍቅራሆን፤እንውደዳቸው

  •  

ንሕነ አንተን ስንወድ፦

አፍቀነከ/አፍቀርናከ፤ወደድንህ

ናፈቅረከ/ናፈቅራከ፤እንወድሃለን

ናፍቅርከ/ናፍቅራከ፤እንወድህ ዘንድ

ናፍቅርከ/ናፍቅራከ፤እንውደድህ

  •  

ንሕነ አንትሙን ስንወድ፦

አፍቀርነክሙ/አፍቀርናክሙ፤ወደድናችሁ

ናፈቅረክሙ/ናፈቅራክሙ፤እንወዳችኋለን

ናፍቅርክሙ/ናፍቅራክሙ፤እንወዳችሁ ዘንድ

ናፍቅርክሙ/ናፍቅራክሙ፤እንውደዳችሁ

  •  

ንሕነ አንቲን ስንወድ፦

አፍቀርነኪ/አፍቀርናኪ፤ወደድንሽ

ናፈቅረኪ/ናፈቅራኪ፤እንወድሻለን

ናፍቅርኪ/ናፍቅራኪ፤እንወድሽ ዘንድ

ናፍቅርኪ/ናፍቅራኪ፤እንውደድሽ

  •  

ንሕነ አንትንን ስንወድ፦

አፍቀርነክን/አፍቀርናክን፤ወደድናችሁናፈቅረክን/ናፈቅራክን፤እንወዳችኋለን

ናፍቅርክን/ናፍቅራክን፤እንወዳችሁ ዘንድ

ናፍቅርክን/ናፍቅራክን፤እንውደዳችሁ

ይህ በቅኔ ቤት አእመረ፤ዐወቀ በሚለው ግሥ ይጠናል። ከላይ የጻፍነው በአድራጊ ግሥ ነው። በአምስቱ አእማድ ሁሉ እስከ መጨረሻው እንደዚህ ይረባል። ቀሪዎቹ አራቶቹን በውእቱ ንኡስ አረባብ ብቻ እንመልከታቸው። እናንተ ደግሞ ከላይ በጻፍኩላችሁ መልኩ የእያንዳንዱን አዕማድ እስከ መጨረሻው ማርባት ትችላላችሁ።

፩) አድራጊ፤ቀተለ-ገደለ

ይቀትል፤ይገድላል

ይቅትል፤ይገድል ዘንድ

ይቅትል፤ይግደል

፪) ተደራጊ-ተቀትለ ተገደለ

ይትቀተል፤ይገደላል

ይትቀተል፤ይገደል ዘንድ

ይትቀተል፤ይገደል

፫) አስደራጊ፤አቅተለ-አስገደለ

ያቀትል፤ያስገድላል

ያቅትል፤ያስገድል ዘንድ

ያቅትል፤ያስገድል

፬) ተደራራጊ፤ተቃተለ ተገዳደለ

ይትቃተል፤ይገዳደላል

ይትቃተል፤ይገዳደል ዘንድ

ይትቃተል፤ይገዳደል

፭) አደራራጊ፤አስተቃተለ አገዳደለ

ያስተቃትል፤ያገዳድላል

ያስተቃትል፤ያገዳድል ዘንድ

ያስተቃትል፤ያገዳድል

የእነዚህ ካልአይ አንቀጹ ጠብቆ ይነበባል። ሌሎች ላልተው ይነበባሉ። ዘንድና ትእዛዝ ላልቶ ይነበባል፤ ባለፉት ክፍሎች የጀመርነውና ዛሬ የጨረስነው አጠቃላይ የግሥ ርባታ ይህንን ይመስላል።

የመልመጃ ጥያቄዎች፦

የሚከተሉትን ቃላት የአማርኛ ትርጒማቸውን ጻፉ!

፩) ሠመርናሃ (ሠምረ፤ወደደ)

፪) ፈጠረኒ (ፈጠረ፤ፈጠረ)

፫) ኀረይኩክሙ (ኀረየ፤መረጠ)

፬) ነአኲተከ (አእኮተ፤አመሰገነ)

፭) መሐርኩከ (መሐረ፤ይቅር አለ)

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን!