መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
ርእሰ ዐውደ ዓመት
በጊዜ ሥጦታ ቀናት ተፈጥራዊ ዑደትን ተከትለውና ወራትን ተክተው ዘመንን ይፈጥራሉ፤ የዘመናት ለውጥም አዲስ ዓመትን ይተካሉ፤ ይህ ሁሉ ግን በእግዚአብሔር አምላክ ቅዱስ ፈቃድ ሆነ፤ እኛም ለአዲሱ ዓመት ዘመነ ማርቆስ እንደ ቸርነቱ ደረስን፡፡…
መልእክት
ክርስቶስ በከበረ ደሙ የዋጃችሁ ሃይማኖታችሁ የቀና የተወደዳችሁ ምእመናን ሆይ ልዑል እግዚአብሔርን ልናመሰግነው ይገባናል። በይቅርታው ገናናነት በጎ የሆኑትን ሁሉ ስለሰጠን የልዕልናውን ምስጋና ጨምረን እጅግ ልናበዛ ይገባናል። እስከዚህች ዕለትና ሰዓት አድርሶናልና።…
‹‹እኔ ሩፋኤል ነኝ››
በሃያ ሦስቱ የመላእክት ነገደ ሠራዊት ላይ እግዚአብሔር የሾመኝ እኔ ሩፋኤል ነኝ፤ እግዚአብሔር አብን ይቅር ባይ ልጁን አጽናኝና አዳኝ የሆነ መንፈስ ቅዱስን እናመሰግነው ዘንድ፤ በደብረ ጽዮን በሚደረገው የሺህ ዓመት ተድላ ደስታ የክብር ጽዋን በሚሰጣቸው ጊዜ ለቅዱሳኖቹ በጎ ነገርን እንድንሰጣቸው ያዘዘኝ ሩፋኤል እኔ ነኝ፡፡ ደግሞም በዚህች ቀን ከዕፀ ሕይወት ዐጽቅ ወስጄ ለተመረጡ ክርስቲያኖች በእጄ እንድንሰጣቸው እግዚአብሔር ያዘዘኝ ሩፋኤል እኔ ነኝ፡፡የሰማያት መዛግብትም ከእጄ በታች ተጠብቀው የሚኖሩ እኔ ሩፋኤል ነኝ፡፡ እኔም እግዚአብሔር እንዳዘዘኝ እከፍታቸዋለሁ፤ እዘጋቸዋለሁም፡፡
ወርኃ ጳጉሜን
የሰው ልጅ እግዚአብሔር አምላኩ ባደለው ሥጦታ ‹ጊዜ› በሕይወት ዘመኑ በበጎ ምግባር እንዲኖርና በጸሎት በጾም እንዲተጋ በዓመታት፣ በወራት እና በቀናት ምልልስ በሚያገኘው ዕድል ዘወትር ፈጣሪውን ደስ የሚያሰኝ ሥራ ሊሠራ እንዲገባ የጊዜ ጭማሪ ተደረገለት፡፡ ይህችም የጭማሮ ጊዜ እስከ ዕድሜው(ዘመኑ) መጨረሻ ከኃጢአት በሙሉ ይነጻ እንዲሁም ጸጋ በረከትን ያገኝ ዘንድ የቀናት ምርቃት ሆነችለት፤ ‹የጳጉሜን ወር› (ወርኃ ጳጉሜን) ተብላም ተሰየመች፡፡ …
ቅዱስ ቶማስ ዘመርዓስ
ቶማስ ማለት የስሙ ትርጉም ፀሐይ ማለት ነው፡፡ በቶማስ ስም የሚጠሩ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሚታወቁ በርካታ ቅዱሳን አሉ፡፡ ከነዚህ መካከል ቅዱስ ቶማስ ዘመርዓስ ናቸው፡፡ ቅዱስ ቶማስ ዘመርዓስ ትሩፋትና ገድሉን ሰው ተናግሮ ሊፈጽመው አይችልም፤ እርሱ አስቀድሞ ከልጅነቱ ቅዱሳት መጻሕፍትን የተማረ፣ ገና በወጣትነቱ መንኖ ገዳም የኖረ፣ በጾም፣ በጸሎት፣ በሰጊድ፣ ቀን እና ሌሊትም በመትጋት ለድኆችና ለምስኪኖችም በመራራት ተጠምዶ የኖረ ነበር፡፡ ቅዱስ ቶማስ ‹‹መርዓስ›› በምትባል አገር የወጣ የንጋት ኮከብ፣ ጻድቅ፣ ገዳማዊ፣ ጳጳስ፣ ሐዋርያ፣ ሰማዕትና ሊቅ ነው፡፡ የእርሱ ሕይወት ኦርቶዶክሳዊ የክርስትና ሕይወትና የጵጵስና የሹመት ሕይወት ምን እንደ ሆነ በትክክል የሚያሳይ ነው፡፡ መርዓስ በምትባል ሀገር ጳጳስ ሆኖ ተሹሞ በእረኝነት ያገለገል ዘንድ የክብር ባለቤት ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መረጠው፤ መንጋውንም እንደ ሐዋርያት ጠበቀ፡፡
የአቡነ ተክለ ሃይማኖት በዓለ ዕረፍት
ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሕይወታቸውን ሙሉ ለእግዚአብሔር በመስጠት፣ እንደ በሬ ተጠምደው፣ እንደ ገበሬ ታጥቀው ይህንን ዓለም ንቀው፣ በጾም በጸሎት ተወስነው በብሕትውና ከመኖራቸው ባሻገር እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት ወንጌልን በመላው ኢትዮጵያ እየተዘዋወሩ የሰበኩ፤ በጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ድውያነ ሥጋን በተአምራት፣ ድውያነ ነፍስን በትምህርት የፈወሱ ሐዋርያ ናቸው፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያችንም ነሐሴ ፳፬ ቀን የዕረፍታቸውን በዓል በትላቅ ደስታ ታከብራለች፡፡
‹‹በእግዚአብሔር ትእዛዝ ሦስት መቶ ሰባ ሁለት ዓመት ተኙ››
….እግዚአብሔር እውነቱን ሊገልጥ እና የሙታን ትንሣኤ በእርግጠኝነት እንደሚከናወን ሰዎችን ለማሳመን ፈለገ፤ እናም እነዚያን ሰባት ቅዱስ ወጣቶች ከእንቅልፉ አነቃቸው።….
‹‹ለችግረኛና ለምስኪን የሚያስቡ ብፁዓን ናቸው›› (መዝ. ፵፥፩)
ሰዎች በቅን ልቡና ተነሣሥተው ችግረኞችን መርዳት ይችሉ ዘንድ እነማንን መርዳት እንዳለባቸው ማወቅ ተገቢ ይሆናል፡፡ ምክንያቱም ችግረኞችን ለይተን ማወቅ ካልቻልን የሚለምኑ ሁሉ ችግረኞች እየመሰሉን ርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ነዳያን ተገቢውን ርዳታ ላናደርግላቸው እንችላለን፡፡ ለዚህም መስፈርት አድርገን የምናስቀምጣቸው መሠረታዊ ነገሮች ምግብ፣ አልባሳትና መጠለያ ያልተሟላላቸውን ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የጤና እክል ያለባቸው፣ በደዌ ዳኛ በአልጋ ቁራኛ የተያዙና ባለባቸው ችግር የተነሣ ሠርተው መብላት ያልቻሉ፣ አልባሽ አጉራሽ ቤተሰብም ሆነ ዘመድ የሌላቸውንም ችግረኞች እንላቸዋለን፡፡ በተጓዳኝ ረዳት ያጡ፣ ጠዋሪና ቀባሪ የሌላቸው አረጋውያን፣ ወላጅ አልባ ሕፃናት፣ በተለያዩ ምክንያቶች ቤት ንብረታቸውን አጥተው ከቀዬያቸው የተፈናቀሉትንም መርዳት ያስፈልጋል፡፡
‹‹ታቦርና አርሞንኤም በስምህ ደስ ይላቸዋል›› (መዝ. ፹፰፥፲፪)
በትንቢት ‹‹ታቦርና አርሞንኤም በስም ደስ ይላቸዋል›› ብሎ ነቢዩ ዳዊት እንደተናገረው ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ታቦር ብርሃነ መለኮቱን፣ ክብረ መንግሥቱን መግለጡን በማሰብ በየዓመቱ ነሐሴ ፲፫ ቀን በዓሉ በድምቀት ይከበራል፡፡ (መዝ. ፹፰፥፲፪)
‹‹ወደ አንተ የጮኹሁትን የልመናዬን ቃል ስማ›› (መዝ.፳፯፥፪)
መሪር በሆነችው በዚህች ዓለም ስንኖር እኛ ሰዎች ብዙ ችግርና ፈተና ሲያጋጥመንም ሆነ ለተለያዩ ሕመምና በሽታ ስንዳረግ እንዲሁም ለአደጋ ስንጋለጥ ስሜታችንን አብዛኛውን ጊዜ የምንገልጸው በዕንባ ነው፡፡ በተለይም አንድ ሰው የተጣለ መስሎ ሲሰማው በኃጢአቱ ምክንያት ቅጣት እንደመጣበት ሲያስብ ያለቅሳል፡፡ ጸጋ እግዚአብሔር እንደተለየው እግዚአብሔርም በጠላቶቹ እጅ አሳልፎ እየሰጠው እንደሆነ ሲያስብ ወደ ለቅሶ የሚያስገቡ መንፈሳዊ ምክንያቶች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በዚህም እጅግ ያዝናል፤ ያለቅሳልም፡፡ አንዳንዴ በፀፀት እና በንስሓ ውስጥ ሆኖ ያለቅሳል፤ አንዳንዴ ደግሞ እግዚአብሔርን እየወቀሰ ያለቅሳል፡፡