የአባቴ ተረቶች
/in ኪነ ጥበብ /by Mahibere Kidusan ሕይወት ቦጋለ
ሐምሌ 16/2003 ዓ.ም.
ሌሊቱን ለረጅም ሰዓታት የዘነበው ዝናብ አባርቶ ቦታውን ለንጋት አብሳሪዋ ፀሐይ ከለቀቀ ቆየት ብሏል፡፡
ከመኝታዬ የተነሣሁት አረፋፍጄ ቢሆንም አሁንም የመኝታ ቤቴን መስኮት ከፍቼ አውራ መንገዱን እየቃኘሁ ነው፡፡ ለምን እንደሆነ ባላውቅም ዘወትር ከእንቅልፌ ስነሣ ሰፈራችን ሰላም ለመሆኗ ማረጋገጫዬ የመኝታ ቤቴ መስኮት ናት፡፡
ከመኝታዬ የተነሣሁት አረፋፍጄ ቢሆንም አሁንም የመኝታ ቤቴን መስኮት ከፍቼ አውራ መንገዱን እየቃኘሁ ነው፡፡ ለምን እንደሆነ ባላውቅም ዘወትር ከእንቅልፌ ስነሣ ሰፈራችን ሰላም ለመሆኗ ማረጋገጫዬ የመኝታ ቤቴ መስኮት ናት፡፡
ሁሉም ወደየ ጉዳዩ እንደየ ሐሳቡ መለስ ቀለስ ይለዋል፡፡ የቸኮለ ይሮጣል፣ ቀደም ብሎ የተነሣው ዘና ብሎ ይራመዳል፡፡ ሥራ ፈቱ ይንገላወድበታል ብቻ መንገዱ ለሁሉም ያው መንገድ ነው፡፡ እንደ እኔ ላጤነው ከቁም ነገር ቆጥሮ ላየው ደግሞ ለዓይን ወይም ለአእምሮ የሚሆን አንድ ጉዳይ አይታጣበትም፡፡ ያባቴን ተረቶች ናፋቂ ነኝና ወደሳሎን ወጣሁ፡፡
በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች የአቋም መግለጫ አወጡ።
/in ስብከት /by Mahibere Kidusan በተ/ሥላሴ ጸጋ ኪሮስ
ሐምሌ 11፣ 2003 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች ወቅታዊውን የተሐድሶ መናፍቃንን እንቅስቃሴና ተዛማጅ ጉዳዮችን አስመልክተው መግለጫ አወጡ። በሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ኃላፊ በልዩ ልዩ የመገናኛ ብዙሃን ከመምሪያው ሊቀ ጳጳስ እውቅና ውጭ «ተሐድሶ የሚባል ነገር የለም» በሚል የተሰጠው መግለጫ ሰ/ት/ቤቶች የማይቀበሉት መሆኑን አሳወቁ።
ለሐመር መጽሔት መካነ ድር /website/ ተሠራለት፡፡
/in ስብከት /by Mahibere Kidusan ለ18 ዓመታት ትምህርተ ሃይማኖታዊ ክርስቲያናዊ ሕይወትን፣ ማኅበራዊ ኑሮንና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን ምዕመኑን ስታስተምር የዘለቀችው ሐመር መጽሔት ለራሷ የሚያገለግል መካነ ድር ተዘጋጀላት፡፡የመካነ ድሩም አድራሻ(URL) http://hamer.eotc-mkidusan.org ነው።
የእግዚአብሔርን ቅንነት የተረዳ ቅዱስ አባት
/in ወቅታዊ ትምህርት /by Mahibere Kidusan ሐምሌ 8፣ 2003 ዓ.ም
ቅዱስ ኪሮስ ወደ አባ በብኑዳ በደረሰ ጊዜ ዐፅሙ በየቦታው ተበትኖ አንበሳ ሲበላው አገኘ በዚህም ሠዓት በጣም አምርሮ እያለቀሰ “ጌታ ሆይ፥ ለምን እንዲህ ታደርጋለህ ፍርድህ መልካም አይደለም፤ በመንግሥት፥ በመብልና በመጠጥ በደስታ የኖሩትን በክብር እንዲቀበሩ ታደርጋለህ፥ ስለ አንተ ሲሉ አባትና እናትን ሚስትን ልጆችን ደስታን ሁሉ ትተው በተራራና በዋሻ በጾምና በጸሎት የኖሩትን ደግሞ ሥጋቸውን ለዱር አራዊት ትሰጣለህ፥ “የአንተን ፍርድ ነገር ላልሰማ እንዳልነሣ ሕያው ስምህን” ብሎ መሬት ላይ ተኛ፡፡
“የሚያየኝን አየሁት”
/in ኪነ ጥበብ /by Mahibere Kidusan በትዕግሥት ታፈረ ሞላ
04/11/2003
የክረምት ብርድ በተለያየ ምክንያት ከቤቱ የወጣውን መንገደኛ ፊት አጨፍግጎታል፡፡ ሰጥ አርጋቸው ደርጉም ከቡድኖቹ ጋር የዕለት እንጀራውን ለመጋገር ታክሲ ውስጥ ገብቷል፡፡ እሱም ሆነ ጓደኞቹ የማውራት ፍላጎት የላቸውም፡፡ ሌሊት በእርሱ አጠራር “ግዳጅ” የሚሉት የተደራጀ የሌብነት ሥራ ሲሠሩ ስላደሩ እንቅልፍ በማጣት ዐይኖቻቸው ቀልተው አብጠዋል፡፡ የወረዛው የታክሲው መስታወት ላይ የእነሱ ትንፋሽ ተጨምሮበት በጉም ውስጥ የሚሔዱ አስመሰላቸው፡፡
መምሪያው ለቤተክርስቲያን ወጣቶች ተፈጠረ እንጂ ወጣቶች ለመምሪያው አልተፈጠሩም
/in የማኅበሩ መልእክት /by Mahibere Kidusan/ምንጭ፦ሐመር መጽሔት 19ኛ ዓመት ቁጥር 2 ሰኔ 2003ዓ.ም/
ለመንጋው ምሳሌ ሁኑ እንጂ ማኅበሮቻችሁን በኃይል አትግዙ 1ጴጥ. 5፣ 3
ቤተክርስቲያናችን በዚህ ዘመን ትኩረት ሰጥታ ልትፈጽማቸው ከሚገባት ተግባራት አንዱ፤ ወጣቶች በቤተክርስቲያን ውስጥ ያላቸውን አገልግሎት ከመቼውም ጊዜ በላይ ማሳደግና ቤተ ክርስቲያን የምትሰጠውን መንፈሳዊ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ነው፡፡ ይህ ጉዳይ ትኩረት እንዲሰጠው የሚያደርጉ በርካታ ነገሮች አሉ፡፡ በዋናነት ግን ሥጋዊው ዓለም በቤተክርስቲያን ወጣቶች ሃይማኖታዊ ሕይወትና መንፈሳዊ አኗኗር ላይ እያሳደረ ያለው ጫና ነው፡፡ ከመረጃ ቴክኖሎጂ ማደግና እርሱን ተከትሎ እየሰፋና እያደገ የመጣው የሉላዊነትና ዘመናዊነት አሉታዊ ገጽታ ባመጣው ግፊት፤ ወጣቶች ባሏቸው ክርስቲያናዊ ኑሮና እሴቶች ላይ ፈተና ደቅኖባቸዋል፡፡
የመዝሙር ዐውደ ርዕይ ተከፈተ
/in ስብከት /by Mahibere Kidusan በዲ/ን ቴዎድሮስ ኃይሉ
ሰኔ 29፣ 2003 ዓ.ም
በማኅበረ ቅዱሳን የአዲስ አበባ ማዕከል ትምህርትና ሐዋርያዊ አገልግሎት የመዝሙር ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ የመዝሙር ዐውደ ርዕይ ሰኔ 28/2003 ዓ.ም በሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ዶክተር ሙሉጌታ ስዩም እና በመዝገበ ጥበባት ጌትነት በማኅበረ ቅዱሳን ሕንጻ ላይ ተከፈተ፡፡
የወልደ ነጎድጓድ ልጆች እንቅስቃሴ
/in ስብከት /by Mahibere Kidusan በፈትለወርቅ ደስታ
ሰኔ 28ቀን 2003ዓ.ም
ጊዜው ትውልዱ በሶሻሊዝም ፍልስፍና እየተሳበ የነበረበት ነበር፡፡ 1960ዓ.ም ማለትም የዛሬ 43 ዓመት ሆነ፡፡ የቤተ ክርስቲያኗ አስተዳደር የነበሩት መምህር መዘምርና መምህር ዘውዴ የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ሰንበት ትምህርት ቤትን እንደመሠረቱት የሚነገረው በዚህ ጊዜ ነው፡፡ ሕፃናትንና ወጣቶችን በመሰብሰብ ምሥረታው አሐዱ የተባለው ሰንበት ትምህርት ቤት አሁን በሕይወት የሌሉት ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ የቅርብ ክትትል ይደረግለት ነበር፡፡ ብፁዕነታቸው የደብሩ አስተዳዳሪ በነበሩበት ወቅት አባላትን እንደልጅ እየኮተኮቱና እየተንከባከቡ ያሳድጓቸው ነበር፡፡ ቅዳሜና እሑድ የሚሰጠውን የትምህርት መርሐ ግብር የሚመጡትንም /የሚመደቡትን/ መምህራንና የሚያስተምሩትን ትምህርት በመቆጣጠርና በማረም ሰንበት ትምህርት ቤቱን ጥሩ ደረጃ ላይ አድርሰውታል፡፡
ትምህርተ ጦም በሊቃውንት
/in ትምህርተ ሃይማኖት /by Mahibere Kidusanሰኔ 24/2003 ዓ.ም.
በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
በዚህ ጽሑፍ ጦምን አስመልክቶ የቅዱሳን አባቶችን አስተምህሮ እንመለከታለን
አንድ የገዳም አበምኔት አንድ ወቅት አባ ጳይመን የሚባሉትን አባት “እግዚአብሔርን መፍራት እንዴት ገንዘቤ ማድረግ ይቻለኛል” ብለው ይጠይቋቸዋል፡፡ እሳቸውም ሲመልሱ “እንዴት ሰው በላመና በጣፈጠ መብልና መጠጥ ሆዱን እየሞላ እግዚአብሔርን መፍራት ገንዘቡ ሊያደርግ ይችላል? ስለዚህም ጦም እግዚአብሔርን ወደመፍራት ይመራል፡፡ የጦም የመጨረሻ ግቡ እግዚአብሔርን ወደመፍራት ማምጣት ነው” ብለው ይመልሱላቸዋል፡፡