መንፈሳዊነት
ኦርቶዶክሳዊነት ርትዕት ሃይማኖት፣ ጽኑ እምነት፣ መልካም ምግባርና መንፈሳዊ እውቀት በአንድነት የተዋሐዱበት፤ አርአያ እግዚአብሔርን አጽንቶ በሐዋርያዊ የሕይወት ተጋድሎ እግዚአብሔርን በግብር ወደ መምሰል የሚታደግበት ፍጹም ሰማያዊ ሕይወት በመሆኑ፤ አባላት በየትኛውም ቦታ፣ ጊዜና ሁኔታ በማሰብ፣ በመናገር እና በመሥራት/በተግባር በሚገለጽ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ታንጸው፣ ፍኖተ አበውን ተከትለው፣ በታማኝነት እና በፈሪሐ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በቅንነት ያገለግላሉ::
አሰግድመኝ ቅድስት ማርያም ገዳም
ግንቦት 11 ቀን 2006 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በቀይት ወረዳ ቤተ ክህነት ሥር በጉዶ በረት አካባቢ የምትገኘውን ጥንታዊትና ታምረኛዋን ገዳም እንድንዘግብላቸው በተደጋጋሚ ቢሯችን በመምጣትና ስልክ በመደወል ቀጠሮ ያስያዙንን የርዕሰ አድባራት ወገዳማት ዳግሚት ፅዮን አዲስ ዓለም ማርያም ገዳም አስተዳዳሪ ንቡረ ዕድ አባ ገብረ ሕይወት መልሴ ጋር በነበረን ቀጠሮ መሠረት ሚያዚያ 15 ቀን 2006 ዓ.ም. ከሌሊቱ 12፡30 ወደ አሰግድመኝ ቅድስት ማርያም ገዳም ለመጓዝ በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በር ላይ እና ላም በረት አካባቢ ከሚገኘው መናኸሪያ በር ተገናኝተናል፡፡
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልኣተ ጉባኤ የ2006 ዓ.ም. ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ተጀመረ
ግንቦት 6 ቀን 2006 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የግንቦቱ ርክበ ካህናት ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ግንቦት 5 ቀን 2006 ዓ.ም. በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ቅዱስ ፓትርያርኩና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በጸሎት ተጀምሯል፡፡ ግንቦት 6 ቀን 2006 ዓ.ም. በቅዱስ ፓትርያርኩ የመክፈቻ መልእክት ጉባኤው ቀጥሏል፡፡
ለአብነት መምህራንንና ተማሪዎች የሕክምና አገልግሎት ተሰጠ
ሚያዚያ 30 ቀን 2006 ዓ.ም.
በዲ/ን ቴዎድሮስ ኃይሉ
በማኅበረ ቅዱሳን የሙያ አገልግሎትና ዐቅም ማጎልበቻ ዋና ክፍል የጤና ንዑስ ክፍል አስተባባሪነት በደብረ ሊባኖስ ገዳም፣ በምዕራፈ ቅዱሳን በልበሊት ኢየሱስ አንድነት ገዳምና በፍቼ ደብረ ሲና ዐራተ ማርያም ደብር ለሚገኙ የአብነት መምህራንና ተማሪዎች ከሚያዝያ 25 እስከ 27 ቀን 2006 ዓ.ም የሕክምና አገልግሎት ተሰጠ፡፡
በጠረፋማ አካባቢዎች ለተጠመቁ ወገኖች አብያተ ክርስቲያናት ለማነጽ ጥረት እየተደረገ ነው
ሚያዚያ 30 ቀን 2006 ዓ.ም.
በእንዳለ ደምስስ
የማኅበረ ቅዱሳን የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ ፕሮግራም በጠረፋማ አካባቢዎች ለተጠመቁ ወገኖች አብያተ ክርስቲያናት ለማነጽ ጥረት በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ገለጸ፡፡
በጂንካ፤በግልገል በለስ፤ በቦረና /ተልተሌ/፤ በቦንጋ/ጮራ/ እንዲሁም በሌሎች ጠረፋማ ወረዳዎች ነዋሪዎች ጥምቀት ተከናውኖላቸው የነበረ ቢሆንም ቤተ ክርስቲያን ሳይሠራላቸው ቆይቷል፡፡ የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ ፕሮግራምም ይህንን ችግር ለመፍታት ቤተ ክርስቲያን ለመሥራት ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡ ቤተ ክርስቲያን በማጣት ከአገልግሎት ርቀው ወደ ኢ-አማኒነት እንዳይመለሱ ምእመናን እገዛ ማድረግ እንደሚገባቸው የጠቀሰው የስብከተ ወንጌል ማስፋፊያው በቅርቡ ሊሠሩ ለታቀዱ ለ12 አብያተ ክርስሰቲያናት የግንባታ ግብአቶችን፤ በተለይም ቆርቆሮ፤ ምስማር፤ እንዲሁም ሌሎች ቁሳቁሶችን ምእመናን እንዲረዱ የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጊያ መርሐ ግብር በማኅበሩ ጽ/ቤት አዘጋጅቷል፡፡
“ሞቱንም በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን፡፡” ሮሜ 6፡5
ሚያዚያ 30 ቀን 2006 ዓ.ም.
በመ/ር ሳሙኤል ተስፋዬ
በጥንተ ጠላት ዲያቢሎስ አሳሳችነት አዳምና ሔዋን የእግዚአብሔርን ሕግ በመተላላፋቸው ሞተ ሥጋና ሞተ ነፍስ ተፈርዶባቸው ነበር፡፡ የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ አዳምና ሔዋን ከክህደት የደረሱት በዲያቢሎስ አሳሳችነት በመሆኑና ለሰው ልጆች ካለው ፍጹም ፍቅር የተነሳ የተፈረደባቸውን ሞት በሞቱ ሊደመስስ ሰው ሆነ፡፡ ዮሐ1፡1 ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደ፡፡ 30 ዓመት ሲሞላው ተጠመቀ፡፡ እንደተጠመቀም ልዋል ልደር ሳይል ገዳመ ቆሮንቶስ ሄደ፡፡ በዚያም ጾመ ጸለየ በዲያቢሎስም ተፈተነ፡፡ ሦስት ዓመት ከሦስት ወር ካስተማረ በኋላ አስቀድሞ ለአዳምና ለሔዋን ሞታቸውን ሊደመስስ፡፡ ዕዳቸውን ደመስሶ ነጻ ሊያደርጋቸው በገባው ቃል ኪዳን መሠረት መከራ ተቀበለ፤ በአይሁድ ሸንጎ ፊት ቆመ፣ ምራቅ ተተፋበት፣ ተገረፈ፣ በገመድ ታስሮ ተጎተተ፣ በመስቀል ተሰቅሎ ሞተ የአዳምና የሔዋንን ዕዳ በደል ደመሰሰ፡፡ ሞት ድል ተነሳ፡፡ ማቴ. 27-28
ማኅበረ ቅዱሳን በሬድዮ አገልግሎቱ የሞገድና ሰዓት ለውጥ አደረገ
ሚያዚያ 30 ቀን 2006 ዓ.ም.
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማኅበረ ቅዱሳን ድምጸ ተዋሕዶ የተሰኘውንና ዘወትር ዓርብ ከምሽቱ 3፡30 እስከ 4፡30 በአጭር ሞገድ 9850 kHz 19 ሜትር ባንድ ሲሰጠው በነበረው ሳምንታዊ የሬድዮ አገልግሎት ላይ የሥርጭት ሞገድና ሰዓት ለውጥ ማድረጉን አሳወቀ፡፡ ለውጡን ለማድረግ ያስፈለገበትን ምክንያት ዲ/ን ዶ/ር መርሻ አለኸኝ የማኅበሩ ሚድያ ዋና ክፍል ሓላፊ ሲያስረዱ «ቀድሞ መርሐ ግብሩ ይተላለፍበት የነበረው ሰዓት፤ ዘወትር ዓርብ ከምሽቱ 3፡30 እስከ 4፡30፤ በንጽጽር ምሽት ስለነበር በተለይ በክልል የሚገኙ አድማጮቻችን አገልግሎቱን አለማግኘታቸውን በልዩ ልዩ መንገድ ሲገልጹልን ቆይተዋል፡፡
የማኅበራችን አገልግሎት የክርስቲያናዊ ግዴታችን አካል ነው
ሚያዚያ 22 ቀን 2006 ዓ.ም.
ክርስቲያኖች የተጠሩት በክርስቶስ እንዲያምኑ በስሙም እንዲጠመቁ ብቻ አይደለም፤ ራሳቸውን ዝቅ አድርገው የፍቅርና የርኅራኄ ሥራ ለሰዎች ሁሉ እንዲሠሩም ነው፡፡ “ስለ እርሱ መከራ ደግሞ ልትቀበሉ እንጂ በእርሱ ልታምኑ ብቻ አይደለም” /ፊል 1÷29/ ያለው የሐዋርያው ቃሉ ይሄንን ያመለክተናል፡፡ ይኸውም የመንፈስ ፍሬዎችን ይዘን እንድንገኝ የታዘዝንበት ነው፡፡ /ገላ 5÷22/
የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት ለመልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙ የማስተማርና የመፈወስ ፈቃድ እንዳልሰጠ አስታወቀ፡፡
መጋቢት 11 ቀን 2006 ዓ.ም.
ከዚህ በፊት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ፈቃድ እንደተሰጠ ተደርጎ ሐምሌ 25 ቀን 2005 ዓ.ም. በቁጥር ል/ጽ/484/420/2005 የተጻፈውን ደብዳቤ ጽ/ቤቱ የማያውቀውና እውነትነት የሌለው የማጭበርበር ሥራ መሆኑን ገልጾ ምእመናን ይህንን ተገንዝበው እንዲጠነቀቁ ገልጿል፡፡
ሕገወጡንና በድጋሚ የታገዱበትን ደብዳቤ ከዚህ በታች ይመልከቱ፡፡
የባሕር ዳር ማእከል ሐዊረ ሕይወት( የሕይወት ጉዞ) ማዘጋጀቱን አስታወቀ
መጋቢት 10 ቀን 2006 ዓ.ም.
ግዛቸው መንግስቱ ከባሕር ዳር ማእከል
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማኅበረ ቅዱሳን የባሕር ዳር ማእከል ምእመናን በጾሙ ወቅት መንፈሳዊ በረከትና ዕውቀት እንዲያገኙ በማሰብ መጋቢት 21/2006 ዓ.ም ወደ ጥንታዊቷና ታሪካዊቷ አብችክሊ ጽርሐ ጽዮን ማርያም ቤተ ክርስቲያን ሐዊረ ሕይወት ቁጥር ፪ ማዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡ እንደ ማእከሉ ገለጻ የዚህ የሐዊረ ሕይወት መዘጋጀት ዋና ዓለማው ሕዝበ ክርስቲያኑ በመንፈሳዊ ሕይወቱ እንዲበረታና መንፈሳዊ እድገት እንዲያመጣ ማድረግ ነው፡፡ ዓላማውን ውጤታማ ለማድረግ በዕለቱ ጸሎተ ወንጌል በካህናት ይደረሳል፣ ምክረ አበውና ቡራኬ በሊቃነ ጳጳሳትና ገዳማውያን አባቶች ይሰጣል፣ የተጠየቁ ልዩ ልዩ ጥያቄዎች በሊቃውንቱ ምላሽ ያገኛሉ፣ ትምርህርተ ወንጌል፣ መዝሙር፣ መነባንቦችና ሌሎችም መንሳፈዊ መርሐ ግብራት በተያዘላቸው መርሐ ግብራት ይቀርባሉ፡፡
የዱባይ ሻርጃ አጅማን ሰአሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን 20ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ተከበረ፡፡
መጋቢት 10 ቀን 2006 ዓ.ም.
እርቅይሁን በላይነህ
በሊባኖስ የተባበሩት ዐረብ ኢምሬትና አካባቢው ክብረ በዓሉ የተካሄደው በዱባይ ከተማ ውስጥ በሚገኝ አንድ የእግር ኳስ መጫወቻ ሜዳ ላይ በተጣለ ድንኳን ሲሆን የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ብፁዕ አቡነ ድሜጥሮስ በበዓሉ ታድመዋል፡፡